2016-12-15 11:33:00

ቅዱስነታቸው ክህነታዊ ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚንጸባራቅ ክፉ ተግባር ነው አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 4/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በእዚህ ሳምንት ማብቂያ ላይ ቅዱስነታቸው ለመገናኘት በማሰብ ወደ ቫቲካን የመጡ ካርዲናሎች በተገኙበት ባሰሙት ስብከት ክህነታዊ ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚንጸባራቅ ክፉ ተግባር መሆኑን ገልጸው የእዚህ በደል የመጀመሪያዎቹ የገፈት ቀማሾች የሚሆኑት ሰፊው ሕዝብ እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ባስተላለፉት መልዕክታቸው እጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት እረኞች (ቄሳውስት) “የሃይማኖት ምሁራን” ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየት ከፍተኛ የሆነ አደጋ ስልሚያስከትል ከእዚህ አደጋ እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስበው ምክንያቱም ይህ “ሃይማኖት ሙሁራን” የመሆን ዝንባሌ ከእግዚኣብሔር ግብረገባዊ ግልጸት በእጅጉ የራቀ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

ድኾች እና በእግዚኣብሔር ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች የእዚህ “የሃይማኖት ሙሁራን” የመሆን ጽንሰ ሐሳብ ሰለባዎች ናቸው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የክህነታዊ ስልጣን ያባበላቸው” ሰዎች በፊት ቀድመው ወደ እግዚኣብሔር መንግስት የሚገቡት ኋጥያተኞች መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ በተነበበው የወንጌል ቃል የተጠቀሰውን ኢየሱስ የካህናት አለቆች እና በሕዝቡ የተመረጡ ሽማግሌዎች የተሰጣቸውን ተግባር በትክክል መተግበር እንደ ሚገባቸው አሳስቦዋቸው እንደ ነበረ ጠቅሰው “ይህም የተሰጣቸው ሕግን የማስከበር፣ ግብረገባዊ እና መንፈሳዊ ስልጣናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደ ሚኖርባቸው አሳስቦዋቸው እንደ ነበረ” ጨምረው ገልጸዋል።

እነዚ ታላቅ የሚባል ሥልጣን የተሰጣቸው ሰዎች ናቸው ለምሳሌም ሊቀ ካህናቱ ሐና እና ቀያፋ ናቸው ኢየሱስ ላይ ፍርድ እንዲፈረድ ያደረጉት፣ የካህናት አለቆች ናቸው አልዐዛርን ሊገሉት የፈለጉት፣ ይሁዳም ቢሆን ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ያባበሉት እነዚሁ የካህናት አለቆች ናቸው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የተሰጣቸውን ተግባር ወደ ጎን በመተው ሕግን ሽፋን በማድረግ በሕዝቡ ላይ እብሪተኛ እና አምባገነን ሆነው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ስለዚህም እነዚህ የካህናት አለቆች እና ሽማግሌዎች ሙሴ የሰጣቸውን አሥርቱን ትዕዛዛት ዘንግተው ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ራሳቸው በጥበብ በደነገጉዋቸው፣ ረቂቅ በሆኑ ሕጎች ውስጥ ራሳቸውን በማስገባት ጌታ የሰጠውን ቃል ችላ ብለውት ነበር ካሉ ቡኋላ ተጨባጭ ከሆነው የእግዚኣብሔር ግልጸት ጋር የሚያገናኛቸውን ትውስታ ዘንግተውት ነበር ብለዋል።

በቅድሞ ጊዜ የእዚህ ጥቃት ሰለባ የነበረው ኢየሱስ ነው፣ አሁን ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ የጥቃታቸው ሰላባ እየሆኑ የሚገኙት የዋሆች እና በጌታ ላይ ከፍተኛ እምነት ያላቸው ድኾች ናቸው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንደ እነዚ ዓይነት ሰዎች እብሪተኛ፣ ኩሩ፣ ከንቱ በሆኑ ሰዎች እንደ ተወገዙ እና እንደ ተበደሉ ይሰማቸዋል ብለዋል።

“እንደ እነዚህ ዓይነት ትሑት ሰዎች፣  ተጥለው የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባ ይሆናሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ዛሬም ቢሆን እኛ በምንኖርበት ዘመን ይህ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንጸባረቀ ይገኛል አንድ አንድ ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ውስጥም የእዚህ ዓይነት ሁኔታ ይታያል ካሉ ቡኋላ “ክህነታዊ ስልጣንን ያለ አግባብ የመጠቀም “ካህናት ከሁሉም በላይ እንደ ሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋል፣ በእዚህም ምክንያት ከሕዝቡ ይርቃሉ፣ ድኾችን የማዳመጫ፣ የሚሰቃዩ እና በሽተኛ የሆኑ ሰዎችን የመጠየቅያ ጊዜ እንኳን የላቸውም” ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.