2016-12-28 16:46:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሐዋርያዊ አካላት የሰጡት ገጸ በረከት


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በበዓለ ልደት ምክንያት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ሐዋርያዊ አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት አገረ ቫቲካን በሚገኘው በቀለመንጦስ የጉባኤ አድራሽ ተቀብለው ምዕዳን ከለገሱ በኋላ ለአያንዳንዱ ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኢየሱሳውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር ገና የ 37 ዓመት እድሜ እያሉ አምስተኛ ጠቅላይ አለቃ ሆነው ለመመረጥ የበቁት ከሳቸው በፊትም ሆነ በኋላም አንድ ወጣት የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ በመሆን ሲመረጥ ይኽ የሳቸ የመጀመሪያ ሲሆን ለ34 ዓመታት በጠቅላይ አለቃነት ያገለገሉ በኢጣሊያ አትሪ ከተማ እ.ኤ.አ. መስከረም 14 ቀን 1543 ዓ.ም. የተወለዱ እ.ኤ.አ. ጥር 31 ቀን 1615 ዓ.ም. በሰማያዊ ቤት የተወለዱ አባ ክላውዲዮ አኳቪቫ ዳራጎና “የነፍስ ኅመምተኞችን ለመፈወስ የሚያሳካ ዘዴ” በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. በ 1600 ዓመታት ውስጥ የደረሱት የመንፈስ መቃወስና ኅመምን ለመፈወስ የሚያስችል ጸጋዊ ባህርይ ለመታደል የሚደረገው ጥረት ማእከል በማድረግ የደረሱት መጽሐፍ መለገሳቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክ ጋዜጠኛ ኤውጀኒዮ ሙራሊ አያይዘው የዚህ መጽሓፍ የአዲሱ ኅትመት የመግቢያውና መቅድም ጽሑፍ ደራሲ ለሆኑት የሮማ ጳጳሳዊ ዓቢይ የዘረእ ክህነት ትምህርት ቤት አበ ነፍስ አባ ጁዘፐ ፎርላይ ባደረጉላቸው ቃለ መጠይቅ፥ ይኽ መጽሐፍ በአባ አኳቪቫ በሕይወት በነበሩበት ዘመን ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸ የሚያገለግል በተለይ ለኢየሱሳውያን ተማሪዎች የቀሰተ ቢሆንም ቅሉ በዘመኑ እንዲህ ያለ መርሕና ገንቢ መንፈሳዊ መጽሐፍ ለዘርአ ክህነት ተማሪ ይድረስ የሚል አልነበረም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ዓበይት አካላት የለገሱት ምዕዳን ሕዳሴ ላይ ያተኮረ በመሆኑ ይኽ የአባ አኳቪቫ መጽሓፍ ለገጸ በረከት ሲመርጡ አለ ምክንያት እንዳይደል ለመረዳቱ አያዳግትም።

ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው በመሆኑም የበጐቹ ሙሉኣዊ ጤንነት ለመንከባከብ የሚያሰማራበት ግጦሽ ጤናማ መሆን አለበት። የቤተ ክርስቲያን እረኞችም የምእመናኖቻቸውን መንፈሳዊ ሰብአዊና ማኅበራዊ ጤንነት ለመንከባከብ ምእመናኑ የሚሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ጤናማ ሊሆን ይገባዋል። ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳቱ ውሉደ ክህነቱ ጤናማ ሊሆን ይገባዋል። ስለዚህ ይኸንን ለማከናወንም የማመዛዘን የማስተዋል ብቃት ያስፈልጋል። መጽሓፉ ይኸንን ነው የሚያመለክተው። ብፁዓን ጳጳሳት የገዳማትና የመንፈሳዊ የወንጌላዊ ልኡካን ማኅበራት አለቆች በቅድሚያ የመንፈስ ጤንነት የሚንከባከቡ መሆን ይጠበቅባቿል። ማለትም የእምነት ተመክሮ የሚመለከት በመሆኑ ነው። በገዳማዊ ባህልና በመንፈሳውያን ወይንም ልኡካነ ወንጌል ማኅበራት ባህል የማኅበሩ አለቃ አበ ነፍስ መሆኑ ይገለጣል። ይኽ ደግሞ የበነዲክቱስ ገዳም ሕግ የሚያመለክተው ሲሆን በሁሉም ማኅበራት የተሰራጨ ባህልም ነው። ከፈረንሳይ አብዮት በኋላ እንደታየው የማኅበራት የገዳማት አለቃ ወደ አንድ ተራ የማኅበሩ አቀናጅና አሰተባባሪ ባጠቃላይ የማኅበሩ ክንዋኔ የሚያስተባብር ተክለ ሰብነት ያለው እንደሆነ ተድርጎ ሲታይ ቆይቷል። ስለዚህ ኅዳሴው ይኸንን ሁሉ የሚያጠቃልልና ግምት የሚሰጥ ጉዳይ ነው። አኳቪቫ ከቤተ ክርስቲያን አበው በተለይ ደግሞ ከካሲያኖ የግረጎሪያ አቢይ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ደንብ እና ከገዛ እራሱ መንፈሳዊ ተመክሮ በመንደርደር ነው ያንን “የነፍስ ኅመምተኞችን ለመፈወስ የሚያሳካ ዘዴ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት፡ ያንድ አለቃ ተቀዳሚ ኃላፊነት የአባላቱን መንፈሳዊ ጉዳይ መንከባከብ የነፍስ ድህነት እንዲከወንም ወደ ኃጢኣት የሚገፋፋትን ምክንያቶች በመለየት የአንዱ አባል መታመም ለሁሉም መታመም ምክንያት ሊሆን ስለ ሚችል። ሁሉም እርስ በእርሱ በመደጋገፍ የምኅበረሰቡን ጤንነት የመጠበቅ ኃላፊነት የሚያበረታታ ነው። አለቃ ሲባል የተረጋጋ ጦርነት ካለ መኖር የሚታይ ሰላም በማኅበሩ ማስፈን ሳይሆን በማኅበሩ ውስጥ ወደ ፍጽምና የሚመራው ወንጌል በሰው ውስጥ የሚያነቃቃው መሠረታዊ ጥያቄ የሚያነቃቃ እርሱም ክርስቶስን በመከተል የሚያስከትለው ውስጣዊ ጥያቄ በማነቃቃት ስር ነቀላዊ መልስ ሰጭ መንፈስ የሚያነቃቃ ተክለ ሰብነት የተላበሰ መሆን ኣንዳለበት የሚያመለክት ሃሳብ ነው፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን እረኞች ይኸንን ተክለ ሰብነት ለበስ መሆን እንዳለባቸው ለማሳሰብና ለማስታወስ ነው መጽሓፉን የለገሱት ብሏል።

እረኛ የበጎቹን ጤንነት በሚገባ የሚያስተውል እያንዳንዱን የሚያወቅ። ሲታመም ሲተክዝ ባጠቃላይ ጉድለት ሲሰማው የሚረዳ የሚገነዘብ መሆን አለበት። እረኛው በጎቹ ማወቅና በጎቹም እረኛውን ማወቅ ይጠበቅባቿል። አባት ልጁን ልጁም አባቱን ማወቅ። አባ አኳቪቫ በመጽሓፋቸው አንድ አለቃ የበላይ መሆንና ተገቢ ውሳኔ የሚሰጥ ነገሮችን የሚቆጣጠር ቅጥ ያጣ ወይንም የተሳሳተ የእናትነት መንፈስ የሚኖር ቅጥ ያጣ ዘበኝነት ለሐሰተኛው ማኅበራዊ ሰላምታ የሚቆም ሳይሆን አባላቱን ወደ ክርስቶስ መምሰል የሚምራና ወደዚህ ክብር የሚያሳድግ መሆን እንደሚጠበቅበት ያሳስባል። ሁሉም ወደ ክርስቶስ መምሰል በግልን በጋራም ማደግ የሚል ነው። መለወጥ ሲባል ይኽ ነው። በአንድ ወንድም ላይ የማየው ግብረ እከይ በሁሉም የማህበሩ አባላት ላይ የማየው ሆኖ ሊሰማኝ ይገባል፡ ስለዚህ የአንዱ መታመም የሁሉም ስሜት የሚነካ መሆን አለበት እንጂ እኔን አይመለከተኝም የሚል ቃኤሊያዊ መንፈስ ሊኖር አይገባም።

ብዙውን ጊዜ ቅዱስ አባታችን በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እያጋቡት ያለው ሕዳሴ ከጥልቅ ማስተዋል የመነጨ መሆኑ ደጋግመው ይናገራሉ። ስለዚህ በቅድሚይ የገዛ እራስ ልብ ከማደስ የሚጀምር ነው። የመለወጥ ጸጋ እግዚአብሔር እንዲለግስልን መጸለይ። ቅርጾች መዋቅሮችን በሕግና በደንብ አንጻር ማደስ ቀላል ነው ነገር ግን በታደሰ በተለወጠ ሰው ካልተመሩ መታደሳቸው ትርጉም እይኖረውም ነገሮችን ለማደስ እራስን ማደስ ወሳኝ ነው። ስለዚህ የቅዱስነታቸው ህዳሴ ከልብ የሚመነጭ ነው። ካልሆነ ውጫዊ ህዳሴ ሆኖ ይቀራል፡ ይኽ መጽሓፍ ይኸንን ሁሉ በጥልቀት የሚያብራራ ነው። ቅዱስነታቸው እያጋቡት ያለውን ህዳሴ በጥልቀት ለመረዳት የሚደገፍም ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.