2016-11-24 12:52:00

ቅዱስነታቸው ጥርጣሬ እምነታችን እንዲያድግ ከረዳ አዎንታዊ ግጽታ አለው ማለት ነው ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመትን አስመልክተው በተከታታይ ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ሊተገብሩትና እስከ የሕይወት ፋጻሜያቸው ድረስ በልባቸው ታትሞ መቅረት ይኖርበታል ያሉትን ሰባቱን አካላዊ ወይም ሥጋዊ እና ሰባቱ መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት ላይ ትኩረት አድርገው ማስተማራቸው ይታወቃል። ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመቱ በይፋ በኅዳር 11/2009 በተዘጋበት ወቅት ቅዱስነታቸው አጽኖት ሰጥተው “ይህንን ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በር ዛሬ በይፋ ቢዘጋም የእግዚኣብሔር የምሕረት በር ግን ሁሌም ክፍት ሆኖ እንደ ሚቀጥል” አስስበው እኛም በዚህ ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት የጀመረነውን መልካም ተግባራት ቀጣይነት ባለው መልኩ መተግብር ይገባናል ብለው ማሳሰባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በማሰብ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 14/2009 አድርገውት የነበረው  የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ከሰባቱ መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት መኋከል በሁለቱ ላይ ማለትም በጥርጣሬ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን መምከርና ማስተማር በሚሉት ሁለት ጭብጦች ዙሪያ እንደ ነበረም ታውቁዋል።

እነዚህ ሁለቱ መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት በግለሰብ ደረጃ ወይም በተቀናጀ ሁኔታ ሊተገበሩ እንደሚችሉ ያስታወቁት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ያልተማሩ ሰዎችን ማስተማር የሚለው በተቀናጀ መልኩ በተቋማት ደረጃ ከዚህ ቀደም ከታሪክ እንደምንረዳው ብዙ ቅዱሳን ወንዶች እና ሴቶች ተግብረውት በነበረበት መልኩ ማከናውን እንደሚቻል ጠቁመዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም እንደ ገለጹት የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላትን በማጠናከር ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና ምስጠት ተማሪዎች እውቀትንና የክርስትናን እሴቶችንም ጠብቀው እንዲያድጉ ማድረግ እንደ ሚገባም ጨምረው ገልጸኋል።

በጥርጣሬ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች መምከር የሚለው ብዙን ጊዜ የጭንቅላት ሥራን የሚጠይቅ አይደለም ነገር ግን “የጭንቀት ምንጮች የሆኑትን በመረጋጋት እጦት የሚሰቃዩ ሰዎችን፣ መከራ በሚያስከትለው ፍርሃትና ጥርጣሬ ምክንያት የሚሰቃዩ ሰዎችን መምከር ነው” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ የምሕረት ተግባር ከጥርጣሬ የመነጨ መከራ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት ያለመ በመሆኑ “የፍቅር መግለጫ ነው” ብለዋል።

አንዳንዴ አሉ ቅዱስነታቸው ሁላችንም ብንሆን ጥርጣሬ ይገባናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም እምነታችንን እንድናጠናክር የሚረዳን ከሆነ አዎንታዊ ገጽታ አለው ካሉ ቡኋላ ነገር ግን ማንኛው አይነት ጥርጣሬን መወጣት መቻል ይኖርብናል ብለዋል። ይህንንም በትምህርተ ክርስቶስ ላይ ተመስርተንና የታወጀልንን እምነታችንን እለት በእለት በኑሮዋችን በመተግበርና እመነታችንን በሙልኋት በመኖር መወጣት እንችላለን ብለዋል።

“እምነታችን እንደ አንድ ረቂቅ ጽንሰ ሐሳብ በመሆን ብዙ ጥርጣሬን የሚፈጥር ነገር አይደልም” ያሉት ቅዱስነታቸው “ነገር ግን እምነታችንን የሕይወታችን መሰረት እንዳርገዋለን፣ ወንድማቻችን በተለይም ደግሞ በጣም የተቸገሩትን  ተጨባጭ  በሆነ መልኩ በመርዳት” መወጣት እንችላለን ካሉ ቡኋላ “ብዙ ጥርጣሬዎቻችን የሚጥፉት እግዚኣብሔር በውስጣችን በመኖሩና በወንጌል እውነተኛ ፍቅር ላይ በመመስረት፣ ለራሳችን ጥቅም ብቻ ብለን ሳይሆን በውስጣችን ባለው በእርሱ አማካይነት ያለንን ከሌሎች ጋር እንድንካፈል ስለሚያደርገን ነው ብለዋል።

እነዚህ ሁለት መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት የሕይወታችን አንዱ ክፍል ሲሆኑ ይገባል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እያንዳንዳችን በሕይወታችን እነዚህን ለመኖር መስዋዕትነት መክፈል ይገባናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እነዚህን በተግባር ለማዋል ያስችለን ዘንድ እግዚኣብሔር በቃሉ እንደ ሚለን የእርሱ ታላቅ ሚስጢር የተገለጸው ለጠቢባብ ሳይሆን ነገር ግን ለትናንሾች ነው እንዳለው ሁሉ ማንኛውንም ጥለቀት ያለውን አስተምህሮ በምናስተላልፍበት ወቅት እርግጠኛነትን ለሰዎች እናቀርባለን፣ ይህም ከጥርጣሬያችን ነጻ ያደርገናል ምክንያቱም በእግዚኣብሔር ፍቅር የተወደድን በመሆኑ ነው” ብለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.