2017-01-09 15:21:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ኣቢያተ ክርስትያን መልካም በዓለ ልደት ተመኙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዩሊዮስ ባሕረ ሃሳብ መሰረት እ.ኤ.አ. ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ላከበሩት የምስራቅ ሥርዓት ተክተታይ ለሆኑት አቢያተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለ አስተርእዮ ባከበረችበት ዕለት ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘንድ ባለው አት ፖነቲፊክስ የግል አድራሻቸው አማካኝነት የመልካም በዓለ ልደት መግለጫ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ ገለጡ።

በዚህ በዓለ አስተርእዮ ምክንያትም እኩለ ቀን ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማስሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በለገሱት አስተምህሮ፥ ለምስራቅ ተከታይ አቢያተ ክርስቲያን በዓለ ልደት የሐሴትና የብርሃን ቀን እንዲሆንላቸው በመመኘት ቅዱስ አባታችን የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን እንዲሁም የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን እንኳን ለበዓለ ልደቱ አደረሳችሁ ሲሉ። የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይትና ከተለያዩ ሃይማኖማኖቶች ጋር የሚደረገው ውይይት የሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አምብሮጆ ስፕረአፊኮ በበኵላቸውም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሚሥጢረ ትስብእትና በመካከላችን ማደሩን በጋራ ለመኖርና በሮቻችንን ከፍተን በወንድማማችነት መንፈስ ስደተኞች ምእመናንን ተፈናቃዮችን በጠቅላላ በተለያዩ ምክንያቶች ከቤታቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው በዓለ ልደት ለማክበር የተገደዱትን ሁሉ ለመቀበልና ለማስተናገድ ያብቃን እንዳሉ ባርቢ አስታውቋል።

ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ፥ ኢየሱስ ሕፃን በእግዚአብሔር እንታመን ዘንድ ያስተምረናል

በዚያ ለክርስትና ሕይወት እጅግ አዳጋች በሆነበት የዓለማችን ክልል የሚኖረው ማኅበረ ክርስቲያንና ብቸኛው ተስፋውም ወደ ሰማያዊ ቤት በማቅናት መኖር መሆኑ በማስተዋል እይታው በሰማያዊ ቤት በማድረግ የሚኖር መሆኑ በግብጽ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ተዋድሮስ በበዓለ ልደት ምክንያት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ባስደመጡት ስብከት ጠቅሰው፡ የእረኞችና የሰብአ ሰገል ፍኖት በመከተል የቅድስት ድንግል ማርያም እሺ እንዳልከው ይሁንልኝ በማለት መላ ሕይወቷን ለሰማያዊ ቤት በማወከፍ እግዚአብሔር በመልአከ ገብርኤል በኩል ላቀረበላት ጥሪ የሰጠቸው ሙሉ መልስ አብነት በማድረግ ለመኖር ተጠርተናል። የሰው ልጅ ሁሉ እይታው ወደ ሰማይ እቅንቶ ከመኖር ይልቅ በተጻራሪው እምቢ በማለት እይታውን ወደ ምድር አጥፎ ሌላውም በግዴየለሽነት የሚኖር አለ። አንዳንዱም የሚጸልይ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ በእግዚአብሔር ብርሃን ላይ ታምኖና በዚያ በዓለም የሰላም መሣሪያ እንድንሆን የሚያደርገውን የእግዚብሔር ብርሃንና ሰላም አስተንፍሶ አድርጎ ከመኖር እርቆ የሚኖር ይመስላል። እርሱ የሚሰጠው ሐሴት እንደዚያ በኖ የሚቀር የዚህች መሬት ሐሴት አይደለም እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ባርቢ አያይዘው፥

የመላ ሩሲያና ሞስኮ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በበኩላቸውም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በውስጣችን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ያሳድጋል ይኽ ትስብእት እንድናተኵርበት የሚያደርገን ግብረ ገባዊ ተምኔታዎች ለመከተልና በሕይወታችን ሰግወን ለመኖር የሚያበቃን ነው ብለው፥ ሁሉም ክርስቲያኖች ለመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ክፍት በመሆን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እርሱም ፍቅር ትእግስት ሌላውን የማገልገል ቍርጠኝነት በውስጡ እንዲያድግ ይፍቀድ ሕዝባችንን ያጋጠመውና ያለፈባቸው ከባድ ፈተናዎችና አደጋዎች ሁሉ በዚህ በተገባው 2017 አዲስ ዓመት የሩሲያ ታሪክ በጥልቅ የለወጥ ሁነቶች የምታስተነትንበትና ለረዥም ሺሕ ዓመታት ታይቶ የነበረው ሃይማኖትን የሚቃወም አማኞን የሚያሳድድ ለሞት የሚዳርግ ፖለቲካዊ ሥርዓት የተኖረበት ያለፈው ታሪክ ተለውጦ የተገኘው የሃማኖት ነጻነት ችላ እንዳይባልና በተለምዶ የሚኖር ሃይማኖት ከመከተል ገዛ እራሳችንን የሚናርቅበትና እምነትን የምናስተውልበት የምናስተነትንበት ይሁንልን እንዳሉ ገልጧል።

በኡክራይን ብፁዕነታቸው የኪየቭና በኡክራይ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ስቪያቶስላቭ ሸቭቹክ ስደተኞችና ተፈናቃዮች መካከል ተገኝተው በዘትንሳኤሁ ካቲድራል  ለበዓለ ልደት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በለገሱት ስብከት፥ ልደት በታሪካችን ውስጥ ህልው የሆነውን እግዚአብሔር ለይተን የምናውቅበትና ከእርስ ጋር የምንገናኝበት ዕለት ነው። ለሁሉም ሰብአውያን ስቃዮችና ችግሮች ውጣ ውረዶች አንድ መልስ የለም ሆኖም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ እርሱ እስከ ዓለም ፍጻሚ ድረስ ከእኛ ጋር መሆኑ እትፍሩ ብሎናል በዓለ ልደት ህላዌውን የተረጋገጠበት ዕለት መሆኑ ያስገነዝበናል። ስለዚህ የእኛ ፋንታ ይኸንን መለኰታዊ ሕፃን መቀበልና ማስተናገድ ብቻ ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.