2016-12-17 11:28:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 8/2009 ዓ.ም. የሰማኒያ ዓመት ልደታቸውን አከበሩ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 8/2009 ዓ.ም. ሰማንያኛ ዓመት የልደት ቀናቸውን ማክበራቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው የእዚህን ዓመት የልደት በዓላቸውን የሚያከብሩት እንደ ተልመደው ብትልቅ ድግስ ሳይሆን የተለመደውን እለታዊ ተግባራቸውን በማከናወን እንደ ሚያከብሩትም ለመረዳት ተችሉዋል።

ከቫቲካን የወጥው ዜና እንደ ሚያሳየው ለቅዱስነታቸው የእንኳን አደረሶ መልዕክት መላክ ለሚፈልጉ በዓለም የሚገኙ ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ለእዚህ በዓል ተብሎ በተከፈተው የኢሜል አድራሻ ተጠቅመው የእንኳን አደረሶ መልዕክታቸውን ማስተላለፍ እንደ ሚችሉ መጠቀሱ ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው የልደት ቀናቸውን በተመለከተ ባለፉት ቀነት ባስተላለፉት መልዕክታቸው “ለኔ ትልቁ የልደት ስጦታ” መስጠት የሚፈልግ ሰው ካለ “ጸሎት ያድርግልኝ፣ ለእኔ ትልቁ ስጦታዬ ጸሎት ነው” ማለታቸውም ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.