2016-12-07 16:37:00

ብፁዕ አቡነ ዩርኮቪች፥ ከዓለማዊነት ትስስር ወደ የተፈጥሮ ሃብት ተካፍሎ መኖር


እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ዓ.ም. ተደራሽ ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ተደራሽነቱን እውን ለማድረግ ውሳኔዎች ምኞቶች ቃል የተገቡት መልካም ሃሳቦችን ሁሉ ገቢራዊ ማድረግ ወሳኝ ነው፡ እቅዱ መልካም ስለ ሆነ አለ መልካም ፍላጎትና መልካም ጥረት ተደራሽ ይሆናል ብሎ ማሰቡ የዋህነት ነው። ስለዚህ ከቃል ወደ ተግባር መሸጋገር ይኖበታል። ይኸንን ያሉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኢቫን ዩርኮቪች የተባበሩት መንግሥታት የንድግና የልማት ጉዳይ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ሲሆን ዓለማዊ ትሥሥር የጋራና በሁሉም ዘንድ ተቀባነት ያለው ለሁሉም ብልጽግና በሚያስጨብጥ እማኔ ሊታሰብና ሊተገበር ይገባዋል። ነጻ ገበያ እየተረጋገጠና ባለፉት በመጨረሻዎች አሥር ዓመታት ውስጥ ዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ሁሉም አገሮች በዓለም አቀፍ ንግድ ተሳታፊያን እንዲሆኑ እድል ፈጥሯል። በዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት አባል ጭምር በመሆን በምርት አቅርቦት ተሳታፊያን እንዲሆን እድል ሰጥቷል። ሆኖም እ.ኤ.አ. በ 2008 እስከ 2009 ዓ.ም. በታየው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚና የቁጠባ ቀውስ ድኾች አገሮች እጅግ ተጎድተዋል በኢንዳስትሪ በበለጸጉት እገሮች ላይ ጭምር ችግር አስከትሏል። ሁኔታው በኑሮ ደረጃ ኢእኩልነትና ተበላላጭነት እያስፋፋ ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ዓለማዊ ትስስር የሚለው እግብር ላይ እየዋለ ያለው ርእየት ዳግም እኩልነትና የተፈጥሮ ሃብት ለሁሉም ማዳረስ በሚል ቁርጥ ፈቃድ ዳግም ካልተስተዋለና በዚህ ረገድ ካልተተገበረ ቀውሱ እየክፋ ይሄዳል። የሃብት ተካፋይነት ተቋዳሽነትን የሚዋስ እንዲሆን በሚገፋፋ እስቤ ሊጤን ይገባውል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒ ባጠናቀሩት ዘገባ ይጠቁማሉ።

እ.ኤ.አ. ድኅረ 2015 ዓ.ም. ተቀባይነት ያለው ባለ 17 ተደራሽ ግቦችን ያስቀመጠው የልማት እቅድ የዓለማችን ሂደት ከግል ጥቅም መሻትና ከግል ጥቅም በመንደርደር ፖለቲካ ኤኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳይ ከማንበብ እሽቅድድም ተላቆ ሁሉም ሕዝቦችና አገሮች ሊያሳትፍ በሚችል ለሁሉም ጥቅም ባጠቃላይ የግል ጥቅምና ማኅበራዊ ጥቅም አመዛዝኝ የሆነ ስልት መከተል ያስፈልጋል። የሚያገል ሳይሆን ማንም የማይነጥል ሁሉንም ለማካተት የሚያግዝ ስልት እግብር ላይ ሊውል ይገባዋል እንዳሉ የገለጡት ዘንጋሪኒ አያይዘው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና ዓለም አቀፍ ማኅበራት ድርጅቶች ሁሉ ቃል የሚገባባቸው መድረክ ከመሆን ተላቀው የተገባው ቃል እግብር ላይ የማዋል ውሳኔ የሚወሰድባቸው ግብራዊነትን የሚያፋጥኑ መሆን አለባቸው ስለዚህ ድኅረ 2015 እና እ.ኤ.አ. እስከ 2010 ዓ.ም. ይደረሳል ተብሎ የተወጠነው ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ በእውነቱ ተደራሽ እንዲሆን ከተፈለገ እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አጀንዳ የሚታወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባካሄደው ሦስተኛው ጉባኤ ያረቀቀው ዝክረ ነገር ተፈጻሚ ማድረግ ግድ ይሆናል። ስለዚህ የልማት እቅድ እጅግ ብዙ ናቸው ስለዚህ ዳግመ እቅዶች ከመዘርዘር ይልቅ ያሉት የልማት እቅዶች ወደ ተግባራዊነት መተርጐም ያስፈልጋል እንዳሉ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.