2016-11-25 16:02:00

ቅዱስ አባታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዘጓዳሉፐ ክብር የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን በላቲን ሥርዓተ ግጻዌ ዓመታዊ በዓል የመላ ላቲን አመሪካና ፊሊፒንስ ቅድስት ጠባቂ ቅድስት ማርያም ዘጓዳሉፐ የሚከበር ሲሆን። በዚህ በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ዓመት ጀምረው ይኸንን በዓል ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ ሲሰሩ በተከታታይ ሦስተኛ ጊዝያቸው ሲሆን። እንደ የመንፈሳዊ ሊጡርጊያዊ ስነ ሥርዓት መርሓ ግብር መሠረትም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ልክ አምስት ሰዓት ከሩብ የሁሉም የላቲን አመሪካ አገሮች ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ወጣት መንፈሳውያን ነጋዴን ዑደት በመፈጸም ሰንደቅ አለማዎችን በመንበረ ታቦቱ ፊት ያስቀምጣሉ፡ በኢጣሊያ የሚኖሩ የላቲን አመሪካ ተወላጅ ዜጎችና የፊሊፒንስ ዜጎች ምእመናን እንዲሁም በሮማ የሚገኙት የላቲን አመሪካና የፊሊፒንስ ውሉደ ክህነት አባላት ገዳማውያንና ልኡካነ መንግስታት ብሎም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅርብ ተባባሪዎች አበይት ሐዋርያዊ ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት ያሳተፈ የመቁጸሪያ ጸሎት ይደገማል።

ልክ 6 ሰዓት ላይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያንን ጥንታዊው ለቅድስት ድንግል ማርያም ዘጓዳሉፐ የሚዘየመው በናሁአትልና በኒቻን ሞፖሁዋ ቋንቋ የተደረሱት ያንን የቅድስት ድንግል ማርያም ግልጸት የታደለው በመክሲኮ ኢንዶስ ተብሎ ለሚጠራው ዘውገ አባል ቅዱስ ኹዋን ዴየጎ ታሪክ የሚያወሳና ስለ ግልጸቱ የሚያወሱ በሌሎች በላቲን አመሪካ ጥንታውያን ቋንቋዎች በሆኑት በከችዋ በማፑቸና ጉዋራኒ የተደረሱት መንፈሳውያን መዝሙሮች በላቲን አመሪካ በየሙዚቃ መምህር ኤድዋርዶ ኖትሪካ የሚመራው መንፍሳዊ ዘማርያንና እንዲሁም በቤተ ጸሎት ሲስቲና ጳጳሳዊ የመዘምራን ቡድን በጣምራዊ ውህደት በሚያቀርቡት መንፈሳዊ መዝሙሮች የተሸኘ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.