2016-11-18 15:40:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ሙስናና ምግባረ ብልሽት ማኅበራዊ ቸነፈር ናቸው


“ማንኛውም የሰው ልጅ እንቅስቃሴ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶችና መዋዕለ ንዋይ የምህረት ማሰልጠኛ ሊሆኑ ይችላሉ” የሚል ቅዉማ ሃሳብ ያማከለ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እነዚያ “የንግድ ድርጅቶች መራሕያን፥ “(ሁሉንም የሚያካትት) ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አባሪነት ለማረጋገጥ የሚያገለግሉ ናቸው” በሚል ርእስ ሥር ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት በተለያዩ 40 አገሮች ቅርንጫፎች ካሉት ከዓለም አቀፍ ክርስቲያን ባለ ሃብቶችና የሥራ ዕድል ፈጣሪያን አካላት ማህበር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የምገኙትን 500 ተጋባኣያን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታወቁ።

ይኽ ዓውደ ጉባኤ በዚህ የምሕረት ዓመት የመገባደጃ ጊዜ በመከናወን ላይ ያለ በመሆኑ ክርስቲያን ባለ ሃብቶች ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አባሪነት እርሱም ሁሉንም ያካተተ ማንንም የማይነጥል ሂደት ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ቀላልና ቁልቁለት ሳይሆን ብዙ ውጣ ውረድና እንቅፋትም ያለበት የላቀ ምርጫ ነው።

የኤኮኖሚ አውታሮች ለአገልግሎት እንጂ ሃብት ለማካበት የሚከወኑ መሆን የለባቸው። በትርፍ ለመትረፍረፍ አይደለም። ገንዘብ ገለልተኛ የሆነ እሴት የለውም ክብር የሚያሰጠው ግቡና የአጠቃቀሙ ውጥን ነው፡ ክብር የሚያሰጠው እምን ጥቅም ላይ ከማዋሉ ሂደቱ ጋር የተቆራኘ ነው። ሆኖም ገንዘብ የገዛ እራሱ ክብር ያለው በውስጥ እሴት ያቀበ አድርጎ መመልከትና የገዛ እራሱ ገለልተኛና ለየት ያለ እሴት እንዳለው አድርጎ መመልከቱ ለገንዘብ ሥልጣን ተገዥ ያደርጋል። ስለዚህ ከዚህ አንጻር ቅዱስ አባታችን የባንኮችና የቁጠባ ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያለው ማኅበራዊ ድማጤው ዳግም ግምት መስጠት ያለው አስፈላጊነት ካብራሩ በኋላ ከዚህ በመንደርደር የድኾች አገሮች ቁጠባና ኤኮኖሚ ለሓራጣው ኤኮኖኖሚ እንዳይዳረግ አቢይ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ በጥልቀት ሊስተዋል ይገባዋል እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታች ሁለተኛው ስጋት ሙስናና ምግብረ ብልሽት መሆኑ ጠቅሰው፥ ሙስናና ምግባረ ምልሽት አቢይ ማሕበራዊ ቸነፈር ናቸው። አንድ ድርጅት የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ መሆኑ በይስሙላ እየኖረ ግላዊና ወይንም የንግድ ድርጅቱ ግላዊ ጥቅም ብቻ ለመሻት የሚያደርገው የማጭበርበር ተግባር ሙስናና ምግባረ ብልሽት ያስከትላል። ስለዚህ ሙስናና ምግባረ ብልሽት ደግሞ የተጭበረበረ ዴሞክራሲ መኖሩ ምልክት ነው። ለሌሎች የክፋት ተግባሮች ክብር ሰራዥ ለሆኑት ምርጫዎች ተብለው ለሚጠሩት ተግባሮች ይዳርጋል። ለምሳሌ ለአደንዛዥ እጸዋት ዝውውር ሰውን ለጾታዊ ስሜት ማርኪያ መሣሪያ የሚያደርግና እንዲሁም ሰዎችን በሕገ ወጥ ተግባር የተጭበረበረ ዴሞክራሲ ከሚፈጥረው ድኽነት ጋር የተላተሙ ተጠቂ የሆኑ ከቦታ ቦታ ለሚያንቀሳቅሱ የወንጀል ቡድኖች መስፋፋት ለአዲስ ባርነት መገልገያነት የሚዳርግ የውስጥ አካለ ብልት ንግድ በተያያዘ መልኩም የሚፋፋሙት ግጭቶች ለሃብት ማደለቢያ ለመጠቀም የጦር መሣሪያ ንግድ ሩጫ ይጣጡፋል። ሙስና የተጭበረበረ ዴሞክራሲይ ይወልዳል የተጭበረበረ ዴሞክራሲ ደግሞ ለዘርፈ ብዙ አደጋ የሚጋልጥ መሆኑ እላይ እንደ ተመለከተው ነው። ሦስተኛው ሥጋቱ ደግሞ የኤኮኖሚ ድርጅት ባለ ሃብቶች መራሕያንና ሠረተኞች መካከል የገዥና የተገዥ አስተዳድራዊ መዋቅር የሚከተሉ እንዳይሆኑ የሚለው ነው። ስደተኞች በተስተናገዱበት አገር ተዋህደውና በተራቸውም ባለ ሃብት ለመሆን የበቁት ለማሕበራዊ ጥቅም የሚተጉ ሆነው ድኽነትን ካለ መርሳት በድኽነት የሚገኙትን መደገፍ ይጠበቅባቸዋል። ስለዚህ ሰብአዊነት ያማከለ የኤኮኖሚ ፖለቲካ ለተካፍሎ መኖር መሠረት ነው። ድኽነት ያለኽን ተካፍሎ ለመኖር ጥበብ ያነቃቃል። ይኽ ጥበብ በኤኮኖሚውና በቁጠባው መስክ አሳክቶ ማንም የማይነጥል የኤኮኖሚ ፖለቲካና ሂደት ማረጋገጥ የሁሉም ባለ ሃብቶችን ባለ ድርጅቶች ኃላፊነት ነው እንዳሉ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.