2016-11-23 16:47:00

የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ መልእክት፥ “Misericordia et Misera-ምሕረትና አሳር”


እ.ኤ.አ. ባለፈው ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ታውጆ በይፋ ተጀምሮ እ.ኤ.አ. ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት መጽሐፈ ግጻዌ ዓመታዊ በዓል ክርስቶስ ዘንጉሥ ዕለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተጠናቀቀው ልዩ የምሕረት ዓመት በማስመልከት “Misericordia et Misera-ምሕረትና አሳር” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ መልእክት እ.ኤ.አ. ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ በቅቷል።

ሐዋሪያው መልእክቱ ሁሉም ካህናት ጽንስ የማስወረድ ሐጢኣት የመፍታት ሥልጣን አላቸው የሚል፡ የምሕረት ልኡካን ቀጣይ አገልግሎት በማስከተል እንዲሁ በሦስተኛ ደረጃ በተለያየ ምክንያት በቅዱስ ፒዮስ አስረኛ የወንድምነት ማኅበረሰብ ካህናት የሚሰጠው ምስጢረ ንስሐ ቅቡል የሚልና በመጨረሻም ዓለም አቀፍ የድኾች ቀን ቅዋሜ በተሰኙት አራት መሠረታውያን ሓሳብ ላይ ያተኰረ መሆኑ ሐዋርያዊ መልእክቱን ለንባብ ለማብቃት በተሰጠው መግለጫ ተብራቷል።

የሐዋርይዊ መልእክቱን ጽማሬ

የኣሳርና የምሕረት ግንኙነት

ቅዱስ አባታችን በዮሐንስ ወንጌል ምዕ 8 ከቁጥር 1-11 ዘንድ ተመልክቶ የሚገኘው ኢየሱስ ከአመንዝራዪቱ ሴት ጋር መገናኘት የሚያወሳው ታሪክ በተለይ ደግሞ ይኽ ግኑኝነት የምሕረት ዓመት ምስል እንዲሆን ቅዱስ አጐስጢኖስ ይኸንን ወንጌላዊው መልእክት በአሳርና በምሕረት መካከል ያለ ግኑኝነት ብሎ የሰጠው ስያሜ የሐርያዊው መልእክት ዋና ርእስ እና መሪ ሓሳብ በማድረግ “በዚህ ወንጌላዊ ቃል ዘንድ የሐጢአትና የፍርድ መገናኘት ሳይሆን የአንዲት ሐጢአተኛ ሴት (ጠፍታ የነበረች ሴት) መገኘት የሚያበክር መሆኑ በተለያየ መልኩ ይተነትኑታል።

ኢየሱስ የሙሴአዊ ሕግጋት ማእከል ፍቅር እንዲሆን ያደጋል

ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በኢየሱስ ፊት አንዲት በዝሙት የተያዘችውን ሴት በማምጣት “መምህር ሆይ ይቺን ሴት ስታመነዝር አግኝተን ያዝናት እንደዚችም ያለቸው በድንጋይ ትወገርም ዘንድ ሙሴ በኦሪት አዘዘን እንድግዲህ አንተ ስለ እርስዋ ምት ትላለህ? በማለት አድቢና ተንኰለኛ ጥያቄ ያቀርቡለታል፡ ኢየሱስ ግን የዚያ የሙሴ ሕግ ትኵረቱና ዓላማው ወደ ሚገልጠው አናስር በመመለስ የሕግ ማእከል ፍርድ ሳይሆን እግዚአብሔር ከሁሉም በላይ ያንን በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለውን ህቡእ ፍላጎቱን ከሁሉም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው በማስተዋል ልብን የሚያነብ መሆኑ የሚገልጥ ህሳብ ነው የሚያማክለው። ኢየሱስም እንደዚሁ ያችን በዝሙት የተከሰሰችውን ሴት ዓይን አይንዋን እያየ ልቧን አንቦቦ ያንን ሌሎች ሊያስተውሉት የተሳናቸውን በውስጧ ያለው የምሕረት የነጻነት ጥልቅ ፍላጎቷን ያስተውላል። ምንም’ኳ የሐጢአቷ ጫና ያለባት ቢሆንም ከዚህ ሰገር ትመለከትና ያንን ትኖረው የነበረውን ሕይወቷ የሚጻረር (የተለወጠ) አዲስ ሕይወት ለመኖር በሚያነቃቃት ፍቅር ታወደች፡

የሕግ ቀዳሜ እሴት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ በደረሱት ሐዋርያዊ መልእክት እግዚአብሔር ያ እንደተሳሳተ ታምኖ ተጸጽቶ በአዲስ መንፈስ ሕይወቱን አንድ ብሎ ለመጀመር ለሚሻና በእርሱ ለመታቀፍ ለሚመለስ ሁሉ የሚከለክል ምንም ዓይነት ሕግ የለም። በሕግ ላይ ብቻ መጽናት እምነትንና መለኮታዊ ምሕረትን ማርከስ ይኾናል። የአንድ ሕግ ቀዳሚ ክብሩ ምን መሆኑ በገላቲያ ምዕ, 3,24 “… በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶ የሚያደርስ ሞግዚታችን (ኣስተማሪ) ሆነ” እንዲሁም በአንደኛይቱ ጢሞቲርዎስ ምዕ. 1,5 “ …  የትእዛዝ ዓላማ ግን ከንጹሕ ልብ ከበጎ ኅሊና እንዲሁም ከእውነተኛ አምነት የሚገኝ ፍቅር ነው” በሚል ሃሳብ ተምልክቶ ይገኛል። ስለዚህ ክርስቲያን (በክርስቶ ያለ)፥ “… የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶ ኢየሱስ ከኀጢአና ከሞት ሕግ ነጻ የወጣ ነው (ሮሜ. 8,2) ክርስቲያን ይኸንን ወንጌላዊ ሕዳሴ ለመኖር የተጠራ ነው። ምንም’ኳ በሕግ ላይ የጸና ፍትሓዊነት ጎልቶ እንዲታይ ቢፈለግም በዚያ ከመለኮታዊ ጸጋ በሚመነጨው ኃይል ላይ መታመን ያስፈልጋል።

ለእግዚአብሔር ምሕረት ልይ ቅድመ ሁነት ለማኖር የሚቻለው ማንም የለም

ከመካከላችን በእግዚአብሔር መሕረት ፊት ቅድመ ሁነት የሚያኖር አንድም የለም። ምሕረቱ የዚያ ቅድመ ሁነት የማያኖር የሰማያዊው አባት ነጻ ተግባር ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር በሙሉ ነጻነት በነፍሰ ወከፍ ሰው ሕይወት ዘንድ ለመግባት ያለው ፍቃዱ በተቃዋሚነት ለመግጠም የማይቻል ብቻ ሳይሆን የሚሆንም አይደለም፡ አይቻለንም ክህሎቱም የለንም። የሚምር የሚለውጥ ተጨባጭ ምሕረት የእግዚአብሔር የፍቅር ተግባር ነው። በዚህ በሥነ እደ ጥበብ (technology) የበላይነት ሥር በሚገኝ ዓለም የተለያዩ ቀቢጸ ተስፋ የሚያመነጩ ትካዜ የሚባዛበት ሆኗል። ስለዚህ ያንን አፍታዊ ደስታ ቃል የሚገባልንን ሰው ሠራሽ ገነት የሚያቀርብ ምትሓት የሚገስጽ የእውነተኛ ተስፋና ደስታ መስካሪያን ያስፈልጋሉ።

ለመላ አለም የፈሰሰ ምሕረት

የተትረፈረፈ ጸጋ የታደልንበት ያንን የጌታ ፈዋሹ ፍቅሩና ምሕረቱ ወደ መላ ዓለም ያፈሰሰበት መልካም አየር የሰረጸበት በጋለ ስሜት የተኖረበት ዓመት ማሳለፋችን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሐዋርያው መልእክታቸው ገልጠው፡ አሁን የሚያስፈልገው ታዲያ ያንን የድሕነት ወንጌል ወደ ሁሉም ማድረስና ያንን የምንከተለው አዲስ ዱካ ለሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስ ታዛዥ በመሆን መንገዱን መከተል ነው። በመሥዋዕተ ቅዳሴና በቃለ እግዚአብሔር ሊጡርጊያዊ ሂደት የምሕረት ማእከልነት እንዲስተዋል የሚያደርግ መርሐ ግብር በየሊጡርጊያዊ ዓመት የእግዚአብሔር ቃል በጥልቀት የሚጠናበት እሁድ እንዲለይ በማሳሰብ ኃላፊነቱንም ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት መስጠታቸው አስታውቋል።

ምስጢረ ንስኀ ሠሪ ካህን ለመማር የሚቀበል ግልጽነትና የዋህነ የተካነ

ቅዱስ አባታችን በአስታራቂው ቅዱስ ምስጢር ላይ በማተኰር የዕርቅ ምስጢር በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ያለው ማእከልነት በማሳሰብ ይኽ ደግሞ ዳምግ ልጆቹ የሚያደርገን ጸጋ ሊጸግወን በሚመጣው አብ እቅፍ ውስጥ እንዳለን ሊሰማን የሚያደርግ ምስጢር ነው ሲሉ አብራርተው፡ ካህን የሐጢአት ከበድ ግድ ሳይለው በማስተናገድ የአብ የዋህነት መስካሪ እንዲሆንና ስለ ተፈጸመው ሐጢአት የሚናዘዘውን ሰው እንዲያስተነትን የሚያግዝ የግብረ ገብ ትእዛዞችን በግልጽነ የሚያቀርብ ምእመናንን በጸጸት ጎዞ ላይ በመሸኘት በትእግስት በመመልከት የእያንዳንዱ ተናዣዥ ጉዳይ የሚያመዛዝን አስተዋይና አርቆ የሚመለከት የአብ ምሕረት በማቅረቡ ረገድ ለጋስ እንዲሆን አደራ ብለው፡ ልክ እንደ ኢየሱስ በዚያች አመንዝራዪቷ ፊት ከኵነኔና ሞት ሊያድናት ጽሞና እንደመረጠ ሁሉ ካህን እንደ እርሱ የነፍስ ወከፍ ሐጢአተኛ መጸጸትን ባጠቃላይ ስብአዊ ሁነትብ የሚመለከት ይሁን፡ እርሱም ሰው ነው። ሐጢአተኛ ቢሆንም የምሕረት መሣሪያ መሆኑ አስተውሎ በመናዛዣ ሥፍራ ለጋስ ርህሩህ ልብ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል። ስለዚህ የንስሓ ምስጢር በሙላት አለ ምንም ፈረቃ ጌታን በመኖር በዚሁ አገግሎት አለ ገደብ የዕርቅ ምስጢር በማክበር ረገድ ተግቶ እንዲገኝ የተጠራ ነው ይላሉ።

አገልግሎት የሚከተሉ የምሕረት ልኡካን

በዚህ ልዩ የምሕረት ዓመት ቤተ ክርስቲያን በምሕረት ልኡካን በኩል የምሕረት ዓመት እንደ ተጨባጭ የምሕረት ጸጋ በቀጣይነት ያለው ኅያውና ፍቱን መሆኑ ከዚያ ልዩ የምሕረት ዓመት ማዶ የሚዘልቅ ጸጋዊ ተመክሮ አረጋግጣልናለች። ስለዚህ የዚህ እጹብ ድንቅ የሆነውን የምሕረት ተልእኮ እንድንኖር የሚያስችል መንገድ አስተውላ በመለየት በዚያ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል በሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በኩል በሊጡርጊያው ዓመት የዚህ ቀጣይ ጸጋ የሚስተዋልበት የሚስተነተንበ ቀን እንዲለይ ሐላፊነት ሰጥቷል።

ሁሉም ካህናት ጽንስ የማስወረድ ሐጢኣት የሚፈቱ

በእርቅ (ንስሐ)ና በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ሳንካ ሊያቆም የሚችል አንድም የለም የጌታ ምሕረት የሚገድብ ማንም የለም። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ሓሳብ መሠረት በማድረግ ሁሉም ካህናት ጽንስ የማስወረድ ሐጢአት የመፍታት ስልጣን አላቸው በማለት በምሕረት ዓመት ሰጥተዉት የነበረውን ስልጣን ቀጣይ ይሁን ብለው ይኽ ሲባል ግን በእርግጥ ጽንስ ማስወረድ የንጹሓን ህይወት የሚቀጭ በመሆኑ ትልቅ ሓጢአት አይደለም ለማለት አለ መሆኑ አበክረው ሆኖም በተመሳሳይ መልኩ በልቡ የተጸጸተ ከጌታ ጋር ለመታረቅ ለሚሻ የእግዚአብሔር ምሕረት እንዳይደርስ የሚያደርግ ምንም አይነት ሐጢአት አይኖርም እንላለን።

የቅዱስ ፒዮስ አስረኛ ወንድምነት ማኅበረሰብ የሚሠሩት ምስጢረ ንስሐ ቅቡል ነው

ያንን ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የምታተኵርበት አሃድነት በማስተዋልና በእነዚያ የቅዱስ ፒዮስ አስረኛ የወንድምነት ማኅበርነት ካህናት ባላቸው መልካም ፍቃድ በመታመን በተለያየ ምክንያት በዚህ ማኅበረሰብ ካህናት በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴና በሚሠሩት ምስጢረ ንስሐ የምሕረት ጸጋ የሚቀበሉት ምእመናን የሚሰጣቸው ስርየተ ሐጢአት ቅቡል መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሐርያዊ መልእክታቸው ዘነድ አስምረውበታል።

በችግር ላይ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን

ቅዱስ አባታችን በዚህ ሐዋርያዊ መልእክታቸው አማካኝነት ሃሳባቸው ወደ እዚያች በችግር ላይ ወደ ምትገኘው ቤተሰብ በማቅናት ማንኛውም ሰብአዊ ችግር ሁሉ በዚያ በማይታክተው በእግዚአብሔር ፍቅር እንዲስተዋልና እንዲሸኝ አደራ ብለው ካህናት ማንም እንዳይነጠል ለብቻው እንዳይተው በማንኛውም ዓይነት ችግር ውስጥም ይገኝ በምሕረት ተግባር ሕዝበ እግዚአብሔር ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ጥንቁቅ አርቆ አሳቢ መንፈሳዊነት አማካኝነት እንዲያስተዋል ያሳስባሉ።

ዓለም አቀፍ የድኾች ቀን

ልዩ የምሕረት ዓመት ተጠናቋል ቅዱስ በርም ተዘግቷል። ይሁን እንጂ የልባችን የምሕረት ቅዱስ በር ክፍት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በፊታችን ዝቅ ብሎ ሊመግበን ይገኛል (ሆሴዕ 11,4) ከዚህ የምንማረውም እኛም በተራችን በወንድሞቻችን በተለይ ደግሞ በድኽነትና በስቃይ ውስጥ በሚገኙት ፊት ዝቅ ማለትን ነው። ድኾችን መርሳት አይገባንም። ይኸንን መሠረት በማድረግም ቅዱስ አባታችን በላቲን ባሕረ ሓሳብ በተራው የሊጡርጊያ ሰላሳ ሦስተኛው እሁድ ዓለም አቀፍ የድኾች ቀን ተብሎ እንዲታሰብ ወስኗል። “…ሰውነቱ በቁስል የተወረረ አልአዛር…” (ሉቃ. ምዕ 16, 19-21) በቤቶቻችን ደጃፍ እስካለ ድረስ በዓለም ፍትህም ይሁን ማኅበራዊ ሰላም እውን ይሆናል ብሎ ማሰቡ የዋህነት ነው።

ባህላዊ አብዮት በገንቢ የፈጠራ ክህሎት የተሸኘ ምሕረት አማካኝነት

ቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊው መልእክታቸውን፥ ጊዜው በገንቢ የፈጠራ ክህሎት የተሸኘ ምሕረት አስፈላጊነት አለው የሚል ነው። ይኸንን በተራና ባልተወሳሰበ በተጨባጩ ዕለታዊው ሕይወታችን የሰናይና የየዋህነት ምልክት አማኣኝንት ገዛ እራሳቸውን የመከላከል አቅምና ብቃት የሌላቸው በብቸኝነትት ሕይወት ለተጠቁት ለተገፉት ለገዛ እራሳቸው ለተተዉት ሕይወት ለመስጠት የሚያስችል በገንቢ የፈጠራ ክህሎት የሚሸኝ ምሕረት ያማከለ የባህል አብዮት ማረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት በማሳሰብ ይደመድማሉ።    








All the contents on this site are copyrighted ©.