2016-11-17 10:04:00

ቅዱስነታቸው "የሚበድሉንን ሰዎች በትዕግስ ማለፍ የክርስቲያኖች መለያ ባህሪ ሊሆን ይገባል" አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 9/2009 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች አስተላልፈዉት የነበረው ጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት ላይ አድርጎ የነበረ ሲሆን መከራዎችን በትዕግስት ማለፍ ይጠበቅብናል ምክንያቱም ትዕግሥት የክርስቲያን አንዱ መገለጫ ባህሪዕ ስለሆነ ነው ብለዋል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ የዛሬው ጠቅላላ አስተምህሮ ክፉ ነገሮችን የሚያደርጉብንን ሰዎች በትዕግስ ማለፍ ይጠበቅብናል በሚለው ጭብጥ ላይ ያተኮረ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ክፉ ነገር የሚፈጽሙብንን ሰዎች በትዕግስት ማለፍ ይጠበቅብናል ብለው በተለይም ሁል ጊዜ እንቅፋት የሚሆኑብንን ሰዎች እግዚኣብሔር ለእኛ ኋጥያተኞች ከሚያሳየውን ትዕግስት በመማር እኛም ይቅር ልንላቸውና ልንታገሳቸው ይገባል ብለዋል።

ታጋሽ መሆን በምንለማመድበት ወቅት ሁሉ ተግባራችንንና ውድቀታችንን እንድናስብ ያደርገናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ትዕግስት ማድረግ ከቀሪዎቹ ሁለት ማለትም ከኋጥያተኞች ጋር አለመተባበር ከሚለው እና የማያውቁትን ሰዎች ማስተማር ከሚሉት  መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት ጋር እንደ ሚገናኙ ገልጸው ከፍተኛ የሆነ ትዕግስት የሚያሳዩ ቤተሰቦችን ማመስገን እንደ ሚገባ ገልጸው መንፈስ ቅዱስ ደጋጎችና ታጋሾች በመሆን በአከባቢያችን ያሉትን ሁሉ መርዳት እንድንችል ይረዳን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል ማለታቸው ተገልጹኋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ አባታችን ካስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ በመቀጠል ያስተላላአፉት መልእክት በተለየ ሁኔታ የሕፃናትን ጉዳይ ትኩረት አድርጎ የነበረ ሲሆን አጋጣሚውን ተጠቅመው በመጭው ኅዳር 11/2009 ዓ.ም ከሚጠናቀቀው ከቅዱስ ልዩ የምሕረት አመት ጋር መሳ ለመሳ በመሆን ዓለማቀፍ የሕጻናት ቀን እንደ ሚከበር ቅዱስነታቸው ገልጸው ለልጆች ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ “ለባርነት፣ ለውትድራና እና ለጥቃት እንዳይጋለጡ መከላልከል እንደ ሚገባ” አሳስበው ለእዚህም ተፈጻሚነት ዓለማቀፍ ማኅበረሰብ ጥበቃ በማድረግ የበኩላቸውን ግዴታ መወጣት እንደ ሚኖርባቸው ካሳሰቡ ቡኋላ መልእክታቸውን አጠንቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.