2016-12-24 12:22:00

ቅዱስነታቸው የገና እና የአዲስ አመት በዓልን አስመልክተወ ለቅድስት መንበር አበይት የአስተዳደር አካላት ያስተላለፉት መልእክት።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር የሚከበረውን የገን በዓል እና ከሰባት ቀን ቡኋላ የሚከበረውን አዲስ ዓመት በማስመልከት በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሣሥ 13/2009 ዓ.ም. ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ብጹዐን ካርዲናሎች እና ለቅድስት መንበር አስተዳድር አበይት አካላት ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደ ገለጹት የገና በዓል “አምላክ ፍቅራዊ የሆነ ትሕትናውን የገለጸበት  እንዲሁም አምላክ አስተሳሰባችንን በመቀየር ትክክለኛ መንገድ እንድንይዝ ያደረገበት በዓል ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

“የገና በዓል” አሉ ቅዱስነታቸው “ለዓለማችን ታላላቅ ለሚባሉ ሰዎች ወይም ደግሞ አስደማሚ እና አስደናቂ ለሆኑ ሐሳቦች እሺታን የምንገልጽበት በዓል ሳይሆን በአንጻሩ በእምነት ራሱን በትሕትና ለወደደን ለአምላክ አዎንታዊ ምላሽ እንድንሰጥ የተጠራንበት በዓል ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ለእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ብጹዐን ካርዲናሎች እና ለቅድስት መንበር አስተዳደር አበይት አካላት ያስተላለፉት መልዕክታቸውን የጀመሩት ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ለእነዚሁ የቅድስት መንበር የመስተዳድር አካልት ያስተላለፉትን የቅድስት መንበር አስተዳደር ሕዳሴ ያስፈልገዋል ብለው እንደ ነበር አስታውሰው ለእዚህም የሕዳሴ ሂደት የሚረዳ መዋቅራዊ መርሆችን እና እነርሱን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉትን ውጤቶችን ጠቅሰው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው መልዕክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “የቅድስት መንበር የአስተዳደር መዋቅር የማይነቃነቅ አስተዳደራዊ መሳሪያ አይደለም፣ ሕዳሴ በሕይወት የመኖራችን የመጀመሪያው እና ዋንኛው ምልክት ነው፣ በንግደት መንገድ ላይ ለምትገኘው፣ ሕይወት ላላት እና በመቀሳቀስ ላይ የምተገኝ ቤተ ክርስቲያን በመሆኑዋ የተነሳ ሕዳሴ ያስፈልጋታል” ብለዋል።

የሕዳሴው ዓላማ የቅድስት መንበር የመስተዳድር መዋቅርን ውበት ለማጎናጸፍ ታስቦ የሚደረግ ሕዳሴ አይደለም ያሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ መጨናነቅን እና መጣበብን ለመፍጠር ታቅዶ የሚተገበር ሕዳሴ አይደለም ካሉ ቡኋላ ይህ ሕዳሴ የሚከናወነው ለቤተ ክርስቲያናችን በማሰብ እና ቤተ ክርስቲያናችን ነቀፋ አልባ ቤተ ክርስቲያን ለማድረግ ታስቦ የሚደረግ ሕዳሴ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አክለውም በመልእክታቸው አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት በሕዳሴ ላይ የሚገኘው የቅድስት መንበር መስተዳድር ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በእዚሁ የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ በአዲስ ሰራተኞች ሲተኩ ብቻ ለውጥ ይመጣል ማለት ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ ታድሶ ስያደርጉ ነው ለውጥ ሊገኝ የሚችለው ብለዋል።

“ቅጣይነት ያለው ሕነጻ በራሱ በቂ አይደለም፣ ከሁሉም በላይ የሚያስፈልገን ቀጣይነት ያለው ለውጥ እና መጽዳት ነው” የሚገባን በማለት መልዕክታቸውን የጠሉት ቅዱስነታቸው “አስተሳሰባችን ካልቀየርን ተጨባጭ የሆነ ለውጥ ለማምጣት የምናደርገው ጥረት ከንቱ ሆኖ ይቀራል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ይህንን የሕዳሴ ጎዞ የሚቃወም ኋይል አለ፣ ይህም ከመጥፎ ልቦና የመነጨ ተቃውሞ እስካልሆነ ድረስ ጤናማ የሆነ ተቃውሞ ነው ማለት እንችላለን በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ረገድ 3 አይነተኛ የሚባሉ የተቃውሞ ኋይሎች እንዳሉም ገለጸዋል።

ከእነዚህም ተቃውሞዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ግልጽ የሆነ ተቃውሞ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ከመልካም  እና ሀቀኛ ከሆነ አስተሳሰብ እና ውይይት የሚመነጭ ተቃውሞ ነው” ካሉ ቡኋላ በድብቅ የሚካሄደው እና ሁለተኛው ዓይነት ተቃውሞ ደግሞ “ከደነደነ ልብ የሚመነጭ እና አንደ መንፈሳዊ ተሐድሶ ከማይፈልግ ከባዶ-ርቱዕነት ጋር ተያይዞ የሚመነጭ” ነው ካሉ ቡኋላ ሦስተኛው እና የመጨረሻው ተቃውሞ የሚምነጨው ከተንኮል አዘል ተቃውሞ ነው ይህም ተቃውሞ በሚመነጭበት ወቅት “ሕሊናችንን በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲያመራ በማድረግ እና ይህንንም ጤናማ ያልሆነ አስተሳሰብ ሰይጣን በሚፍጥርበት ወቅት በእዚህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ውስጥ ራሳችን ደብቀን ራሳችንን ለማጽደቅ በማሰብ ሌሎችን እነውቅሳለን ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተልም ይህ የሕዳሴ ጉዞ የተሳካ ውጤት ያመጣ ዘንደ የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ያፈልጋል ብለዋል።

  1. ግለሰቦች ራሳቸውን በመለወጥ የተሰጣቸውን ኋላፊነት በአግባቡ መፈጸም ይገባቸዋል
  2. ሐዋሪያዊ የሆነ ለውጥን በመቀናጀት ለሐዋሪያዊ ተግባራት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ይገባል።
  3. ኢየሱስን መአከል ያደረገ የተልዕኮ መንፈስ ማዳበር ያስፈልጋል።
  4. ግልጽ የሆነ አደረጃጀት መፍጠር ያስፈልጋል።
  5. የአሠራር ሕደትን ማሻሻል ያስፈልጋል።
  6. የአሠራር ሂደታችንን ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ማድረግ ያስፈልጋል።
  7. ተግባሮቻችንን በቅድስና መፈጸም ያስፈልጋል።
  8. ተግባሮቻችንን በመደጋገፍ መፈጸም ያስፈልጋል።
  9. ሥራችንን በወንድማማችነት መንፈስ ማከናወን ያስፈልጋል።
  10. ተግባሮቻችንን በካቶሊካዊ መንፈስ መተግበር ታፈልጋል።
  11. ሥራዎቻችንን ሙያዊ ክህሎትን በተጎናጸፈ መልኩ መተግበር ይገባል።
  12. ሥራዎቻችንን በቁርጠኝነት ማከናወን ይገባናል። ብለዋል

 








All the contents on this site are copyrighted ©.