2016-12-17 10:50:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀን በተከበረበት ወቅት ያስተላለፉት የሰላም ምልዕክት ክፍል ሁለት።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረቱን ዓለማችን እያጣች ያለውን “ነውጥ አልባ” የሆነ የፖለቲካ ባሕል መልሳ ትጎናጸፍ  ዘንድ ሁሉም ሰዎች በተለይም የዓለም የፖሌቲካ ኋይሎች የበኩላቸውን አስተዋጾ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸውና  ለግጭቶች ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ግጭቶችን የባሰ ከማፋፋም የዘለለ ፋይዳ እንደ ሌለውም መገለጻቸውን በታኅሣሥ 5/2009 ዓ.ም. ባስተላለፍነው የዜና ስርጭት መዘገባችን ይታወቃል።

ይህንን የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘት በተከታታይ ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት እንሆ ዛሬ ሁለተኛውን ክፍል እናቀርብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

ቁጥር 1

“ነውጥ አልባ (nonviolence) እንቅስቃሴ ለሰላማዊ የፖሌቲካ ሂደት”

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር አሁን በመገባደድ ላይ በሚገኘው ዓመት መጀመሪያ ላይ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ እና ለሀገሮቻቸው ሰላምን ይጎናጸፉ ዘንድ ከልብ የመነጨ ምኞቴ መሆኑን ለሀገር መሪዎች እና አስተዳዳሪዎች፣ ለሐይማኖት ተቋማት፣ ለሲቪክ ማኅበረሰብ እና ለማኅበራት መሪዎች መግለጸ ይታወሳል።

ሰላምን ለእያንደንዱ ሰው በመመኘት በእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳያ የተፈጠረ እያንዳንዱ ሰው በእዚህ ክብር የተፈጠረ እና በእግዚኣብሔ ክብር የተሞላ መሆኑን እንድንገነዘብ ይረዳን ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው። በተለይም ደግሞ በግጭቶች ወቅት “ጥልቅ ለሆኑው የሰው ልጅ መብት” ክብር በመስጠት ነውጥ አልባ የሆነ የሕይወት መንገድ መምረጥ ተገቢ ነው።

አሁን እያከበርነው የምንገኘው ሃምሳኛውን ዓለማቀፍ የሰላም ቀንን ነው። ነገር ግን በመጀመሪያው ዓለማቀፍ የሰላም ቀን በተከበረበት ወቅት በጊዜው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ብፁዕ ጳውሎስ 6ኛ ለመላው የዓለም ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክታቸው “ አጉዋጊ በሆነው ሀገራዊ ስሜት፣ ነውጥ በመፍጠር ለውጥ ለማምጣት  በመሞከር፣ ወይም ደግሞ ጠንካራ የሆነ ስርዓትን በመዘርጋት ሳይሆን  ሰላምን ማረጋጋአጥ የሚቻለው ሰላምን የሰው ልጆች እድገት ዋነኛው መንገድ በማድረግ ብቻ ነው ሰላምን ማረጋገጥ የሚቻለው” ማለታቸው ያትወሳል።

በዓለም ላይ የሚታዩ አለመግባባቶች ምክንያታዊ የሆኑ ሐሳቦችን በማፍለቅ ማለትም በሕግ አግባብ ላይ መሰረት ባደረጉ ድርድሮች፣ በፍትህና በእኩልነት ሳይሆን ሊፈቱ የሚችሉት ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ ገዳይ ኋይል በመጠቀም ነው ሊፈቱ የሚችሉት የሚለው አስተሳሰብ በጣም አደገኛ ነው።

በአንጻሩም ከእኔ ቀደም የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዴክቶስ 16ኛ “Pacem in Terris” በአማርኛው ሠላም በምድር በሚለው ሐዋሪያዊ መልዕክታቸው እንደ ገለጹት “የሠላም ስሜት እና ፍቅር ሊረጋገጥ የሚችለው በእውነት፣ በፍትህ፣ በነጻነት እና በፍቅር ብቻ ላይ ተመሥርቶ ነው” ብለው መጻፋቸው ይታወሳል። ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ እነዚህ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ቃለት ተረስተዋል ወይም ደግሞ ጠቃሚነታቸው እና አስፈላጊነታቸው ትኩረት ተነፍጎት ቆይቱዋል።

ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ “ነውጥ አልባ”  ፖሌቲካዊ ለሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ትንታኔ ለመስጠት እፈልጋለሁ። ሁላችንም ነውጥ አልባ የሆነ የግል አስተሳሰብ እና እሴቶች ይኖሩን ዘንድ፣ ፍቅር እና ነውጥ አልባ የሆኑ ተግባራት እርስ በእራሳችን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ እና በዓለማቀፍ ደረጃ መተግበር እንችል ዘንድ  እግዚኣብሔርን  እንዲረዳን እጸልያለው።

ከእዚህ ቀደም የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች የበቀልን ስሜት ማስወገድ ከቻሉ እነርሱ ታማኝ የነውጥ አልባ እንቅስቃሴ አራማጆች ሊሆኑ ይችላሉ። በማንኛውም ዓለማቀፋዊ፣ አከባቢያዊ እና እለታዊ  ሁኔታዎች ወይም ተግባራት ውስጥ ነውጥ አልባ የሆኑ እንቅስቃሴዎች በግንኙነታችን እና በተግባሮቻችን በተለይም ደግሞ በፖሌቲካዊ ሕይወት ውስጥ የውሳኔዎቻችን መዐከል እንዲሆኑ ያስፈልጋል። 

 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ቅዱስ አባታችን ረዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉትን መልዕክት ሙሉ ይዘቱን ሁለተኛ ክፍል አቅርበንላችኋል ቀጣዩን እና ሦስተኛውን ክፍል በሚቀጥለው ሰኞ እናቀብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.