2016-12-19 16:39:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 80 ዓመት ዕድሜያቸውን አከበሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም.  በጠቅላላ በሮማና በአገረ ቫቲካን ከሚኖሩት ብፁዓን ካርዲናሎች ታጅበው አገረ ቫቲካን በሚገኘው በፓውሊና ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ  80 ዓመት ልደታቸውን አክብሯል። ቅዱስነታቸው በዚህ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፥ ሃሴት የተሞላውና ፍሬያማ የሆነ በዕድሜ መግፋት ሁነት ተመኝተው እርጅናው መንበረ ጥበብ ሲሆን ነው ትርጉም የሚኖረው፡ የክርስትያን ሕይወት ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት የሚደረግ ጽናት የተሞላው ጉዞ ነው በማለት እንደገለጡ ያሳወቁት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አያይዘው፥ ቅዱነታቸው ስብከት ከማሰማታቸው በሁሉም ካርዲናሎች ስም መልእክት ያስደመጡት የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ መሆናቸው ገልጠው፥ ቅዱስ አባታችን ብዙውን ጊዜ በእድሜ የገፋው የኅብረተሰብ ክፍል ጠቅላይ መጥሪያው ወይንም ስሙ እርጅና የሚል ቃል ነው። ይኽ ቃል አክብሮት የለሽ ቃል ቢመስልም ተጨባጭ የሕይወት ምዕራፍም ነው፡

እርጅና መንበረ ጥበብ ይሁን

ቅዱስነታቸው ለ80 ዓመት ዕድሚያቸው ምክንያት ብፁዕ አቡነ ካቫሊየረ የለገሱላቸው ስጦታ አንድ “ሌላ ተጨማሪ ጠብታ” በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. በ 44 ዓ.ም. ቺቸሮነ በእድሜ መግፋት ወይን እርጅና ርእስ ዙሪያ የደረሰው ፍልስፍናዊ መጽሐፍ በማስታወስ እርጅና የሚል ቃል የሚያስፈራ ሊመስል ይችላል ይሆናል ሆኖም የሕይወት ምዕራፍ መሆኑ የሚያስገነዝብ ጥልቅ መጽሓፍ ነው፡

እ.ኤ.አ. መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄዱት ግኑኝነት በእድሜ መግፋት መንበረ ጥበብ ይሁን ሲሉ የገለጡት ሃሳብ መለስ ብለው በማስታወስ ለእኔም እንዲሁ ይሁንልኝ። የጥበብ የተስፋ የደስታ መኖር ምዕራፍ ጅማሬ ነው። ህልደርሊን በጻፈው ግጥሙ እርጅና መረጋጋትና ሃማኖተኛነትን ያሰማል ሲል በእድሜ የመግፋት ሁነት ምን ተመስለው ይገልጥልናል። ስለዚህ ለእኔም እንዲሁ እንዲሆንልኝ ጸልዩልኝ።

የእምነታችንን ጉዞ መመልከ

ቅዱስነታቸው የዕለቱን ምንባበ ወንጌል እርሱም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶ ትውልደ ሐረግ የሚዘረዝረውን ቃል ተንተርሰው የትውልድ ሐረግን የአለ መርሳት ተዘክሮ። ይኽ ተዘክሮ ጸጋ ነው። አለ መርሳትና ተዘክሮ ከፍቅር የሚመነጭ ተግባር ነው። ከየት መጣን ወዴትስ ነው እምንሄደው የሚለውን ጥያቄ በፍቅር ሥር ማንበብ፡ ስለዚህ የቀድሞ ወላጆቻችን አባቶቻችን የእምነት ጉዞን የምናስተነትንበት ጥያቄ ናቸው። ስለዚህ ተዘክሮ ጥሩ እንዲሰማን የማድረግ ኃይል አለው። በዚሁ መልክ ይኸው ቅዱስ በዓለ ልደትን እየተጠባበቅን እንገኛለን።

የዛሬው ወንጌል ለአንድ የሐጢአት ታሪክ የጸጋ ታሪክ አማካኝነት መልስ የሚሰጥ የድህነት ታሪክ መፈጸሙንም ያረጋግጥልናል። ማቴዎስ ምዕ. 1, 1-17 ባለው ምንባብ ከተዘረዘሩት ስሞች ውስጥ የተለያዩ ሰዎች ስም እናገኛለን ሁላችን የገዛ እራሳችን መሆናዊነታችንን የምናገኝበት ገጽ ነው። ታማኝነት በእምነት መጉደል ሐጢአተኛነት ሁሉን ዓይነት ሰዎችን የምናገኝበት ገጽ ነው። የዚህ የዘር ሃረግ ምንባብ ድህነት ፈላጊዎች መሆናችን እኔ ኃጢአተኛ ነኝ መዳኔ ካንተ ነው የምንልበት የእምነት ኑዛዜ መግለጫ ነው፡ ስለዚህ እኛም በተስፋ ሃሴት ወደ ፊት እንበል እንዳሉ ጂሶቲ አስታውቋል።

ክርስትና ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት የሚደረግ ጉዞ ነው

በነቃ ክርስቲያናዊ ጥበቃ … ነቅቶ መጠበቅ የምፅአትን ጊዜ መኖር። ጊዜ የሚለው ቃል ጥልቅ ትርጉሙ በዚህ ምጽአት በሚል ቃል የሚገለጥ ነው። ቆም ብለን ወደ ኋላ በመመልከት እስካለንበት ወደደረሰን መንገድ በመመልከት የጉዞው ውበትና ውህበትን እናደንቃለን። እግዚአብሔር የማያደናግር አምላክ ነው። ታማኝ ነው። ወደ ፊት እንድንል የሚያደርገንም እምነት ነው።

ይኸንን መኖር አልፎ ወደ ሌላ መገናኘት የማያሸጋግር ፍጹም መገናኘት ወደ ሆነው ምዕራፍ ነው ጉዞአችን። ከጌታ ጋር ለመገናኘት። የጊዜ ትርጉም የርስትናው ሕይወት ትርጉም እርሱ ነው። ስለዚህ ይኽ ጉዞ ያለፈውን ያለውን ታሪክ ያጠቃለለ በመዳን ተስፋ የሚነበብ ታሪክ ነው። ዛሬ የተነበበው የወንጌል ቃል ለምን እንደምናነበው ላይገባን ይችል ይሆናል እንዳውም ብዙዎች አሰልቺ ብለው ያስቡታል። እንትና እንትናን ወለደ እያለ በተዋለድ የጸናው የትውልድ ሐረግ ያትታል። ሆኖም እግዚአብሔር ሥጋ ለብሶ በሰዎች መካከል አብሮ መጓዝን እንደመረጠ የሚያረጋግጥ የመዳን ታሪክ ከምንነቱ ወዴትነቱ የሚያመለክት ነው፡ ጌታ አብሮም ከሁላችን ጋር ከእያንዳንዳችን ጋር በሕይታችን ታሪክ ውስጥ በመግባት አብሮን ይጓዛል።

ሁለተኛው ምንባብ ከዕብራውያን የተወሰደው መሆኑም በማስታወስ ምዕ. 12 ቁጥር 4 ላይ “… ገና ደም እስከ ማፈስስ ድረስ…” የሚል ቃን ጠቅሰው። ይኽ ቃል ወደፊት እንድንል የሚመክረን ቃል ነው። ምክር ነው። ብለው ጌታ ጸጋውን ይስጠን በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ ጂሶቲ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. የ80 ዓመት እድሜያቸውን ቀን በብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ታጅበው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ካከበሩ በኋላ የቁርስ ማዕድ አገረ ቫቲካን በሚኖሩበት ቅድስት ማርታ ሕንጻ ባለው ማዕድ ቤት በጳጳሳዊ የምጽዋት ጉዳይ የሚንከባከበው ቢሮ ተጠሪ በሆኑት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኮንራድ ክራየውስኪ የተሸኙት የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመቀበል አብረው ቁርስ በመቋደስ 80 ዓመት ልደታቸው አክብሯል።

በተለያዩ ቋንቋዎችም ከተለያዩ የዓለም መንግሥታት ተራ ምእመናን ከተለያዩ ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች ከ 50 ሺሕ በላይ የመልካም ልደት መግለጫ በእጦማር እንደደረሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታውቋል።

በሮማና አካባቢዋ ለሚገኙት ለጎዳና ተዳዳሪዎች በተለያዩ የድኾና የስደተኞች መጠለያ ሰፈር እና ለድኾች ማእድ በሚዘጋጅበት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በሚተዳደሩት የግብረ ሰናይ ማእከሎች በህሙማን ማገገሚያ በማከሚያ ቤቶች በእድሜ የገፉት የሚተዳደሩበት ማእከል ሁሉ አቢይ በዓል ሆኖ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመልካም ልደት መግለጫ መልእክት ተላፏል። እኚህ የድኾች አባት በሚል ስም ለሚጠሩት ቅዱስ አባታችን የጎዳና ተዳዳሪዎች ስማቸው የታተመበት ብርድ ልብስ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንደ ስጦታ አበርክቷል። በትውልድ አገራቸው በአርጀቲና በሁሉም ሰበካዎችና ቁምስናዎች የድኾች በዓል በሚል መጠሪያ ግብረ ሠናይ ማእከል ባደረገ ስነ ሥርዓት ተከብሮ መዋሉንም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታውቋል።

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ባስተላለፉት የመልካም ምኞች መግለጫ መልእክት ቅዱነታቸው በዓለም የሰዎች ግኑኝነት አወንታዊ እንዲሆን ለሚያደጉት ጥረት በኩባና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት መካከል ለረዥም ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ግኑኝነት ዳግም በመቀራረብ በአዲስ መንፈስ ግኑኝነቱ እንዲጀመር በሁለቱ አገሮች መካከል መልካም ግኑኝነት እንዲረጋገጥ ያደረጉት ጥረት ያስገኘው ውጤት ጠቅሰው ሲያመሰግኗቸው። የኢጣሊያ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፒየትሮ ግራሶ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ላውራ ቦልድሪኒ በሁሉም የኢጣሊያ የሕዝብና የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት አባላት ስም የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት የተላለፈ መሆኑም ጂሶቲ ገልጠዋል።

ቅዱስነታቸው ለ80 ዓመት ልደታቸው ምክንያት ለተላለፈላቸው የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረገጽ ባለው ኣት ፖንቲፊክስ በተሰየመው የግል አድራሻቸው አማካኝነት፥ “ለምታሳዩኝ ፍቅር አመሰግናለሁ። ስለ እኔ መጸለይ አትርሱ” የሚል መልእክት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ማስተላለፋቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ በዚሁ የቅዱስነታቸው ልደት ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተለያዩ አገሮች በሚገኙት ሰበካዎች ጭምር ስለ ቅዱስነታቸው መጸለዩ ጠቅሰው በቅዱስ ጴጥሮስ ከተገኙት ምእመናን ውስጥ አንዳንዶቹ በቀጥታ በቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አማካኝነት የመልካም ትውልድ ቀን መልእክት ማስተላለፋቸውና ሕጻናት እንወድዎታለን ሲሉ ብዙዎች ደግሞ እድሜና ጤንነትን ሲመኙ የድኻ ወዳጅ የሚሰቃዩትን እስታዋሽ ህሙማን አዛውንት የተናቀትን የሚገፉትን የሚበዘበዙትን ሁሉ አፍቃሪ አባታችን እንኳን ደስ አለዎት እድሜውን ያርዝም፡ የክርስቶስ ድኽነት በድኾች የሚገለጥ መሆኑ ካለ መታከት የሚያስተምሩ ቃሉና ትምህርቱን የሚኖሩ ትልቅ አባት ናቸው ተስፋን ፍቅርንና እምነት የሚመሰክሩ ናቸው፡  ማኅብራዊና ሰብአዊ ፍትህ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን የሚናገሩ አባት በማለት አድናቆታቸውን በመግለጥ ያኑርልን በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለጡትም ስፍር ቁጥር እንዳልነበራቸው አስታውቋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.