2016-12-21 15:00:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ክፍል አራት


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረቱን ዓለማችን እያጣች ያለውን “ነውጥ አልባ” የሆነ የፖለቲካ ባሕል መልሳ ትጎናጸፍ  ዘንድ ሁሉም ሰዎች በተለይም የዓለም የፖሌቲካ ኋይሎች የበኩላቸውን አስተዋጾ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸውና  ለግጭቶች ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ግጭቶችን የባሰ ከማፋፋም የዘለለ ፋይዳ እንደ ሌለውም መገለጻቸውን በታኅሣሥ 5/2009 ዓ.ም. ባስተላለፍነው የዜና ስርጭት መዘገባችን ይታወቃል።

ይህንን የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘት በተከታታይ ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት እነሆ ዛሬ አራተኛ  ክፍል እናቀርብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

ቁጥር 3.

መልካም ዜና

ኢየሱስ ራሱ የነበረበት ዘመን በነውጥ የተሞላ ዘመን ነበር። እርሱም ትክክለኛው የጦር መዳ የሚገኘው ነውጥ እና ሰላም በሚገኛኑበት በልባችን ውስጥ መሆኑን አስተምሮናል። ለእዚህም ነው በማርቆስ ወንጌል በምዕራፍ 7,23 ላይ “እነዚህ ሁሉ ክፉ ነገሮች ከሰው ልብ ይወጣሉ” በማለት ኢየሱስ የገለጸው። ነገር ግን በእዚህ ረገድ  ኢየሱስ የሰጠን አስተምህሮ አዎንታዊ የሆነ ገጽታ አለው። በዓይነታቸው ለየት ያሉ ተቀባይ እና ይቅር የሚለውን ምንም ቅድመ ሁኔታ የማይጠየቅበትን የእግዚኣብሔር ፍቅር ሰብኮናል። ደቀ-መዛሙርቱ ጠላቶቻቸውን እንዲወዱ አስተምሮዋቸዋል (ማቴዎስ 5,44) እንዲሁም አንደኛውን ጉንጫቸውን ለሚመታቸው ሰው ሌላኛውን እንዲያዞሩለትም አስተምሮዋቸዋል (ማቴዎስ 5,39)። ስታመነዝር ተገኝታ በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት የተፈረደባትን ሴት ከሳሾቹዋ ክሳቸውን እንዲያንሱ አድርጉዋል (ዩሐንስ 8,1-11)፣ እየሱስ ተላልፎ  በሰጠበት ሌሊት ሐዋሪያው ጴጥሮስ ያወጣውን ጎራዴ ወደ ሰገባው እዲመልስ ነግሮታል (ማቴዎስ 26,52) ኢየሱስ በሁሉም ረገድ የተከተለው የነውጥ አልባ መገድን ነበር።

በእዚህም መንገድ እስከ መጨረሻው ተጉዞ ነበር በእዚህም የጥብን መገድ አስወግዶ የሰላምን መንገድ እንድንከተል አሳይቶናል። ማንኛውም የክርስቶስን መልካም ዜና የሚቀበል ሰው ይህንን ነውጥ አላባ የሆነ መንገድ በመከተል በእግዚኣብሔር ምሕረት ይፈወሳል፣ የእርቅ መሳሪያም ይሆናል።

የአሲዚው ቅዱስ ፍራንቸስኮ በገዛ ራሱ ቃላት “በአፍህ ስለሰላም ከማውራትህ በፊት በልብህ ውስጥ ሰላም እንዳለ ማረጋገጥ አለብህ” ብሎ እንደ ነበረ ይታወቃል። ስለዚህም ትክክለኛ የኢየሱስ ተከታዮች ለመሆን እርሱ ያሳየንን ነውጥ አልባ አስተምህሮዎችን አቅፎ መያዝን ይጠይቃል። ከእኔ በፊት የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኔድክቶስ 16ኛ “በጣም ብዙ የሚባል ነውጥ በሚታይበት፣ ፍትህ በጎደለበት ዓለማችን ይህንን ሁኔታ ለመፍታት ወይም ለመጋፈጥ  የሚቻለው በብዙ ፍቅር እና መልካምነት ነው፣ ይህም በአብዛኛው የሚገኘው ከእግዚኣብሔር ነው” በተጨማሪም “ለውጥ አልባ የሆነ እንቅስቃሴ ለክርስቲያኖች አንደ አንድ የባሕሪ መቀየሪያ ዜዴ ተደርጎ የሚወሰድ ነገር ብቻ ሳይሆን የሰዎች ህልውና መገለጫ እና በእግዚኣብሔር ፍቅር የተማረከ ሰው እና የእርሱን ኋይል የተላበሰ ሰው በምንም ዓይነት መነግድ ክፉ ነገርን በፍቅር እና በእውነት ላይ ተመርኩዘው መዋጋት አይፈሩም፣ ጠላትህን ውደድ የሚለው ሐረግ የክርስትና ሕይወታቸው ምዕከል ሆኖ ሊቀጥል ያስፈልጋል” ብለው እንደ ነበር ይታወሳል።

ይህም በክፉ ነገር መሸነፍ የሚለውን አያካትትም ነገር ግን ለክፉ ነገሮች ሁሉ በመልካም መንገድ መልስ በመስጠት የኢፍታዊ ተጋባራት ማብቂያ እኒያገኙ ማድረግ ይቻላል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉትን መልዕክት አራተኛ ክፍል ሙሉ ይዘቱን ነበር ስትከታተሉት የቆያችሁት ቀጣዩን እና አምስተኛውን ክፍል በሚቀጥለው አርብ በታኅሣሥ 14/2009 ዓ.ም. እናቀብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.