2016-12-09 16:25:00

የውሉደ ክህነት ሕንጸት፥ ሰብአዊና መንፈሳዊ ብስለት ያማከለ


ያንን የዛሬ 46 ዓመት በፊት መሠረታዊ አመክንዮ በሚል ርእስ ሥር ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የውሉደ ክህነት ዙሪያ የሚመለከት ሰጥተዉት የነበረውን ሥልጣናዊ ምዕዳን በማደስና ወቅታዊው ሁነቶችን ግምት የሰጠ “Ratio fundamentalis institutionis sacerdotalis – መሠረታዊ አመክንዮ ለክህነታዊ ሕንጸት” በሚል ርእስ ሥር የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ያወጣው ስለ የካህናትና ሕንጸት ጉዳይ የሚዳስስ በክህነታዊ ሕንጸት ማእከላዊው መሠረተ ነገሩ በአጽንዖት ለይቶ የሚተነትን ሰነድ የቅዱሱ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል በኒያሚኖ ስተላ በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በክብረ በዓለ ጽንሰታ ለማያም (የማርያም አለ አዳም ሓጢኣት መጸነስ) ይፋ አድርጓል።

ብፁዕ ካርዲናል ስተላ ሰነዱን በማስደገፍ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓም. ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የሰነዱ ጽማሬ በጥልቀት ሲያቀርቡ፥

ሰነዱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስለ ካህናትና ክህነት ዙሪያ የሰጡት ምዕዳን እስትንፋስ ያደርገ ነው

ሰብአዊና መንፈሳዊ ልኬት በማመዛዘን ያዋሃደ ከዚህ ጋር የማሰብና የመመራመር እርሱም የአእምሮና የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሕንጸቶችን በማካተተ በደረጃና ግላዊ ጉዞ ላይ ያተኮረ ሥነ ምምህር ያጠቃለለ ሕንጸት የሚል ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚለያቸው መንፈሳዊነት ነቢያዊነት የተካነ ትምህርታቸው መሰረት ያደርገ ሰነድ ነው። የካህናት እንክብካቤ (ክትትል) እና ሕንጸት ቤተ ክርስቲያናዊ ገጽታ እንዳለው የሚያብራራ  ነው።

በሥነ ምርምር ፈተናዎችን በብቃት መወጣት ለብቻው በቂ አይደለም ስለዚህ ምሉእ ሕንጸት ወሳኝ ነው

ብፁዕ ካርዲናል ስተላ በማያያዝ፥ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ‘ሕዳሴ ከትውፊትና ባህል ፈጽሞ የተነጠለ አይደለም። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ሕዳሴ ትውፊትንና ባህልን ያሟላና በጥልቀት ትውፊቱና ባህሉን በጣምራ የሚያጤን ነው፡ በሰነዱ እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ Pastores dabo vobis - እረኞች እሰጣችኋለሁ’ በሚል ርእስ ሥር የለገሱት ድኅረ ሲዲኖዶስ ሓዋርያዊ ምዕዳን የሚያመለክተው ምሉእ ሕንጸት የሚለውን መሠረታዊ ነጥብ ደግሞ የሚያስተጋባ ነው። አዲሱ አመክንዮ አንዳንድ ባለፈው ሂደት እየተፈጠረ የመጣውን ራስሰርነትን ወዲያ ለመሻገር የሚደግፍ ነው። ስለዚህ ይኽ ተጋርጦ በሁሉም ገጽታና በጠቅላይ ጉዞ ላይ የጸና የመጨረሻው ምሉእ ግምገማ ለመስጠት የሚያስችል የምሉእ ሕንጸት ጉዞ ማቅረብ ያለው አስፈላጊነት ያስገነዝባል። ባጭሩ የተገባ መልካም እረኛ ለመሆን የሚሰጠው የሥ ምርምር ሕንጸት ፈተናዎችን በሚገባና ባጥጋቢነት ማለፍ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ መንፈሳዊ እና ግብረ ኖላዊ (ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ) ብስለት ጭምር ወሳኝነቱን አስረግጦ የሚሳስብ ነው።

ክህነታዊ ሕንጸት ሰብአዊነት መንፈሳዊነትና አስተዋይነትን ይጠይቃል

ብፁዕነታቸው የሰነዱን ቅዉም ሃሳብ በሚገባ ለመረዳት ያስችላሉ የሚልዋቸውን ሦስት ቁልፍ ቃላቶች ሲያስቀምጡ፡ በቅድሚያ ሰብአዊነት የሚለው ቃል በደረጃም ተወዳጅነት ሐቀኛንነት ቅንነት ውስጠ ነጻነት የተመዛዘነ የተረጋጋና የጸና ስሜት (የስሜት ብስለት) ሰላማዊ ግኑኝነት ያላቸው አለ ምንም ግትርነት አለ አስመሳይነትና ካለ ምንም የአቋራጭ ሽሽት ምርጫ ወንጌላውያን ምዕዳኖችን (ድክነት ተአዝዞ እና ንጽሕና) የሚኖሩ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መንፈሳዊነት የተሰኘው ቃል ነው፡ ክህነት ሃማኖታዊ ድርጅት ወይንም የተቀደሰ ነገር የሚያስተዳደር ሙያ ሳይሆን ከጌታ ጋር ፍቅር የያዘው ሐዋርያነትና ሕይወቱ አገልግሎቱ (ካህንነትን) ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ጥልቅ ግኑኝነት ላይ የተመሰረተ ነው የሚል መሆኑ አብራርተው ሦስተኛው ደግሞ አመዛዛኝነት የሚለውን ቃል መሆኑ ጠቅሰው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚያ በ36ኛው የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ ወቅት ለተጋባእያኑ በሰጡት ምዕዳን፥ “በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤቶች ግትርነት ወይንም ገታራ ኮስታራነት የሚያንጸባርቁ ሁኔታዎችንና ኩነቶችን ያለ መማዛዘን ወይንም ያለ ማስተዋል አዝማሚያ የመኖሩ ሂደት ያለ ይመስላል። ስለዚህ አርቆ አሳቢ አስተዋይ አመዛዛኝና አስተዋይ ካህን ማነጽ ያስፈልጋል በማለት የሰጡት ምዕዳን የሰነድ አንዱ ማእከላዊ ነጥብ ነው ብሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.