2016-12-29 11:37:00

ቅዱስነታቸው የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላላአፉት መልእክት ክፍል 6


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረቱን ዓለማችን እያጣች ያለውን “ነውጥ አልባ” የሆነ የፖለቲካ ባሕል መልሳ ትጎናጸፍ  ዘንድ ሁሉም ሰዎች በተለይም የዓለም የፖሌቲካ ኋይሎች የበኩላቸውን አስተዋጾ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸውና  ለግጭቶች ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ግጭቶችን የባሰ ከማፋፋም የዘለለ ፋይዳ እንደ ሌለውም መገለጻቸውን በታኅሣሥ 5/2009 ዓ.ም. ባስተላለፍነው የዜና ስርጭት መዘገባችን ይታወቃል።

ይህንን የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘት በተከታታይ ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት እነሆ ዛሬ ስድስተኛ  ክፍል እናቀርብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

 

ቁጥር 5

የነውጥ አልባ ፖሌቲካ ሥር መሠረት

የነውጥ መነሻ ሥር መሰረቱ የሰው ልብ ከሆነ የነውጥ አልባ እንቅስቃሴ ደግሞ በቀዳሚነት በቤተሰብ ውስጥ ነበረ ማለት እንችላለን። ቤተሰብ የማይነጣጠል የአባት እና የእናት፣ የልጆች፣ የወንድም እና የእህት ስብስብ ነው። በእዚህ ስብስብ ውስጥ ለሌሎች የማሰብ፣ ርኅራኄ የማሳየት፣ የመወያየት፣ የመከባበር፣ ለሌሎች መልካም የመመኘት፣ ይቅርታ የመደራረግ መንፈስ አለ። ከቤተሰብ ውስጥ የሚፈልቀው የፍቅር መንፈስ ደግሞ በዓለም ውስጥ በመሰራጨት ለሁሉም የማሕበረሰብ ክፍል ይዳረሳል። በመንድማማችነት እና በመከባባር ላይ የተመሰረተ አብሮ የመኖር ስነ-ምግባር በግለሰቦች እና በሕዝቦች መካከል ያለምንም፣ ፍርሃት፣ ነውጥ እና ጠባብ አስተሳሰብ ተወግዶ መልካም ስነ-ምግባር እንዲሰፍን በማድረግ በአላፊነት እና በመከባበር ላይ የተመሰረት ሐቀኛ የሆነ ውይይት እንዲደረግ ያደርጋል።

ስለዚህም ማንኛውንም ዓይነት የኒውክለር የጦር መሣሪያ እና ጅምላ ጨራሽ የሆኑ መሣሪያዎችን ማስወግድ ያስፈልጋል። በእየአከባቢው የሚታዩ ነውጦች፣ በሴቶች እና በሕፃናት ላይ የሚደረጉ ብዝበዛዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪ አደርጋለሁ።

በኅዳር ወር ውስጥ የተዘጋው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ራሳችንን በጥልቀት እንድንመለከት  እና የእግዚኣብሔር ምሕረት በዓለማችን ይገባ ዘንድ እንድንፈቅድለት ያበረታታናል። የነውጥ አልባ ፖሌቲካ የሚጀምረው ከቤታችን ውስጥ ሲሆን ይህም ከቤታችን የጀምረው የነውጥ አልባ ፖሌቲካ ለሰው ልጆች ሁሉ  ሊዳረስ ይችላል። ቅድስት ትሬዛ ዘ ሌዚዬክስ “ጥቃቅን የሚባሉ የፍቅር መግለጫ የሆኑ  እንደ መልካም ቃላት፣ ፈገግታ ያሉት ጓደኝነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በተቻለን መጠን መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ትመክረናለች። በተለይም ደግሞ የግጭቶች ሁሉ መንስሄ የሆነውን ራስ ወዳድነትን ማስወገድ ይጠበቅብናል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉትን መልዕክት ስድስተኛ ክፍል ሙሉ ይዘቱን ነበር ስትከታተሉት የቆያችሁት ቀጣዩን እና ሰባተኛውን ክፍል  በመጪው ዝግጅታችን እናቀርብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.