2016-11-21 16:29:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የውይይት ባህል ነቢይ


የዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የቅዱስ ዓመት መዝጊያ እ.ኤ.አ. ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ብሔራዊ የሰላምና የዕርቅ የጸሎት ቀን እንዲሆን በሰጡት ውሳኔ መሠረት በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ያንን የአገሪቱ ሕዝብ የተጋረጠበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አለ መረጋጋት ምክንያት ተከስቶ ያለው አስጊ ሁነት እንዲቀረፍ ሁሉም ሰላምን በመሻት ሂደት እንዲተጋና እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲሰጥ ከሚያደርገው ጸሎት ጋር የሚዋሃድ ቃልና ተግባር እንዲኖር ማሳሰቧ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳብሪና ስፓኞሊ አስታወቁ።

በዴሞክራሲያዊት ረፓሊክ ኮንጎ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ በቋፍ ላይ ያለ ከመሆኑም ባሻገር የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ጆሰፍ ካቢላ ዳግም በሚካሄደው የርእሰ ብሔር ምርጫ በእጩነት እንደሚቀርቡ በማሳወቃቸው በአገሪቱ ያለው ስጋት እጅግ እንዲባባስ እያደረገ ነው። ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች የርእሰ ብሔሩ ፍላጎት በመቃወም እምቢተኝነንት እያስተጋቡ ሲሆን፡ ገሚሱ የተቃዋሚ ኃይሎች ከርእሰ ብሔሩ ጋር ቅንጅት በመፍጠር ብሔራዊ የአገር አንድነት መንግሥት እንዲመሠረት የሚል አካሄድ የሚከተሉ መሆናቸው አፍሪካ ለተሰየመው መጽሔት ጋዜጠኛ ኤሪኮ ካዛለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለምልልስ ገልጠው፡ አገሪቱን ከሩዋንዳ ጋር በሚያዋስነው የምስራቃዊ የኪቩ ክልል አለ መረጋጋት ያለ ከመሆኑም ባሻገር ያለው አለ መረጋጋት እልባታ እንዲያገኝ አገራዊና ፖለቲካዊ እርቅ እንዲጨበጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ወሳኝ መሆኑ ምልክት ነው፡ የአንዲት አገር ሰላም የሚረጋገጠው በጦር መሣሪያ ሳይሆን የሕዝብ ፍላጎት በማክበር ነው፡ ስለዚህ ሁሉም የፖለቲካ አካላት ይኸንን ማእከል በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ማረጋግጥ ብቸኛ መትሔ መሆኑ ታምነው ስልጣን ሳይሆን ሕዝብ ማስቀደም ይገባቿል ብሏል።

ምስራቃዊው የዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ክልል በተፈጥሮ ሃብት የታደለ በመሆኑ ጎረቤት አገሮች ብቻ ሳይሆኑ ኅብረ-ኢንዳስትሪዎችና ዓለም አቀፍ ባለ ሃብቶች የሚቋምጡት አንዳንዶቹም በተዘዋዋሪ በመቆጣጠርና በክልሉ ያለው የተፈጥሮ ሃብት ለመቀራመት የፈጠሩት የሰላሙ እጦት ሁኔታ ተገን በማድረግ ለትርፍ ማካበቻ እያዋሉት ነው። ሌላው በበኒ የአገሪቱ ክልል በቅርቡ ጅሃዳዊ እስላም ርእዮተ ዓለም ያደረገ እስላማዊ ኃይል ጭምር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ይኽ የሸበራ ኃይልም ባለፉት የመጨረሻ ሁለት ዓመታት ውስጥ በፈጸመው የሽበራ ጥቃት ሳቢይ ብዙ ንጹሓን ዜጎችን ለሞት ዳርጓል። ስለዚህ ያለው የፖለቲካው አለ መረጋጋት ይክ ዓይነት ጅሃዳዊ ኃይል ከታከለበት በእውነቱ የአገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለክልሉ መረጋጋት አቢይ ስጋትና ለመቅረፉም እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የሚጠይቅ ይሆናል፡ ካቢላ ሁለቴ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ሆነው ከመሩ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ በእጩነት በመቅረብ ሕገ መንግሥት የሚጻረር ተግባር እውን ካደረጉ በአገሪቱ ያለው ችግር ሊያባብሰው እንደሚችል ነው ያም ሆኖ ይኽ በሚቀጥሉት ሳምንት ስለዚህ ጉዳይ የርእሰ ብሔር ካቢላ ውሳኔ ምን እንደሚመስል የሚታይ ይሆናል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.