2016-12-09 14:19:00

ቅዱስነታቸው ክርስቲያኖች የማሪያምን አብነት ተከትለው ለእግዚኣብሄር ጥሪ “አዎንታዊ ምላሽ” ሊሰጡ ይገባል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 29/2009 ዓ.ም. እንደ አውሮፓዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር የተከበረውን ያለ አዳም ኋጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ድንግል ማሪያ አመታዊ በዓልን ለመታደም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ባደረጉት አስተምህሮ ክርስቲያኖች የማሪያምን አርሃያ ተከትለው ለእግዚኣብሄር ጥሪ “እንዳልከኝ ይሁንልህ” ማለት ይጠበቅባቸዋል ካሉ ቡኋላ ይህም  በኋጥያት ምክንያት ያረጀውን ማንነታችንን ቀይሮ እግዚኣብሔር በሕይወታችን አዲስ ታሪክ እንዲያከናውን እድሉን ይሰጠዋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ በተነበቡት ምንባባት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተጠቀሰውን የአዳም እና የሄዋን ውድቀትን በተመለከተ እና እንዲሁም በሉቃስ ወንጌል ላይ የተጠቀሰውን መልአኩ ገብርኤል ማሪያምን ያበሰረበት ታሪክ ላይ ተመርኩዘው ቃል እግዚኣብሔር ያሰሙ ሲሆን እነዚህ ሁለት ምንባባት በእግዚኣብሔር እና በሰዎች መካከል ለተፈጠረው ግንኙነት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ ክስተቶች እንደ ነበሩ ጠቅሰው በአጠቃላይም እነዚህ ምንባባት የመልካም እና የክፉ ነገሮች ሥር መሰረት ምን እንደ ሆነ እንድንረዳ ያስችሉናል ብለዋል።

በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተጠቀሰው ታሪክ የኋጥያት ምንጭ የሆነውን የመጀመሪያውን በእግዚኣብሔር ላይ የተፈጸመውን እቢተኝነት የሚያሳይ ታሪክ እንደ ነበረ በማውሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የሰው ልጅ እግዚኣብሔርን ሳይሆን ራሱን መመልከት በሚጀምርበት ወቅት ከእግዚኣብሔር ጋር የነበረው ሕብረት ይቋረጣል” ብለዋል።

“ይህም ኋጥያትን እንድንፈጽም ያደርገናል” በማለት ስብከትቻውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ነገር ግን እግዚኣብሔር የሰው ልጆች ላይ ስይጣን ይጫወትባቸው ዘንድ ብቻቸውን ሊተዋቸው አይፈልግም፣ በፍጥነት ፍለጋቸውን በመውጣት በፍርሃት የተደበቁትን ሁሉ “የት ነው ያለሄው?” በማለት እንደ ሚጠራቸው ገልጸዋል። ይህም እናት ወይም አባታ የጠፍውን ልጃቸውን እንደ ሚፈልጉት ዓይነት ፍለጋ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔርን በእዚህ ረገድ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፍለጋውን የሚያከናውነው በታላቅ ትዕግስት መሆኑ ብቻ ነው ብለዋል፣

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም የስብከታቸውን ትኩረት ያደረጉት በእለቱ በተነበበው የወንጌል ቃል ላይ ሲሆን ይህም “እግዚኣብሔር ሰው በመሆን በመካከላችን ለማደር እንደ ሚመጣ” በሚያወሳው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ ተመስርተው ይህም በማሪያም “አዎንታዊ ምላሽ” ምክንያት ተግባራዊ ወይም ፍጻሜን ማግኘቱን አውስተው በእዚህ አዎንታዊ ምላሽ ምክንያት ኢየሱስ በምድር ላይ መጥቶ የሰው ልጆችን ሕይወት እንዲካፈል አድርጎታል ካሉ ቡኋላ ይህንንም የተገበረው እንደ አንድ ወጣት ወይም ጎልማሳ ሰው ሆኖ በመከሰት ሳይሆን ነገር ግን የሰው ልጆች የሚያልፉበትን የሕይወት ሂደት በመከተል ጅማሬውን ያደረገው  በእናቱ በማሪያም ማሕጸን ውስጥ እንደ ነበረ አውስተዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ጸጋን የተሞላሽ” የሚለው ቃል በማሪያም ሕይወት ውስጥ ምንም ዓይነት ኋጥያት ወይም የክፋት ድባብ” እንደሌለ ያሳያል ካሉ ቡኋላ የማሪያም “እሽታ” ሙልኋት የነበረው እና ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ያልተቀመጠበት ቁጥብ ያልበረ እሽታ እንደ ነበረም አውስተዋል።

“ለእያንዳንዳችንም ቢሆን የማዳን ታሪካችን ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ለእግዚኣብሔር በምንገልጸው እሽታ ወይም እምቢታ ላይ መሰረቱን አድርጎ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ አንዴም እግዚኣብሔር ከእኛ የሚፈለገውን ነገር እንዳልተረዳን በማስመሰል አእምሮዋችን የሚለንን ነገር ብቻ እናከናውናለን ብለዋል። እንዳንዴም ትክክለኛ የሆን እንቢታን ለእግዚኣብሔር ሳንገልጽ ‘ዛሬ ይህንን የማድረግ አቅም የለኝም ነገ ግን አደርጋለሁኝ’ በማለት ብልሆች ለመሆን እንሞክራለን ያሉት ቅዱስነታቸው ‘ነገ የተሻለ ሰው እሆናለሁ፣ ነገ ጸልያለሁ፣ ነገ መልካም ነገር አከናውናለሁ” የሚሉትን እና የመሳሰሉትን በማለት ለእግዚኣብሔር በራችንን በመዝጋት ለሰይጣን እሽታችንን በመግለጽ ሰይጣን በሕይወታችን እንዲነግስ እድሉን እንከፍትለታለን ብለዋል።

“በተቃራኒው ግን ለእግዚኣብሔር ሙሉ እሽታን በምንገልጽበት ወቅት ሁሉ በሕይወታችን ውስጥ አዲስ ታሪክ እንዲፈጠር በር እንከፍታለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለእግዚኣብሔር የምንለው እያንዳንዱ እሽታ ለራሳችን እና ለሌሎችም አዲስ የመዳን ታሪክ እንዲጀመር እንድሉን ይከፍታል ካሉ ቡኋላ በእዚህ የስብከተ ገና ወቅት እግዚኣብሔር የእኛን እሽታ እየተጠባበቀ ይገኛል ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.