2017-01-03 10:23:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የታኅሣሥ 24/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 23/2009 ዓ.ም. እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከተከበረው አዲስ ዓመት ጋር አብሮ በተከበረው ማሪያም የእግዚኣብሔር እናት ዓመታዊ ክብረ በዓልን አስምልክተው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት የእግዚኣብሔር እናት የሆነችውን ማሪያምን መቀበል “መንፈሳዊ ባዶነት” እንዳይሰማን ያደርገናል ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በስብከተቸው ጨምረው እንደ ገለጹት በተለይም ደግሞ ውሳኝ እና አደገኛ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ በምንገኝበት ወቅት ሁሉ ተስፋን እና ኋይልን የምታጎናጽፈን እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በመሆኑዋ እርሷን አጥብቀን መያዝ ይጠበቅብናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.