2016-12-21 16:53:00

ብፁዕ አቡነ ፒዛባላ፥ በማእከላዊ ምስራቅ ያለው የክርስቲያኖች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው አሉ


በሶሪያ በኢራቅ በግብጽ እና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ክልል አገሮች ያለው የክርስቲያኖች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ሊቀ ጳጳስ ሆነው በቅርቡ ከተሾሙ ወዲሁ ለመጀመሪያ ግዜ እንደ ፓትሪያርክ ከምእመኖቻቸው ጋር በመሆን በሚያከብሩት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶ በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሰመሩበት የቫቲካ ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ አስታወቁ።

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የማኅበረ ክርስቲያንንና የአቢያተ ክርስቲያን ሁኔታ ብዙዎች እንድሚሉት ተስፋ የሌለው ማለቂያ በሌለው ችግር ውስጥ የተነከረ ነው፡ ይኸንን የጠቀሱትም ብፁዕነታቸው በጋራ ሰላም እንገንባ በማለት ያሰመሩበተ ሃሳብ ዙሪያ “Mondo e Missione - ዓለምና ተልእኮ” ለተሰየመው መጽሔት ጋዜጠኛ ጆርጆ በርናርደሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ብፁዕ አቡነ ፒዛባላ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የማኅበረ ክርስቲያን ሁኔታ ለመግለጥ የተጠቀሙበት ቃል ብርቱ ሊመስል ይችል ይሆናል ሆኖም በክልሉ ያለው ወቅታዊው የማኅበረ ክርስቲያን ሁኔታ ካለ ምንም አጋኖና አቃሎ በትክክል የሚገልጥ ነው። በሶሪያ በኢራቅ በግብጽ የሚታየው የክርስቲያን ማኅበረሰብ ሁኔታ ዕለት በዕለት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን መስኮቶች በኩል ወደ መኖሪያ ቤቶቻን ጎራ የሚል ልሙድ ነገር ሆኗል። ይኸንን የማይለመደው ስቃይ ዜና ጽሑፍ ሆኖ መመልከቱና ማንበቡ ልሙድ እየሆነ ያለ ይመስላል። መካከለኛው ምስራቅ በአመጽ ተነክሯል። አመጽና ግጭት ባለበት ክልል ሁሉ የጦር መሣሪያ አምራች አገሮች የጦር መሣሪያ ንግድ ያጧጡፋሉ። አመጽ እየረገበ እንዳሄድ ይባስ ተቀጣጥሎ እንዲቀጥል ያደርጋሉ። የጦር መሣሪያ አቅርቦት የዓለም ኃያል የመሆን ሹኩቻ የሚረባረብ ክልል። አክራሪነት የሚፈጥረው ሽብርተኛነት መስፋፋት የሚያደማው ክልል ነው። በወታደር ኃይል ተክኖ ባለ ድል ሊኮን ይቻላል። ሆኖም ለዳግመ ግንባታ የሚበጀው ፖሊቲካ ነው። ስለዚህ ጦርነት ግጭት የመሳሰሉት ጸረ ሰብአውያን ድርጊቶች እንዲያከትሙም ግጭቶች እና አመጾችም እንዳይከሰቱ ጥበብ የተካነው ፖሊቲካ አሰፈላጊ ነው፡ በአሁኑ ወቅት ጥበብ የተካነ ፖሊቲካ ፈልጎ ከማግኘት ይልቅ ግመል በመርፌ ዓይን ማሳለፉ ሳይቀል አይቀርም ብሏል።

በእስራኤልና በፍልስጥኤም መካከል የሚደረገው የሰላም ድርድር ባለበት የሚራመድ እንዳውም መፍትሔ ከማስገኘት ይልቅ ወደ ችግር የሚወዘውዝ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ብፁዕ አቡነ ፒዛባላ የገለጡ ሲሆን ይኽ እውነት መሆኑ በርናርደሊ በማብራራትም ባንድ የሰላም ስምምነት ላይ ካልተቋጨ ካለው የዓለማችን ሁኔታ አንጻር ሲታይ ነገሮች ወደ ከፋ ያመራሉ። አሁንም ችግር የተሞላበት ሁኔታ ነው ያለው ሆኖም ጉዳዩ ሰላማዊ መፍትሔ ካልተገኘለት ጸጥታና ደህንነት ሁሌ በጦርነት የሚረጋገጥ ሆኖ እንዲቀር ያርጋል። በመሆኑም ዜጎች በሰላም ባህል ማነጽ አንዱ የችግሩ መፍትሔ እንደሚሆን ነው ብሏል።

በእስራኤል የሚገኙት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ያለባቸው ችግር ቀላል አይደለም። እነዚህ ትምህርት ቤቶች የሰላም ማእከሎች ናቸው፡ አክራሪነት ጽንፈኛነት መቼም ቢሆን መፍትሔ እንደማሆን በማስተማር ለማንም ፖሊቲካ አስተሳሰብና አመለካከት ጥገኛ ወይም ተገዥ ሳይሆኑ በቤተ ክርስቲያን የሥነ ማኅበረሰብአዊ ጠመቅ ትምህርት ላይ የጸና ሕንጸት የሚያቀርቡ በመሆናቸው በሁሉም ችግር ይደርስብቿል። ለተለየ አደጋም ተጋልጠው ይገኛሉ በማለት አያይዘውም  የሰላም ድልድይ ከመገንባት ይልቅ በቤተልሔም አቅራቢያ የተገነባው ግንብ በጣም የሚያሳዝን ነው። ምክንያቱም ግንቡ የተገነባበት መሬት የብዙ ክርስቲያኖች መኖሪያ ክልል የነበረበት ነው ስለዚህ ይኽ’ኳ ቢነገርም አወንታዊ ምላሽ አላገኘም።

በእስራኤልም ሆነ በፍልስጥኤም ውስጥ ላክራሪነት ለጸንፈኛነት የሚያንጹ ብዙ ናቸው በማለት ብፁዕ አቡነ ፒዛባላ የሰጡት መግለጫ እውነት ነው። ይኽ ሁነት ደግሞ በሁለቱ አገሮች ውስጥ ያሉት ሰላም ፈላጊዎችና የሰላም ባህል በማረማመድ ላይ ለሚገኙ አቢይ ችግር እየፈጠረ ነው። ምንም’ኳ ሰላም ፈላጊው ሕዝብ ተስፋ ሳይቆርጥ አሁንም ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት እየቀጠለበት ቢሆንም ሕይወቱ ላደጋ እያጋለጠ ይገኛል። ሕይወት ለአደጋ መጋለጡ አልቀረም ስለዚህ በጸረ ሰላም አመለካከት ሕይወትን ላደጋ ከማጋለጥ ይልቅ የላቀው እሴት ለማስፋፋት ሕይወትን ለአደጋ ማጋለጡ የላቀ ክብር አለው።

ብፁዕ አቡነ ፒዛባላ እንደገለጡትም በእየሩሳሌ በሳቸው በሚመራው የላቲን ሥርዓት የሚከተለው ሰበካ ዘርፈ ብዙ ሕዳሴ በማስገባት የሐዋያዊ ግብረ ኖልዎ ሂደት የሰበካው ተቋማትና በሰበካው በሚተዳደሩት የሕንጸት ተቋማት በጠቅላላ ዳግም በታደሰ መንፈስ ለማዋቀር እቅዱ እንዳለቨው ለማወቅ ተችላል። ይኽ ህዳሴ ሰላም ለማረጋገጥ የሚል ዓላማ ላይ የጸና ሰላም የሚያበረታታ እንደሚሆንም ገልጧል። ችግርና ውጥረት ባለበት ሁሉ የምሕረትና የእርቅ መሣሪያ ሆነን እንገኝ ብሏል። ህዳሴ ይኸንን ማእከል ያደረገ መሆኑ በርናርደሊ ከገለጡ በኋላ በማያያዝ በሁሉም አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት በማጠናከር ሃይማኖት የሰላም መሣሪያ እንጂ የግጭትና የአመጽ ምክንያት አለ መሆኑ ዕለት በዕለት መስከ የሁሉም ሃይማኖቶችና ምእመናኖች ኃላፊነት ነው፡ አምናለሁኝ እያሉ የግጭትን የአመጽ መሣሪያ መሆን የማይቻል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.