2016-11-25 12:54:00

ቅዱስነታቸው ማፍያ ከአደንዛዢ እጽ ጥገኝነት ለመውጣት የሚታገሉ ሰዎችን ይገላል ማለታቸው ተገለጸ።


በቫቲካን በቅድስት መንበር የሳይንስ ማዕከል አስተባባሪነት ከኅዳር 14 እስከ 15/2009 ዓ.ም. ተካሄዶ በነበረው ጉባሄ ላይ ቅዱስነታቸው አስተላልፈውት የነበረው መልዕክት “አደንዛዢ እጽ፣ ችግሩና ለእዚህ ዓለማቀፍ ርዕሰ ጉዳይ መፍትሄ” በሚል አርዕስት  መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ቅዱስነታቸው  የአደንዛዥ እጽ ጥገኛ መሆን “የዘማናችን አዲሱ የባርነት ቀንበር ነው፣ የማሕበረሰባችን ቁስል” በመሆኑ በትምሕርት እና መልሶ ማገገሚያ ቦታዎችን በማቋቋም ልንዋጋው ያስፈልጋል ማለታቸው ተገለጸ።

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ቅዱስነታቸው አደንዛዢ እጽን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ገለጹት በእዚህ አደንዛዢ እጽ ወጥመድ ውስጥ የገቡ ተጠቂ ሰዎች “ነጻነታቸውን ተገፈዋል” ይህም “ልክ አዲስ የባርነት ስርዓት ውስጥ እንደ መግባት ይቆጠራል” ብለዋል።

የአደንዛዢ እጽ ጥገኝነት መነሻውን በተመለከተ በመልዕክታቸው አስተንትኖ የሰጡት ቅዱስነታቸው በርከት ያሉ መነሻዎች እንደ ሚኖሩት ገልጸው በተለይም ደግሞ “ወላጅ አልባነት፣ የማሕበረሰቡ ጫና፣ የአደንዣዢ እጽ አዘዋዋሪዎች ቅስቀሳና አዲስ ዓይነት ሕይወት ለመኖር ከመፈልግ የመነጨ” ሊሆን ይችላል ብለዋል።

ቢሆንም አሉ ቅዱስነታቸው ቢሆንም “የእዚህ የአደንዛዢ እጽ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገኛ የሆኑ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ለየት ያለ ታሪክ ይኖራቸዋል፣ ልናደምጣቸውም፣ ልንረዳቸው፣ ልንወዳቸውና ከተቻለም እንዲድኑ ወይም ከእዚህ እንዲነጹ ልናደርግ ይገባል” ካሉ ቡኋላ “በምንም ዓይነት ሁኔታ እንደ አንድ ቁስ ወይም ደግሞ የተሰበረና ግብስብስ እንደ ሆኑ አድርገን ልንፈርጃቸው እንደ ማይገባ ገልጸው በምትኩም ሁሉም የሰው ልጆችን ለመፈወስ ማንነታቸው ማክበር እና መብታቸውን መጠበቅ አስፈላጊ ነው ካሉ ቡኋላ ምክንያቱም የእግዚኣብሔር ልጆች በመሆናቸው ሰባዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል” ማለታቸው ተዘግቡኋል።

ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው እንደ ገለጹት “በእዚህ አላፊ በሆኑ ነገሮች ላይ በማትኮር ለአንድ አፍታ ደስታ እንድናገኝ በሚገፋፋን ዓለማችን  “ ብዙ ሰዎች የአደንዛዢ እጽ ጥገኞች መሆናቸው ብዙም አያስገርምም በማለት መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእዚህ ችግር ምንጭ አደንዛዢ እጹ በበቂ ሁኔታ መገኘቱና ተጠቃሚው ሰው ወይም ፈላጊው እየበዛ በመምጣቱ ዋነኛ ምክንያቶች እንደ ሆኑም ጠቅሰዋል።

የአደንዛዢ እጽ አቅርቦት “ለተደራጀ የወንጀል ቡድን አደኛውና አስፈላጊ ክፍል ነው” ስለዚህም ይህ የአቅርቦት መስመር ታድኖ መውደም ይኖርበታል ያሉት ቅዱስነታቸው በሁለተኛ ደርጃም የአደንዛዢ እጽ ተጠቃሚ ለሆኑ ሰዎች ትምህርት በመለገስና ማህበራዊ የሆኑ ዝግጅቶችን በማመቻቸትና በቤተሰብ ድጋፍ ከችግሮቻቸው እንዲላቀቁ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

“የተቀናጄ ሰባዊ ሕነጻ መስጠት በቀዳሚነት ሊመጣ የሚገባ ጉዳይ ነው” በማለት መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህም ሰዎች መውሰን እንድችሉ እንድል ስለሚሰጣቸው በመሆኑን መሆኑን ገልጸው ይህም ለራሳቸውና በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ያሉትን በውሳኔ አወሳሰድ ሂደት መርዳት ስለ ሚያስችላቸው በመሆኑ ነው ብለዋል። ይህም የሕነዛ ፕሮግራም በመርዕ ደረጃ ተጠቂ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ለምሳሌም ለልጆችና ለወጣቶች በመስጠት ይህንንም ፕሮግራም ወደ ወላጆችም እንዲደርስ በማድረግ የመከላከልና መልሶ የማቋቋም ተግባራትን በመሥራት ይህንን የአደንዛዢ እጽ ችግር መቋቋም ይቻላል ብለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው በእዚህ አሳሳቢ ችግር ውስጥ የሚገኙ ወንድምና እህቶቻችን የእግዚኣብሔር እርዳታ በሕይወታቸው እንዲታከልበት ተማጽነው መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.