2016-12-28 14:31:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "ክርቲያኖች የአብርሃምን ፈለግ በመከተል ተስፋ በሌለበት ቦታ ተስፋ ማድረግ መማር አለባቸው" አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በታኅሣሥ 19/2009 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አደራችሁ! ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ አብርሃም የነበረውን ታላቅ ገጽታን በማስታወስ የእምነትን እና የተስፋን መንገድ ያሳየናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ስለ አብርሃም ጳውሎስ “አብርሃም ያመነው እና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ ባልነበረበት ጊዜ ነው፣ ስለዚህም የብዙ ሰዎች አባት ሆነ” (ሮሜ 4,18) ብሎ እንደ ጻፈ አስታውሰው ምንም ተስፋ ባልነበረበት ወቅት ተስፋ ማድረግ መቻሉ በራሱ በጣም ከባድ ነገር ነው ካሉ ቡኋላ አብርሃም ይህንን ተስፋ ያገኘው እግዚኣብሔር ያለውን ነገር ሁሉ በእምነት አምኖ መቀበል በመቻሉ እና ሚስቱ መሃን በመሆኑዋ የተነሳ እና እርሱም በእድሜ የገፋ ሰው በመሆኑ ምክንያት የቆረጠውን ተስፋ መልሶ ማለምለም ችሎ ነበር ብለዋል።

አብርሃም እግዚኣብሔር በገባለት ቃል በመተማመን የገዛ ሀገሩን፣ መሬቱን በመተው ዘርህን እንደ ባሕር አሸዋ አበዛለሁ በሚለው ተስፋ በመታመምን ሀገሩን ትቶ ሄዶ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው በሰዎች እይታ የማይቻል የሚመስለውን ነገር እግዚኣብሔር እንደ ሚያከናውን በማመን ጎዞውን ቀጥሎ ነበር ካሉ ቡኋላ ተስፋ የማይቻል የሚመስሉ ነገሮች እንዲከናወኑ ያደርጋል ብለዋል።

ተስፋ አንድ አንድ ጊዜም በጨለማ ውስጥ በመግባት ከእዚያ ጨለማ ባሻገር ያለውን ብርሃን እንድናይ ያደርገናል ያሉት ቅዱስነታቸው ለእዚህም ነው ተስፋ በጣም ጥሩ ነገር ነው የምላችሁ ተስፋ ሕይወታችን ወደ ፊት እንድንቀጥል ጉልበት ይሆናታል ብለዋል።

ነገር ግን በተስፋ የሚደረግ ጉዞ ሁሌም ቢሆን አልጋ በአልጋ ነው ማለት አይቻለም አብርሃምንም የገጠመው እውነታ ይህንኑ የሚያሳይ ነው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ተስፋ ምቾት የሚቀንስ፣ ቤቱን እና መሬቱን ጥሎ እኒሄድ የምያደርገ፣ ከጉዋደኞች እንዲለይ የሚያስገድድ ገጽታ ያለው ተስፋ ነበረ አምኖ የተቀበለው ብለዋል።

እነዚን ነገሮች ሁሉ ትቶ እግዚኣብሔር ወደ አመለከተው ሃገር አብርሃም ለመጉዋዝ ወጣ በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንደ ዛሬ ጊዜ  የመጓጓዣ ዘዴ ባልተስፋፋበት በእዚያን ወቅት ረጅሙን መንገድ በእግሩ ለመጓዝ አብርሃም ሀገሩን ለቆ ሄደ ካሉ ቡኋላ ጉዞው ረጅም እና ጊዜን የሚወስድ ነበረ በእዚያኑም ልክ ደግሞ የሚስቱ የሳራ ማሕጸን እንደ ተዘጋ ነበር በእዚህም አብርሃም ተስፋ አልቆረጠም ነበር፣ነገር ግን በእግዚኣብሔር ላይ አብርሃም ማጉረምረም ጀምሮ ነበረ ብለዋል።

በእግዚኣብሔር ላይ ማጉረምረም በራሱ አንድ የመጸለያ መንገድ ነው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ አንድ ጊዜም በንስሓ ስፍራዎች አንድ አንድ ሰዎች በእግዚኣብሔር ላይ አጉረምርሜ ነበር ሲሉ አድምጫለሁ ነገር ግን ይህን በምሰማበት ወቅቶች ሁሉ የምናጉረመርመው አባት ስለሆነ ነው ብዬ እመልስ ነበር፣ በእግዚኣብሔር ላይ ማጉረምረም መልካም ነገር ነው ብለዋል።

አብርሃም እግዚኣብሔርን “ጌታ ሆይ ምንም ልጅ የለኝም፣ የንብረቴም ወራሽ የሚሆነው የደማቆ ሰው የሆነው ኤሊዬዘር ነው” በማለት በእግዚኣብሔር ላይ አብርሃም አጉረምርሞ እንደ ነበረ ያወሱት ቅዱስነታቸው “ተተኪ ዘር ስላልሰጠህኝ የንብረቴ ወራሽ የሚሆነው የእኔ አገልጋይ ነው” በማለትም ጨምሮ ያጉረመርም ነበር ብለዋል።

ይህንንም ማጉረምረም የሰማው እግዚኣብሔር ደግሞ “ይህኛው አገልጋይ ያንተ ወራሽ አይሆንም ከአንተ የሚወለደው ልጅ ነው ወራሽህ የሚሆነው” ብሎ እግዚኣብሔር ለአብርሃም መልሶለት ነበረ ያሉት ቅዱስነታቸው ከቤቱ ውጥቶ ወደ ሰማይ እንዲመለከት ካደረገው ቡኋላ ወደ ሰማይ ተመልከት፣ ከቻልክ ኩዋክብትን ቁጠራቸው፣ ዘርህን እንዲ ነው የማበዛው ብሎት እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው በስተምህሮዋቸው አስታውሰዋል።

እግዚኣብሔር በተደጋጋሚ ለአብርሃም በሚያሳያቸው ምልክቶች የተነሳ የአብርሃም ተስፋ እየለመመለ እንደ መጣ ያወሱት ቅዱስነታቸው ይህም ተስፋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊለመልም የቻለው እግዚኣብሔር አብርሃምን ከድንኳኑ ውጥቶ ወደ ሰማይ እዲመለከት ካደረገው ቡኋላ መሆኑን ገልጸው በሚገባ ለማመን እንድንችል ነገሮችን በእምነት ዐይን መመልከት አስፈላጊ ነው ካሉ ቡኋላ በጊዜው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ከዋክብትን ያዩ ነበር ነገር ግን ለአብርሃም ከዋክብት ልዩ ትርጉም ነበራቸው፣ የተስፋ ምልክቶቹ ነበሩ ብለው እኛም ሁላችን ልንጓዝበት የሚገባው የተስፋ መንገድ እንድህ አይነቱ መነገድ ሊሆን ይገባል ካሉ ቡኋላ ይህም በእግዚኣብሔር ላይ ያለንን መተማመን በማሳደግ እንድንኖር ያደርገናል ካሉ ቡኋላ የእለቱን አስተምህሮ አጠናቀዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.