2017-01-12 10:18:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስብከታቸው "የኢየሱስ ስልጣን መገለጫ ባሕሪ የነበረው ለሕዝቡ ያለው ቅርበት ነው" ማለታቸው ተገልጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 2/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሁለተኛው የኢየሱስ ስልጣን መገለጫ ባሕሪ የነበረው ለሕዝቡ ያለው ቅርበት ነው ማለታቸው ተገልጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመንካት ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ለሕዝብ ቅርብ መሆን ያለነን ስልጣን ያረጋግጣል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ኢየሱስ ለሕዝቡ የነበረው ቅርበት ከፈሪሳዊያን በተሻለ ሁኔታ ስልጣኑን ሊያረጋግጥለት ችሎ እንደ ነበር በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ በምንም ዓይነት ሁኔታ ለምጻሞችን እና በሽተኞችን መንካት በፍጹም ተጸይፎ” አያውቅም ነበር ብለዋል።

ነገር ግን በተቃራኒው ፈሪሳዊያን “ድኸ እና ያልተማሩ ሰዎችን ይንቁ ነበረ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በየ አደባባዩ ምርጥ የሚባሉ ልብሶችን በመልበስ መዘዋወር ይወዱ እንደ ነበረም ጭምረው ገልጸዋል።

በሦስተኛ ደረጃ ከሕግ አዋቂዎች እና ከፈሪሳዊያን  ለየት ባለ ሁኔታ የኢየሱስን ስልጣን የሚገልጸው “ኢየሱስ በቃል የተናገረውን በሥራ መተግበር መቻሉ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሱ በሚናገራቸው እና በሚሰራቸው ነገሮች መኋከል ከፍተኛ የሆነ ጥምረት መኖሩን ገልጸው አንድ የካህን ባሕሪ አለኝ የሚል ሰው ከማንነቱ የተለየ ሥራ እያከናወነ በሚገኝበት ወቅት ሁሉ ከእዛ ባሕሪ የሚጠበቅበትን ነገር በተግባር ባለማሳየቱ የተነሳ  ወደ ግብዝነት ተቀይሩዋል ማለት እንችላለን ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ከላይ የተጠቀሰውን አሳባቸውን በሚገባ ለማስረዳት በማሰብ የመልካሙን ሳምራዊ ምሳሌ መጠቀማቸው የታወቀ ሲሆን በወንበዴዎች ተደብድቦ የሞት አፋፍ ላይ የነበረውን ሰው አንድ ካህን ባየው ጊዜ መንገድ ቀይሮ አልፎ መሄዱን አስታውሰው ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ይህ በወንበዴዎች ተደብድቦ በሞት አፋፍ ላይ የነበረው ሰው ደም በደም ሆኖ ስለነበረ ደሙን መንካት እንደ መርከስ ይቆጠር ስለነበረ ላለመርከስ አስቦ ጥሎት መሄድ እንደ መረጠ ጨምረው ገልጸዋል።

በመቀጠልም ሌዋዊው ሰው በተመሳሳይ መልኩ ተደብድቦ በሞት አፋፍ ላይ የነበረውን ሰው አልፎት መሄዱን የገለጹት ቅዱስነታቸው ምን አልባትም ይህንን ያደረገበት ምክንያት ብዙ የሚሠሩ ጉዳዮች ስለነበሩበት እና በእዚህ ጉዳይ ውስጥ ራሱን አስገብቶ በየፍርድ ቤቱ መንከራተት ባለመፈልጉ ሊሆን እንደ ሚችልም ግልጹዋል።

በመጨረሻ ግን ኋጥያተኛ የተባለው እና በጊዜው ተገልለው ከነበሩ ማኅበረሰብ ውስጥ የወጣው ሳምራዊ ሰው ግን ለእዛ በወንበዴዎች ተደብድቦ በሞት አፋፍ ላይ ለነበረው ሰው በመራራት መልካም ነገርን አደርጎለት እንደ ነበረ የጠቀሱ ቅዱስነታቸው ይህም በጣም አስደናቂ እና አስገራሚ ተግባር ሊሆን የቻለበት ምክንያት ይህ ኋጥያተኛ የተባለው ሰው ይህንን መልካም የርኅራኄ ተግባር መፈጸም መቻሉ ነው ካሉ ቡኋላ ይህንንም ተግባር ከኢየሱስ ስልጣናዊ ነገር ግን በየዋህነት ከተሞላው አግልግሉቱ ጋር በማነጻጸር የኢየሱስ ስልጣን ለሕዝብ በጣም የቀረበ በመሆኑ የተነሳ ስልጣኑን ተጨባጭ በሆነ አገልግሎት አሳይቶ እንደ ነበረ ከጠቀሱ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.