2016-12-21 16:44:00

ጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምዕዳን እግብር ላይ በማዋል መርሓ ግብር


በዓመጽ በጥላቻ ምክንያት ዓለማችን መልከ ጥፉና አልቦ ሰብኣዊነት የተሞላ መሆኑ የተለያየ የመገናኛ ብዙኃን ዜና መዋዕላቸው የሚመሰክረው ነው። ሽብርተኝነት ሥልጣን የበላይነት የሕዝቦች የተፈጥሮ ሃብት ዘረፋና ብዝበዛ የሰው ልጅ ፍጡራዊ ሰብአዊ መብት ጥሰት ድኽነት የመሳሰሉት ዓለማችንና ሕዝቦችን ሁሉ እያደማ ያለው እኵይ ተግባር ሁሉ ጨርሶ እንዲወገድ በተለያየ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስለ ሰላም በሚያቀርቡት ጥሪም ሆነ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ጸሎትና ግኑኝነት በማነቃቃት ለያይ ግንብ ሳይሆን አገናኝ ድልድይ እንገንባ ስለ ድኾች መጠለያ አልቦ ስለ ሆኑት በማሰብ ስደተኞችን በመቀበል በማስተናገድ ለግብረ ሠናይ እንተባበር ሲሉ የሚያስተላልፉት ቀጣይ መልእክት ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ተማሪዎች ለየት ባለ መልኩ ባለንጀራህን እንደ ገዛ እራስህ ውደድ በሚለው ወንጌላዊ ቃል ሥር በማንበብ አምሳ ሰዓት ለሮማ በሚል መርሐ ግብር የመንበረ ጥበቡ የተማሪዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተል ቢሮ ያሰናዳው የአገልግሎት ተልእኮ ሥር በመሰባሰብ በሮማ ከተማ ጥጋ ጥግና ውጫዊ ክልል ለሚኖሩት ቅርብ በመሆንና ግብረ ሠናይን በዘርፈ ብዙ ተግባር እየመሰከሩ መሆናቸው የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታውቋል።

ወደ ውጫዊው የከተሞቻችንና የህልውና ክልል እንበል  የሚለው የቅዱስ አባታችን ጥሪ ያንን የሰው ልጅ የህልውና ውጫዊውን ሁነት በይባስ የገዛ እራሱ በማድረግ የተሰገወው ክርስቶስ እንዲኖር የሚሰጡት የአደራ ምዕዳን ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሰበካዎች ቁምስናዎች የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተቋማት ጳጳሳውያን መናብርተ ጥበብና ትምህርት ቤቶች እግብር ላይ እያዋሉት ናቸው ይኸንን ጉዳይ በተመለከተም የጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቢሮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ሚርኮ ኢንተሊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ይኽ የግብረ ሠናይ እቅድ አሁን ተወጥኖ የተተገበረ ሳይሆን በተለያየ ወቅት ቅዱስ አባታችን ለካቶሊካውያን ወይንም ለጳጳሳውያን መናብርተ ጥበብ ተማሪዎችና አስተማሪዎ የለገሱት ምዕዳኖች በማስደገፍ አስተንትኖ አውደ ጥናት በማካሄድ ምዕዳኖቻቸውን በተለያዩ የቲዮሎጊያ የጥናት ዘርፎች አማካኝነት በማጤን ጥሪውን እግብር ላይ ለማዋል አስቀድሞ ያሰናዳው መርሃ ግብር መሆኑ አብራተዋል።

ግብረ ሠናይ ለአንድ ክርስቲያን የትርፍ ግዜ አገልግሎት አይደለም ሁሉም ክርስቲያን በቤቱ በሚሰራበት በሚማርበት በጠቅላላ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ሊኖረው የሚገባው ጥሪ ነው፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ በእውነቱ ግብረ ሠናይ የፈረቃ ጉዳይ አለመሆኑ ለመረዳቱ የሚያዳግት አይደለም። አንድ የቶሪኖ ተማሪ እንዳለው መንበረ ጥበብ አገልግሎት ጭምር ማለት ነው። ጥበብ ማካፈል ግብረ ሠናይ ነው፡ ያለህን ማካፈል መቻል ጥበብ ነው፡ ከሁሉም የበለጠው ፍቅር ገዛ እራስ አሳልፎ መስጠት ነው። ይኸንን የበለጠውን ፍቅር በሁሉም መስክ መኖር ክርስቲያናዊ ጥሪያችን ነው።

ተማሪዎቹ በተለያዩ ሮማ በሚገኙት የስደተኞች መጠለያ ሠፈር፡ ለድኾና ለስደተኞች የሰብአዊ አገልግሎት መስጫ በሆኑት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥር በመንፈሳዊ ማኅበራት ገዳማት በቅዱስ ኤጂዲዮ እንቅስቃሴ በየቅድስት ተረዛ ዘካልኩታ ልጆች በአዲስ አድማስ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴና በሌሎች ካቶሊካውያን ተቋሞች ሥር በሚተዳደሩት ብሎም በተለያዩ ማከሚያ ቤቶች ወህኒ ቤቶች የጎዳና ተዳዳሪዎች በሚገኙበት ክልል ሁሉ በመሰማራት የሚፈጽሙት አገልግሎት መሆኑ አባ ኢንተሊያ ገልጠው፡ የላቀው ጥበብ ፍቅር ነው ጌታ ማፍቀርን ባለንጀራህንም ማፍቀር በማለት የሰጡትን ቃለ መጠይቅ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.