2016-11-14 16:29:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እግዚአብሔር ፈጽሞ ለብቻችን አይተወንም


ቅዱስ ሥፍራ ቢሆን በጠቅላላ የሰው ልጅ የሚገነባው ሁሉ አላፊ ነው፡ ስለዚህ በምንገነባቸው ነገሮች ሁሉ የሰውን ልጅ የሚሻውን የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ግምት ለሚሰጡት የሃሰት መሲሃውያን ሁሉ ደህንነታችንን አናወክፍ። ብቸኛው እርግጠኛነት ሕይወታችን በእግዚአብሔር እጅ ላይ መሆኑ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ፈጽሞ አይተወንም፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. እኩለ ቀን በለገሱት የጸሎት መልአከ እግዚኣብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በማብራራት አያዘውም ዕለቱ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች በሚገኙት ካቴድራሎች የምህረት ዓመት ምክንያት ላንድ ዓመት ተከፍቶ የቆየው ቅዱስ በር የሚዘጋበት ዕለት መሆኑ አስታውሰው፡ ሕይወታችንን በከንቱ ማጣት አይገባንም፡ ምክንያቱም በጌታ እጅ ነውና። ኢየሱስ እነዚያ ለሰው ልጅ መሠረታዊ አስፈላጊነት ያላችው ነገሮች ሁሉ የሚያሰላስሉ ለእራስ ጥቅም በማሰብ ግምት የሚሰጡ እንዳሉ ጠንቅቆ ያወቀዋ። ስለዚህ ከእንደነዚህ ዓይነት መሲሃውያን እንድንጠበቅ ያሳስበናል። ዛሬም እነዚህ የሐሰት መሲሃውያን አሉ። እነርሱ የዚህ የዓለማዊ ተጨባጭ ሁነት አካል ናቸው።

ስቃይ መከራ ሁሉ ቢፈራረቅባቸውም ሕይወታቸው በጌታ እጅ ላይ ጸንቶ የቆመ መሆኑ በመታመን በእርጋታ ሳይረበሹ የኖሩ ሰዎች እንደነበሩና እንዳሉም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሚያረጋግጠው ሐቅ ነው። በዚህ ዓይነቱ ታሪክ ቤተ ክርስቲያን እጅግ ሃብታም ነች። እግዚአብሔር ታማኝ አባት ነው። ልጆቹን ፈጽሞ ለብቻቸው የማይተው የሚባባ እርህሩህ አባት ነው። ይኽ እማኔ በልባችን ልንይዘው ይገባናል። እግዚአብሔር ፈጽሞ ለብቻችን አይተወንም።

ቅዱነታቸው በላቲን ሥርዓት በዕለቱ ከሉቃስ ወንጌል የተወሰደውን ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ፊት ሆኖ ስለ የመጨረሻው ቀን በተመለከተ የተናገረው ቃል ላይ ያማከለ ምንባብ መሠረት በማድረግ በለገሱት አስተንትኖ፥ ሁሉም ያ የሰው ልጅ የሚገነባው ቅዱስ ሥፍራ’ኳ ቢሆንም ያልፋል ይፈርሳል በሚያልፈው ነገር ላይ ደህንነታችን እናስቀምጥ። በሕይወታችን ጽኑ መልሕቅ ብለን ያልናቸው እምነታችን ያኖርንባቸው ምድራውያን እርግጠኞቻችን መድህን ብለን ያሰንብናቸው ነገሮች ሁሉ ከንቱና ጠፊዎች ናቸው። አንዚህ ነገሮች ሁሉ መጠጊያችን አናድርግ። ማምለጫ የማይገኝባቸው ከእኛ አይርቁም ብለን ያልናቸው ችግሮች ቆይውተው ሲፈቱና በነው ሲጠፉ አይተናል። ማኅበረ ክርስቲያን ወደ ጌታ ያመራና ከዚያች ከጌታ ቀን ጋር ለመገናኘምት ሲጓዝ ቀኑን በጌታ ቀን ላይ አነጣጥሮ ሲኖር ደስተኛ ይሆናል። በጥልቀት የጌታ ቀን የጌታ እውነት ለመረዳት ለምትደግፈን ድንግል ማርያም ጥበቃ ገዛ እራሳችንን እናወክፍ በጌታ ጸንቶ ለመገኘት። በዚያ ጌታ ፈጽሞ እንደማይተወን ለሚያርጋግጥልን እውነት ምንም’ኳ ያ በሕይወታችን ጠባሳ ጥሎ የሚያልፈውም ችግር ቢፈራረቅብንም በጽናት ታምነን ተስፋ በማድረግ የበለጠውን ዓለም ለመገንባ እንትጋ፡ ለመትጋቱ  የምናደርገው ጥረት ሁሉ … በዚህች በተለያ አገሮች በሚገኙት ካቴድራሎች በምሕረት ዓመት ምክንያት ተከፍተው ለአንድ ዓመት የቆዩት ቅዱሳን በሮች በሚዘጉበት ዕለት ጋር በማጣመር ልንመለከተው ይገባናል። ቅዱስ ዓመት እይታችንን በዚያ በሙላት በተገለጠው በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ለማኖር በሌላው ረገድም በዚህች ምድር መጻኢያችንን ነባሪውን ሁነት ለሁሉም የመዳን ጊዜ እንዲሆን በወንጌል በመስበክ እየጣርን እንገንባ።

እግዚአብሔር የታሪካችን መሪ ነው። የነገሮችና የሁነቶችን ውስጠ ነገር ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቅ አምላክ ነው። ምክንያቱም በእርሱ በጌታ መሐሪው እይታ ሥር ነው። ሁሉም በእርሱ ነው።

በመጨረሻም ዕለቱ በኢጣሊያ የምርት ቀን ተብሎ የሚታሰብ መሆኑ ዘክረው አደራ ተፈጥሮን ለማስተዳደር የተሰጠን ኃላፊነት ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ በማራመድና ገቢራዊ በማድረግ ለሁሉም በማሰብ እንወጣው። ቤተ ክርስቲያን ለአርሶ እደሩ ቅርብ ነች ብለው እነዚያ ለሕይወት መሠረታውያን ነገር ሁሉ ለተነፈጋቸው እጅግ ቅርብ ነች ካሉ በኋላ በምሕረት ዓመት ምክንያት ሮማ የገቡትን ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡትን መፍሳያን ነጋድያን ሰላምታቸውን አቅርበው እንዳበቁም፡ በቅርቡ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሚገኘው በቅድስተ ቅዱሳት ቤተ ጸሎት ውስጥ ያለው ጥንታዊው የስቁል ኢየሱስ ቅዱስ ምስል መታደሱና ወደ ነበረበት ስፍራ መመለሱ አስታውሰው ይኽ ደግሞ ከምሕረት ዓመት ጋር የተገናኘ እቅድ መሆኑም እጅግ ከፍ ያለ ትርጉም አለው በማለት የለገሱት አስተንትኖ አጠናቀው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብቷል።








All the contents on this site are copyrighted ©.