2016-12-30 16:32:00

አባ ስፓዳሮ፥ ቅዱስ አባታችን በቤተ ክርስቲያን የሕዳሴ ልኡክ ናቸው


በአውሽዊዝ የናዚው ፈላጭ ቆራጭ የዕልቂት ሠፈር፡ በግሪክ ለስቦ ደሴት የስደተኞችና የተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር በመሳሰሉት ክልሎች የተካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋያዊ ጉብኝቶች የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ከብፁዕ ወቅዱ ፓትሪያርክ ኪሪል ጋር ግንኙነት በስዊደን ሉንድ ለዝክረ 500 ኛው የሉተራን ተሓድሶ ቅዋሜ መሳተፍ የመሳሰሉት በተለይ ደግም በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተኖረው ቅዱስ የምሕረት ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በ 2016 ዓ.ም. ካከናወኑዋቸው ሂደቶች ውስጥ ለየት ባለ መልኩ ለመጥቀስ የሚቻል መሆኑ እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ፍጻሜዎች ርእስ ዙሪያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት በኢየሱሳውያን ልኡካን ማኅበር በሁለት ሳምንት አንዴ የሚታተመው ካቶሊካዊ ስልጣኔ ለተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ጠቅሰው፥ የቅዱስነታቸው የ 2016 ዓ.ም. መላ ክንዋኔዎች ጠቅለል ባለ መልኩ ማስተዋልና ምሕረት በተሰኙት ሁለት ቃላት ውስጥ ማካተት ይቻላል።

ምሕረት የሕዳሴአቸው ማእከል ነው። ይኽም ግላዊና ቤተ ክርስቲያናዊ መለወጥ የሚል ሲሆን፡ ይህ የሕዳሴ ተልእኮ በወንጌላ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በአበው ቅዱስ ታሪክ የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥልጣናዊ ትምህርት ላይ የጸና ሆኖ ይኸንን ጥልቅ ህዳሴ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልክ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው እንደተመረጡ ሳይውሉ ሳያድሩ ያነቃቁትና እግብ ላይ እያደረሱት ያለው ር.ሊ.ጳጳሳዊ ዓላማቸው ነው። ይኽ ህዳሴ በዚያ ወንጌላዊ ሐሴት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ የተመላከተ ነው ለማለት ይቻላል። ከአብ ፍቅር የሚነጥለን ምንም ነገር ማንም ነገር እንደሌለ ለማረጋገጥም የአብ ምሕረት ቲዮሎጊያዊ መጽሓ ቅዱሳዊ ሥነ ቤተ ክርስቲያናዊ በሕገ ቀኖናም ሳይቀር ትርጉምን በጥልቀት አሳውቋል። ትርጉሙም የአብ በር የአብ ልብና የቤተ ክርስቲያን በር መቼም ቢሆን የማይዘጋ ነው በሚል ሓሳብ ማጠቃለል ይቻላል ብሏል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስቃይ ምን ማለት ነው ለሚለው ጥያቄ የስቃይ ትርጉም በመስጠት አይደለም ያብራሩት፡ ስለዚህ ያንን ጥንታዊው የሥነ እግዚአብሔር ጥናት እንደሚያመለክተው ስቃይ በእግዚአብሔር ስም ምክንያታዊ ለማድረግ አይደለም የሞከሩት፡ በተቃራኒው እግዚአብሔር ለሚሰቃየው እጅግ ቅርብ ብቻ ሳይሆን አብሮ የስቃዩ ከሚሰቃየው በላይ ተካፋይ መሆኑ ነው ያብራሩት። ስለዚህ የሚሰቃየው ለምን ስቃይ ሲል ለሚያቀርበው ጥያቄ በመልካም አሳቢነት ደጋማና ጣፋጭ መልስ በመስጠት ሳይሆን በጽሞና በስቃይ ላይ ላለው ቅርብ መሆን ከጎኑ መሆኑ አብሮነትን መኖር የሚል ላይ የጸና ነው። በለያይ ግንቦች ክልል በቤተልሔም በአውሽዊዝ ቅዱስነታቸው ተገኝተው በጽሞና የኖሩት መንፈሳዊነት ያስተላለፉልን ጥልቅ ትምህርት በተግበር የሰጠው መልስ ነው። የሰዎችን ቁስል በመንካት የሚሰቃዩትን በመዳበስ የስቃያቸው ተካፋይ መሆን ነው። ይኽ ነው የክርስቶስ መስቀል። የመስቀል ቲዮሎጊያ እንደሚያመለክተውም ነው። ስለዚህ የሰብአዊ ስቃይ የእራስ አድርጎ የሥነ ማርያም ጥናትና ቅዱስ መጽሐፍ ባጠቃላይ እንደሚያስተምረው እርሱም እመ ጽሙረ - Stabat Mater ሁነትን መኖር የሚልና ይኽ የማርያም ጽሙርነትም አናትና ልጅ ልጅ እና እናት ያገናኘ ታሪካዊ ቅዱስ ኵነት ነው። ስለዚህ ይኽ በጽሞና ከሚሰቃየው ጎን መሆን አብሮ መሆን ዝምታ ወይን ባዶ ጽሞና ሳይሆን ባንጻሩ ሙሉና ጥልቅ ቅርበትና ውህደት የሚያመለክት ነው። ከሚሰቃየው ጋር ተጻማሪነት መኖር።

ይኽ መሆናዊ ግጭት በማለት የሚገልጡት መንፈሳዊ ውጣ ውረድ ከሌለ መንፈሳዊ ምቾት ላይ ከተኖረ የሚኖረው መንፈሳዊነ ትክክለኛ ነው ለማለት ያዳግታል። ይኸንንም በተለያየ ወቅት ቅዱስነታቸው ያሳሰቡት ምዕዳን ነው። ይኸንን ሃሳብ በጥልቀት የፍቅር ሐሴት በሚል ሐዋያዊ ምዕዳናቸው ዘንድ ያብራሩታል። በሰውና በእግዚአብሔር በሰዎች መካከል ያለው ግኑኝነት የታወከ ሊሆን ይችላል ውጣ ውረዱ ልክ የአንድ ልብ ህያው መሆኑ የሚያሳየው የልብ ትርታ የመለኪያው ሰንጠረዥ ከፍና ዝቅ ወደ ላይ ወደ ታች ሲል እንጂ ሙትንነት እንደሚያመለክተው በቀጥታ መስመር ላይ ሲጸና እይደለም። ስለዚህ የሕይወት ውጣ ውረድ ሕይወት ነው መንፈሳዊነት ነው። ሆኖም በዚህ ውጣ ውረድ የማስተዋል ሚዛን ሊኖረን ይገባል። ማስተዋል በጥሪዎች፡ በትዳር በክህነት በጠቅላላ በጥሪዎች ሁሉ። በእምነት ላይ የጸና የማስተዋል ብቃት። ቅዱስ አባታችን የደረሱዋቸው ሐዋርያዊ ምዕዳኖችና ዓዋዲ መልእኽቶ ስብከቶቻቸው አስተምህሮዎቻቸው አማካኝነት ለሰው ለሚሰቃየው ለቆሰለው ቅርብ መሆን የሚያሳስብ ተጨባጭ ምዕዳን እንጂ በስቃይ ለሁሉም ዓይነት ስቃይ ረቂቅ ቀመራዊ መልስ አላስቀመጡም።

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እርጋታ ነገሮችን የማመዛዘን  በማስተዋል ምንም’ኳ የሳቸውንም ሓሳብ አንዳንዴ ተቀባይነት ሳያገኝ ቢቀርም ታጋሽና ነገሮችን ተረጋግተው የሚያጤኑ ናቸው። አይረበሹም አጠገባቸውና ካጠገባቸው እራቅ ብሎ የሚፈጠረውን ነገር ሁሉ በጥሞና የሚከታተሉ የሚመረምሩ የሚያጤኑና የሚተነትኑ ናቸው ይኽ ደግሞ ጸላይነት ፍቅር ለቃለ ወንጌል ፍቅር ለቤተ ክርስቲያናዊ ለስልጣናዊ ትምህርትዋ ጭምር ባላቸው የፍቅር መንፈስ የሚያከናውኑት ጉዳይ ነው። ሰላምተኛነታቸው እርጋታቸውን በምንም ተአመር የማያዛቡ ናቸው። ጸላይ ናቸው። በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ የሚኖሩ በዚህ ፍቅር ውስጥ የተነከሩ ናቸው። ጸላይነታቸው በእውነቱ ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን ለሰው ዘር ሁሉ ጋሻ ነው በማለት አባ ስፓዳሮ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.