2016-11-25 13:04:00

ቅዱስነታቸው ሙስና እግዚኣብሔርን እንደ መሳደብ ይቆጠራል "ገንዝብ አምላክ ነው" የሚል ስልጣኔ ይፈራርሳል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 15/2009 ዓ.ም. በቅድት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ሙሳን ገንዘብን እንደ ማምለክ ስለሚቆጠርና ሌሎችን የሚበዘብዝ ሴራ በመሆኑ እግዚኣብሔን እንደ መሳደብ ይቆጠራል ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ የተነበቡት ምንባባት ትኩረታቸውን በዓለም ፍጻሜ ስለሚከሰቱ ነገሮች፣ ስለመጨረሻ ፍርድና  ታማኝ አገልጋይ የሆኑ ሰዎችን እግዚኣብሔር እነርሱን እንደ ሚበጅ የሚገልጽ እንደ ነበር የታወቀ ሲሆን ቅዱስንታቸውም በእዚህ ዙሪያ ባጠነጠነ ስብከታቸው እንደ ገለጹት ታላቂቷ ባቢሎን የፈራረሰቺው በሙሳን መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ሙስና እግዚኣብሔርን እየተሳደቡ እንደ መኖር ይቆጠራል ብለው በአጽኖት በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ቃል ዓለማዊ ኑሮን ስሚገልጽ የባቢሎኖች ቋንቋ ነው ብለዋል። ሙስና አምላክ በሌለበት ቦታ አምላክን እንደ መሳደብ ይቆጠራል በማለት ስብከታቸውን የቅጠሉት ቅዱስነታቸው በዛ ስፍራ የሚኘው እንደ አምላክ የሚቆጠረው ገንዘብና በሌሎች ላይ የሚደረግ ብዝበዛ ነው ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ኋያላንን የሚያባብል ይህ ዓለማዊነት ፈራሽ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ልክ አሁን በዩሐንስ ራእይ (18) ሲነበብ እንደ ሰማነው ከንቱ፣ እብሪተኛና ክፉ የነበረችሁ ባቢሎን በፈራረሰችበት ወቅት  የመልአኩ የአሸናፊነት ድምጽ ተሰምቶ እንደ ነበረም አስታውሰዋል።

ብልሹ የነበረው ሥልጣኔ በመፈራረሱ ምክንያት መልአኩ ያበሰረውን የድል አብሳሪ ድምጽን በንጽጽር በማቅረብ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሌላም እግዚኣብሔርን የሚያመሰግኑ እጅግ ብዙ ሕዝብ “መዳን፣ ክብርና ኋያልነት የአምላካችን ነው!” እያሉ እግዚኣብሔርን ያመሰግኑ እንደ ነበር ግልጸው ይህም ኋጥያተኛ የሆኑ ነገር ግን ሙስኞች ያልሆኑ ሰዎች በሚድኑበት ወቅት የሚያሰሙት የወዳሴ ድምጽ መሆኑን በአጽኖት ገልጸዋል።

ኋጥያተኝ ሰው ምሕረት እንዴ መጠየቅ እንድሚገባው ያውቃል፣ ምንም እንኳን ቀላል ባይሆም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመዳን በመሻት አምላክን ያመልካል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሆነ ነገር አምላክን በምንጠይቅበት ወቅት በጸሎት እንጎብዛለን በዚያም ልክ አምላካን ማመስገን መማር ይኖርብናል ብለዋል። 

በመጨረሻ ቀን ይህንን በጥድፊያ መማር አስቸጋሪ በመሆኑ የተነሳ ይህንን አሁኑኑ መማር ይሳፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ቅዱስ ቁርባን በሚያርፍበት ሥፍራ ፊለፊት ላይ ሆነን በቀላል ቋንቋ “አንተ አምላክ ነህ፣ እኔ ደግሞ በአንተ የተወደድኩኝ ሚስኪን ልጅህ ነኝ” ማለት እንደ ሚገባ በአጽኖት ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታችውን በቀጠሉበት ወቅት በእለቱ በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ መልአኩ ለመጽሐፉ ጸሐፊ ለዩሐንስ ያሰማው ሦስተኛ ድምጽ እንዳለ ጠቁመው ይህም “ወደ በጉ የሰርግ ግብዣ የተጠሩ ሰዎች ሁሉ ብጹዕን ናቸው” ብሎት እንደ ነበረ ጠቅሰው የጌታ ጥሪ የለቅሶ ጥሪ ሳይሆን በየዋህነት እና በሎህሳስ ለልባችን ነው የሚናገረው ካሉ ቡኋላ ይህም ጌታ ለኤሊያስ በተገለጸበት ጊዜ አድርጎ እንደነበረው ዓይነት መሆኑን ገልጸው እግዚኣብሔር በሚናገርበት ወቅት ሁሉ በእዚህ መንግደ ነው ለልባችን የሚናገረው፣ ልክ ትንፋሽ በሚመስል ድምጽ ነው የሚናገረው ብለዋል።

ወደ ሰርጉ ድግስ የተደረገው ጥሪ ምሳሌ እንደ ኢየሱስ አገላለጽ የደኅንነታችን ጥሪ ምሳሌ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ጥሪ ክፉ፣ በጎ፣ ዓይነ ስውሮችን፣ መስማት የተሳናቸውንና የአካል ጉዳተኞችን ሁሉ የሚያጠቃልል ጥሪ መሆኑን አውስተው ሁላችንም ብንሆን “እኔ ኋጥያተኛ ነኝ፣ እግዚኣብሔር ያድነኛል” ለማለት የሚያስችል በቂ የሆነ ትህትና በልባችን ያለን ኋጥያተኞች ነን ብለዋል።

በእለቱ የተነበበው የወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ሁሉ መሆን በሚጀምርበት ጊዜ” (ሉቃስ 21. 20-28) የሚለውን በመጥቀስ እብሪታችንና ከንቱነታችንም ይፈራርሳል ስለሆነም “ቀና ብላችሁ ወደ ላይ ተመልከቱ ምክንያቱም ደኅንነታችሁ ቀርቡኋልና” በማለት ከወንጌሉ ጠቅሰው እግዚኣብሔር ያዛን ፀጋ እንዲሰጠን ተማጽነው ራሳችንን ለዛ እንድናዘጋጅና “ኋጥያተኞች የነበራችሁ ነገር ግን ታማኝም የሆናችሁ እናንተ ታማኝ አገልጋዮቼ ወደ እኔ ኑ የጌታን የሰርግ ግብዣም ኑና ታደሙ” የሚለውን ድምጽ መስማት እንድንችል ጸጋውን ይሰጠን ዘንድ መማጸን ይገባል ካሉ ቡኋል ስብከታቸውን አጠቃለዋል።  

 








All the contents on this site are copyrighted ©.