2016-12-12 16:37:00

ቅድስት መንበር ለኤውሮጳ የጸጥታና የትብብር ማኅበር አግላይነትና ወጋኝነት ተግባር ጦርነትና አመጽ ይወልዳል


የኤውሮጳ አገሮች የጸጥታ ደህንነትና ትብብር ማኅበር በአባልነት በሚታቀፉት 57ና  በሽርክነት በሚያካትታቸው 11 የኤውሮጳ ክልል አገሮች አቀፍ ማኅበር እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 8 ቀን እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በሆምበርግ ከተማ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚና የፖለቲካ ርእስ ዙሪያ ባካሂደው ጉባኤ ቀዳሚነት በመስጠት የመከረባቸው ርእሰ ጉዳዮች እርሱም ዓለማዊነት ቅርጸ ለበስ ሆኖ በተለያየ ክልል የሚታየው ስላም የሚያናጋው ግብረ ሽበራ፡ በሶሪያ ያለው ጦርነት፡ የጦር መሣርያ ቅነሳ፡ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት በተሰኙትን ሌሎች በዓለማችን ክልሎች የሚታዩት ሰብአዊ ማኅብራዊ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሐሳብ ልውውጥ ማካሄዱና በተካሄደው ስብሰባም ቅድስት መንበርን ወክለው የቅድስት መንበር የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ፓውል ሪቻርድ ጋላገር መሳተፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

የማንኛውም ግብረ እኩይ መንስኤው ተገፊነት ነው

ሌላውን ማግለል ወይንም መግፋትና ተገፍቶ መኖር ሰወርተኛው የሰላም የጸጥታና የደኅንነት መደፍረስ ቀንደኛ መንስኤ ነው፡ በሚከናወኑት ቃል ኪዳናዊ ክብረ ስምምነቶች በስተጀርባ ብዙ ገጽታ ያለው ዘርፈ ብዙ የሆነው አድልዎና ምግባረ ብልሽት የሌላው ሰብአዊ መብትና ክብር ግድ ያለ ማለት የሰው ልጅ ክብር ለሞት የሚዳርግ ፍርህት አመጽና ጦርነት የመሳሰሉት ሰላም የሚያናጉ ተግባሮች ያስከተለ ከመሆኑም ባሻገር ይኽ ደግም በሰው ልጅ ሕይወት ላይ ዕልቂት የሚከስት ዓመጽና ጦርነት የሚያነቃቃ ፍርሃት የሚዘራና ብዙዎች ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የሚዳርግ ዋና ምክንያት ሆኖ ይገኛል። ልዩ የዓለም አቀፋዊ የጸጥታ ደህንነትና ትብብር ማኅበር ጭምር የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ተልእኮዎችም በተያዩ ክልሎች ለምሳሌም የዩክራይን ወቅታዊ ሁኔታ ጠቅሰው በማስታወስ የቶክስ አቁም ስምምነቶች እንዲከበሩ በማድረጉ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ የሰጠ ነው ሆኖም የውጥረቱ መንስኤ አዳፈነ እንጂ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ አላድረግም።  ጥላቻ ዘረኝነት የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ መስፋፋት፡ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ተግባር፡ የሰው ልጅ የውስጥ አካል ብልት ንግድ ለአቅመ አዳም ያልደረሱት ዜጎች ለወሲብ ዓመጽ መዳረግ፡ ለጾታዊ ስሜት ማርኪያን ንግድ መሣሪያ እንዲሆኑ የማድረግ ጸያፍ ተግባር፡ የአደንዛዥ እጸዋት ዝውወር አሸባሪነት የተደራጁ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት ዘርፈ ብዙ ሕገ ወጥ ተግባሮች በጠቅላላ ለአዲስ ባርነት ተግባር የሚያጋልጥ በዚህ ሰለጠነ በሚባለው ዓለማችን ሲከሰት ማየቱ ከማሳዘንም አልፎ በዓለማችን የሚኖረው ስልት እጥያቄ ውስጥ የሚያስስገባ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ ጋላገር አያይዘው፥

ሴቶችና ሃይማኖቶች ለሰላም መረጋገጥ ጥረት አብነት ናቸው

ሰላም ጸጥታና መረጋጋት ለኤውሮጳ ከአግላይነት ተገፍቶ መኖር የሚለው ጥያቄ ጋር የተሳሰረ ችግር መሆን አለበት። ማለትም ከኤኮኖሚው እድገት ተገለው እንዲኖሩ የሚገደዱት የኤኮኖሚው ዓለም የሚከተለው አግላይ ደንብ ላለመረጋጋት አቢይ ጠንቅ ነው። ሰላም ለማረጋገጥ ጦርነትና ግጭት ከወዲሁ እንዳይከሰት በሚደረገው ጥረት ሁሉ ሴቶችና ሃይማኖቶች አቢይ ሚና አላቸው። ሃይማኖት ለሰላም ለሰላማዊ አብሮ መኖር ጉዳይ እክል ሊሆኑ ፈጽመው አይችሉም። የዚህ ምስክርም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአፍሪቃ በላቲን አመሪካ ክልል አገሮች ሰላም እንዲረጋገጥ ያደረጉት ጥረትና የተደረሰው ውጤት እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ 1965 ዓ.ም. የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤትና የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በፖላንድና በጀርመን መካከል እርቅ እንዲደረግ የእርቅ የሰላም ይቅር የመባባል ባህል እንዲስፋፋ የሚጠራ ያስተላለፉት መልእክት እንደ አብነት ዘክረው ሃይማኖ መቼም ቢሆን ጸረ ሰላም ሊሆን አይችልም እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታውቋል።

ስደተኞችና ተፈናቃዮችን ለብቻቸው እንዳይተዉ አደራ

ብፁዕነታቸው ባስደመጡት ንግግር ምግባረ ብልሽት ለዓመጽ ጠንቅና ብሎም በድኽነት የሚጠቁት ዜጎች ለከፋ ስቃይ የሚያጋልጥ ኢግብረ ገባዊ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ከድኾች ዕለታዊ እንጀራ የመንጠቅ ተግባርና ድኽነት እንጅግ እንዲስፋፋና ምግብረ ብልሽት ቅርጽ ለበስ ሆነ እንዲስፋፋ የሚያደርግ ተግባር እየሆነ ሰላም የሚነሳና ማኅበራዊ ህውከት እንዲለኰስ የሚያደርግ መሆኑ በአጽንኦት ከገለጡ በኋላ በዓለማችን የሚታየው ስደትና መፈናቀል የሚወልደው ማኅበራዊ ኢእኩልነት የኤኮኖሚ አድልዎ፡ ስግብግብነት የሌላውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት መሆኑ አብራርተው ዓመጽና የተፈጥሮ አደጋ የመሳሰሉት በሃይማኖትና በጎሳ ምክንያት የሚፈጸመው ረገጣና ስደት አድልዎ ጭምር የሚወልደው ነው። እነዚህ ችግሮች ሁሉ ለዓለም ጸጥታና መረጋጋት መሰናክል ከመሆናቸውም አልፎ በአንድ አገር ሕዝብ ውስጥ ልዩነት በማስፋት ውሁዳን ለአደጋ የሚያጋልጥ እየሆነ ለአደጋ የተጋለጠውም ለስደትና ለመፈናቀል እየዳረገ ነው። አደራ የሚሰደዱትና የሚፈናቀሉት ዜጎች አደራ ለብቻቸው እንዳይተዉ ብለው በዚህ አጋጣሚም ለስደተኞና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አቅራቢ ለሆኑት አገሮች ምስጋናቸውን አቅርበው ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የሚዳርጉት ምክንያቶች መፍትሔ ማሰጠት ወሳኝ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ  አያይዘው፥

መልካም አስተዳደርና ግኑኝነት

ቅድስት መንበር ጉባኤው ያቀረበው እርሱም የመልካም አስተዳደር አሠራር በማበረታታት የመልካም አስተዳደር ተግባር ለማስፋፋትና ይኸንን ለማነቃቃት በአገሮች መካከል ግንኙነትና መቀራረብ እንዲበረታታ የጸጥታው የደህንነትና የትብብር ማኅበር አቢይ ድጋፍ ለማቅረብ የገባውን ቃል በማመስገን ይኽ ግኑኝነት ያንን በዓለምችን የሚታየው ኤኮኖኢያዊና ማኅበራዊ ተገልሎ ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት አቢይ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተስፋ እንዳላት በማብራራት ብፁዕ አቡነ ጋላገር ንግግራቸውን እንዳጠቃለሉ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.