2016-11-30 13:27:00

ቅዱስነታቸው "ስለምሕረት ሲደረግ የነበረው አስተምህሮ ዛሬ ቢጠናቀቅም ምሕረት በቀጣይነ የሚፈጸም ተግባር ሊሆን ይገባል" አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ልማዳዊ በሆነው እና ዘወትር ርዕቡ እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ እንደ ሚሰጡ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬ እለት ማለትም በኅዳር 21/2009 ዓ.ም. ያስተላለፉ መልዕክት ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመትን አስመልክተው በተከታታይ ስያደርጉት የነበረው ሰባቱን አካለዊና ሰባቱን መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን የተመለከተ አስትምህሮ በዛሬ የመጨረሻዎችን ሁለቱን መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን ማለትም በሕይወት ላሉ ሰዎችና ከእዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ ሰዎች መጸለይ በሚሉት ጭብጦች ላይ ያጠነጠነ አስተምሕሮ ማድረጋቸው ተዘገበ።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እሕቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

“በዛሬው የትምሕረተ ክርስቶስ ትምህርታችን ምህረትን በተመለከተ ሳቀርብላችሁ የነበረው አስተምህሮ መደምደሚያ ነው። ምንም እንኳን ስለምሕረት ሲደረግ የነበረው አስተምህሮ ዛሬ ቢጠናቀቅም ነገር ግን ምሕረት በቀጣይነ የሚፈጸም ተግባር ሊሆን ይገባል። እግዚኣብሔርን ሰለሁሉም ነገር እያመሰገነው ይህንን ምሕረት በልባችን እንደ መጽናናት እና ማጽናኛ ጠብቀን ልናቆየው ይገባል”።

ይህ ዛሬ በቀጥይነት የምንሰማው ስድስተኛውና ሰባተኛው መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት የሆኑትን በሕይወት ላሉና ከእዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ ሰዎች መጸለይ የሚሉትን እንመለከታለን በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ መንገድ ነው በሕይወት ያሉትን እና በሞት የተለዩንን ወገኖቻችንን በመንፈስ ቅርብ መሆን የምንችለው ብለዋል። በሕይወት ለሚገኙ ሰዎች መጸለይ የሚለውን በምንመለከትበት ወቅት በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ ጉዳይ በመሆኑ በተለይም ደግሞ በዓለማችን በአንድ አንድ አከባቢ በጦርነት እየማቀቁ ለሚገኙ ሰዎች ጸሎት ማድረግ አስፈላጊነቱ የጎላ ነው በማለት አስተምህሮዋቸን የቀጡሉ ቅዱስነታቸው ቀን ከሌሊት በሚደርገው የቦንብ ድብደባ ንጹሐን ሰዎች ሳይቀሩ የአደጋው ሰላባ እየሆን ስለሚገኙ ለእነዚህ በፍርሃትና በሽብር ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ጸሎት ማድረግ አስፈላጊ ነው ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሰዎችን በጸሎት በምናስታውስበት ወቅት ሁሉ በሕይወት ከእኛ ጋር በነበሩበት ወቅት ጥለውልን ያለፉትን መልካም የሚባሉ ተግባራትን በማስታውስ ያንን መልካምነት እኝም እንድንላበስ ይረዳናል ብለው ስላሳዩን መልካም ፍቅርና ጓደኝነትም እግዚኣብሔርን የምናመሰግንበትን አጋጣሚ ይከፍታል ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያናችን በተለይም በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሰዎችን በጸሎቱዋ ታስባለች በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በስርዐት ቅዳሴ ወቅት ካህኑ “ጌታ ሆይ በእምነታቸው ጸንተው ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን አስብ፣ የዘለዓለም ረፍት ስጣቸው፣ የዘለዓለም ብርሃንን አብራላቸው” ብሎ እንደ ሚጸልይ አስታውሰው ይህም በጣም ቀላል የሚባል ማስታወሻ ነገር ግን በውስጡ ብዙ ትርጉም ሰጪ የሆኑ ቃላትን የያዘ ነው ምክንያቱም በሞት የተለዩ ውድ የሆኑ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በአደራ ለእግዚኣብሔር እንደ መስጠት ስለሚቆጠር ነው ብለዋል።

ስለእዚህም አሉ ቅዱስነታቸው በክርስትና ተስፋችን ታግዘን ከእርሱ ጋር በገነት እንዲያኖራቸው መጸለይ ያስፈልጋል ብለው በድጋሚም በሰው አእምሮ ለመረዳት በሚያስቸግረን የፍቅር ምስጢር ከእነርሱ ጋር ተመልሰን መገናኘት እንድንችል ምኞታችንን በመገልጽና ኢየሱስ  ሁላችንም ከሞት እንደ ምንነሳና ከእስርሱ ጋር ለዘላለም እንደ ምንኖር ተስፋ ስለሰጠን በእዚህ እውነተኛ ተስፋ ተማምነን ጸሎታችንን በሕይወት ላሉና ከእዚህ ዓለም በሞት ለተለዩን ሰዎች ሳንታክት ማቅረብ ይገባናል ካሉ ቡኋላ የእለቱን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.