2016-11-25 16:17:00

ብፁዕ ካርዲናል አማቶ፥ በመከባበር እሴት ይሸኝ እንጂ ቲዮሎጊያዊ ምጉት በጀ የሚባል ነው


ዮሴፍ ራትዚንገር በነዲክቶ 16ኛ የተሰየመው ማኅበር ያነቃቃው፥ “ስነ ፍጻሜ ትንተናና እይታ” በሚል ርእስ ሥር ያሰናዳው በጳጳሳዊ ቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ የተጀመረው ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የ2016 ዓ.ም. በዮሴፍ ራትዚንገር የሚጠራው የቲዮሎጊያ ኖበል ሽልማት ብቁ ተብለው ለ 2016 ዓ.ም. ለተሸላሚነት ለተመረጡት የቲዮሎጊያና የሊጡርጊያ ጉዳይ በሚመለከቱ አርእስቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍት ደራሲ የልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቲዮሎጊያ መምህር ከዛም ጳጳስ ብሎም ካዲናልና ር.ሊ.ጳ. ሆነው በሰጡት ሐዋያዊ አገልግሎትና ልሂቅ ከሆኑም በኋላ የለገሱት አስተምህሮዎች ስብከቶችን ያካተተ በጥልቅ እንደየ አርእስቱና ቲዮሎጊያዊ ዘርፉ አመካኝነት በመተተን ባንድ ተከታታይ መድብላዊ ስብስብነት ባለው ስልት እስካሁን ድረስ 20 መጻሕፍት የደረሱ ለንባብ ያስበቁና ገና እንደሚቀጥሉበ የሚነገርልቸው በተለይ ደግሞ የማእክላዊ ዘመን ቲዮሎጊያና ፍልስፍና ባላቸው ሊቅነት የደርስዋቸው የጥናት መጻሕፍቶች ዓቢይ ግምት በመስጠ ለሽልማት ዮሴፍ ራትዚንገር ለተመረጡት ለየኔታ አባ ኢኖስ ቢፊና በተሶሎንቄ መንበረ ጥበብ አሪስጦትል የቲዮሎጊያ ዘርፈ ትምህርት መምህር በሳሎኒቆ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መምህር የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመን ዮአኒስ ኩረምፐአስ በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንጻ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እጅ በመቀበል ስነ ሥርዓት የሚጠቃለል መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ..አ. ህዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅዱስ መስቀል ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ “ስነ ፍጻሜ ትንተናና እይታ” በሚል ርእስ ሥር የሚካሂደው ዓውደ ጥናት ቅዱሳንና ስነ ፍጻሚ በሚል ርእስ ሥር የቅዱሳን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ባስደመጡት ስልጣነ ትምህርት የተጀመሪ መሆኑ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፡ እንደሚታወሰውም ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ገና የኔታና ከዛም ጳጳስ እያሉ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጲጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመመረጣቸው ዓመታት በፊት ቀደም ብሎ በኅየንተነት ሐዋርያዊ ሥልጣን ያገለግሉበት በነበረው የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ባገለገሉበት ወቅት የቅርብ ተባባሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ዓውደ ጥናቱን ለመክፈት ባስደመጡት ንግግርም በዮሴፍ ራትዚንገር “ስነ ፍጻሜ ትንተናና እይታ” ምን ተመስሎው በጥልቅ ማብራራታቸው አስታውቋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.