2016-11-26 14:04:00

ቅዱስነታቸው የዘላለም ሞት ማለት የቅጣት ቦታ ሳይሆን ከእግዚኣብሔር መራቅ ነው አሉ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 16/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የዘላለም ፍርድ ከእግዚኣብሔር የምንርቅበት ሥፍራ እንጂ እግዚአብሔር እኛን የሚቀጣበት ቦታ አይደለም ስለዚህም ክርስቲያኖች አማላይ ከሆነው ከዲያቢሎስ ጋር በፍጹም መነጋገር የለባቸውም ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ ከዩሐንስ ራእይ በተነበበውና መልአኩ እባቡን እንዴት እንደ ያዘው፣ አስርቶም ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ከወረወረው ቡኋላ ዘግቶ መግብያውን እንዳሸገው በሚገልጸው ምንባብ ላይና በዓለም መጨረሻ ስለ ሚከሰቱ ነገሮች ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስይጣን እና ድያቢሎስ ወደ ጥልቁ ጉድጓድ ተወርውረዋል “ከአሁን ቡኋላ ሀገራትን በተሳሳተ ምንግድ እንዲሄዱ ማድረግ አይችልም” ምክንያቱም አማላይ የነበረው ሰይጣን ስለተደመሰሰ ነው ብለዋል።

“ሰይጣን አታላይ ነው፣ በተጨማሪም የውሸቶች ሁሉ አባት ነው፣ የውሸት ሁሉ ምንጭና ቀጣፊ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ‘ይህንን እጸበለስ ብትበላ እንደ እግዚኣብሔር ትሆናለህ’ በማለት እንድታምን ያደርግኋል በእዚህ አይነት መንገድ ይሸጥልኋል አንተም ትገዛዋለህ በመጨረሻም ያታልልኋል፣ ይሸውድኋልም ከእዚያም ሕይወትህ እንዲበላሽ ያደርጋል ብለዋል። “አባ ታዲያ እንዴት ነው በሰይጣን ከመሸወድ የምንድነው?” ብላችሁ ትጠይቁኝ ይሆናል መልሱም አንድ እና አንድ ነው፣ ኢየሱስ እንዳስተማረን ከሰይጣን ጋር እስከ መጨረሻ መነጋገር ማቆም ነው መልሱ ብለዋል። ኢየሱስ በሰይጣን በተፈተነበት ወቅት ምን እንዳደረገ ታውቃላችሁ? ወዲያውኑ ነው ያባረረው፣ ስሙ ማን እንደ ሆነ ብቻ ጠየቀ እንጂ ምንም ዓይነት ቃላት ከእርሱ ጋር አልተለዋወጠም” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንዳብራሩት ኢየሱስ በበረሃ በነበረበት ወቅት ራሱን ከሰይጣን ፈተና ያተከላከለው ለሰይጣኑ በእግዚኣብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ መልስ በመስጠትና ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስለዚህም ሕይወታችንን ለማበላሸት በመፈለጉ ምክንያት ወደ ጉድጓድ ከተወረወረው ከእዚህ ቀጣፊ ዲያብሎስ ጋር በፍጹም መነጋገር የለብንም ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደገለጹት የዩሐንስ ራእይ እግዚኣብሔር ለታላላቆችና ለታናናሾች “እንደየተግባራቸው እንደሚፈርድ” ያሳያል ካሉ ቡኋላ የተፈረደባቸውም ወደ እሳት ባሕር ይወረወራሉ ይህም ሁለተኛ ሞት ይሆና ማለት ነው ብለዋል።

“የዘላለም ፍርድ ማለት ቅጣት የሚደረግበት ስፋራ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን የሁለተኛው ሞት መገለጫ ነው እንጂ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት ያልገቡ ሰዎችና ወደ ጌታ ለመቀረብ ያልፈለጉ ሰዎች ብቻ ናቸው ካሉ ቡኋላ እንዲህ ዓይነቱ ሰዎች ከጌታ መንገድ በመራቅና በእርሱ ፊት ይመላለሱ የነበረ ነገር ግን ከእርሱ ለመራቅ አስበው የራሳቸው መንገድ መጓዝ የመረጡ ሰዎች ናቸው ያሉት ቅዱስነታቸው የዘላለም ቅጣት የሚመጣው ቀጣይነት ባለው መልኩ ራሳችንን ከእግዚኣብሔር በምናርቅበት ወቅት ነው ብለዋል።

ራሳችንን ከሚወደን እና ደስታን ከሚሰጠን ከእግዚኣብሔር በምናርቅበት ወቅት ሁሉ ወደ እሳትና ወደ ዘላለም ቅጣት እንወረወራለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ልባችንን በትህትና ለእግዚኣብሔር በምንከፍትበት ወቅት ሁሉ እኛም ደስተኞች እንሆናለን፣ እንድናለንም በኢየሱስ ይቅርታም ይደርገልናል ብለዋል።

“ተፋ ነው ልባችን በመክፈት ከኢየሱስ ጋር እንድንገናኝ የሚያደርገን” ቅዱስነታቸው ካሉ ቡኋላ የሚጥበቅብንም ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ነው፣ ይህም በጣም ቆንጆ ነገር ነው፣ እጅግ ደስ የሚል ነገርም ነው ካሉ ቡኋላ እርሱ የሚጠይቀን የዋህ እንድንሆን ብቻ ስለሆነ በየዋህነት ‘ጌታ ሆይ!’ ማለት ብቻ በቂ ነው እርሱም የቀረውን ነገር ሁሉ በራሱ ያከናውናል” ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.