2016-11-11 16:25:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃለ ምዕዳን የክርስቲያን አኃድነት ለሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጉባኤ ተጋባእያን


ብፁዓን ካርዲናላት

የተከበራችሁ ወንድሞች ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት

የተከበራችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ

“አኃድነት ክርስቲያን፥ ለተሟላ አኃድነት የትኛውን አብነት” በሚል መሪ ቃል የክርስቲያኖች አንድነት የሚነያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያሰናዳው ምሉዕ ዓመታዊ ጉባኤ ለአኃድነት የሚደረገው ጉዞ እንደ አብነት የሚከተለውን መንገድና ስልት የሚለው ነው። እ.ኤ.አ. በዚህ በ 2016 ዓ.ም. በውስጥና በውጭ ያደረግኳቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎች በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን በሚደረገው የጋራው ውይይት ላይ የተማከለ በመሆኑ የጋራው ውይይት በቅድሚያ እንድኖር እድል ፈጥሮልኛል። በተካሄዱት ግኑኝነቶች ያንን ህያውና ብርቱ የአኃድነት ፍላጎት መኖሩ ለማስተዋል በቅቻለሁ። ይኽ ደግሞ በእውነት ያጽናናኛል። እንደ የሮማ ጳጳስና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንድሆን ጌታ በሰጠኝ የአደራ ኃላፊነት የአቢያተ ክርስቲያን አኃድነት ማረጋገጥ ተቀዳሚ ሐዋርያዊ ጥረቴ መሆኑ ያመላክተኛል። የጥምቀት ምስጢር የተቀበለ ሁሉ የዚህ ፍላጎት ተካፋይ እንዲሆንም እማጠናለሁ።

የክርስቲያን አንድነት የእምነት አስቸኳይ መሠረተ ነገር ነው፡ ይኽ የአኃድነት አስቸኳይ መሠረተ ነገርነቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ካለን እምነት የመነጨ ነው። አኃድነትን ስንማጠን ኢየሱስን እንማጠናለን። አኃድነት ለመኖር እንሻለን ምክንያቱም ኢየሱስን ፍቅሩን ለመከተልና ለመኖር ስለ ምንፈልግና ያ የመለኰታዊ ፍቅር ማንነቱ የሆነው እርሱ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ያለው የአኃድነት ምስጢር ለማጣጣም ስለ ምንፈልግ ነው። ኢየሱስ በገዛ እራሱ በመንፈ ቅዱስ አማካኝነት፥

“ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ። ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤ እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ” (ዮሐ. 17, 21-26 ተመል.)።

ሲል በደገመው ጸሎት እናብር ዘንድ ያብቃን። የኢየሱስ ክህነታዊ ጸሎት ያ አኛ የምንመኘውን በዚያ በኢየሱስ አማካኝነት ከአብ የተጸግወልን ኅልዩና ጠመቅ ትምህርት የሚያስቀምጠው አኃድነት በፍቅር የሚል ነው፡ ወንጌልን መረዳቱ ላይ ስምምነት ማድረግ ለብቻው በቂ አይደለም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ እኛ በክርስቶስ አማኞች በክርስቶስ ያበርን መሆናችን ማመን ያስፈልገናል። በግልም በማሕበርም እምነታችን ደረጃ በደረጃ ወደ ጌታ ማሳደግ የሚል ነው (ሮሜ. 8,28 ተመል.)። በመካከላችን ሱታፌ ለማጎልበት የሚያበቃን ዘወትር መኖራችን በእርሱና ለእርሱ (ገላ. 2,20 ተመል.) የሚል ሲሆን ነው። ይኽ ደግሞ የዚህ የምታካሂዱት ዓውደ ጉባኤና ሌሎች አኃድነት ላይ በማነጣጠር የሚካሄዱት ጥረቶች ሁሉ ያለውን ልዩነት እንዲጠብ የሚያደርግ መንፈስ ነው። ይኸንን ግምት ውስጥ ማስገባትም ወደ አኃድነት የሚሸኙን ከአኃድነት መሠረታዊ ትርጉሙ ጋር ተጋጭነት ያላቸው ቅንነት የሌላቸው የሱታፌ አብነቶችን ለይተን ለማስተዋል ይርዳናል።

በቅድሚያ አኃድነት ለሰው ልጅ ጥረትና የቤተ ክርስቲያናዊ የሥነ ግኑኝነት ብልሃት የሚያስገኘው ውጤት ሳይሆን ከላይ የሚመጣ ተሰጭ ጸጋ ነው። ለእኛ የሰው ልጆች ለብቻችን አኃድነትን ለማረጋገጥ አይቻሌ ነው። ግዜውናን ዓይነተ ቅርጾቹን ለመወሰኑም ብቃቱ የሌላቸው ነን። እዲህ ሲሆን የእኛ ሚና ምን መሆን ይገባዋል? የክርስቲያን አኃድነት ለማነቃቃት ምድርን ማድረግ ይገባናል? ኃላፊነታችን ያንን ጸጋ የሆነውን አኃድነት በእሺታ ልባችንን ከፍተን መቀበልና ለሁሉም መመስከር ነው፡ በዚህ እይታ ደግሞ አኃድነት የእነዚያ በአኃድነት ተግባር የሚሳተፉ የማንንት መለያቸውን ለማቀብ የሚያስችላቸው የገዛ እራሱ ምትና ጊዜ ቀስ የሚልበትና ፈጣኝነቱን የሚያርፍበት የጊዜ ህርመት ሁሉ ያለው ጉዞ ነው። ስለዚህም ጉዞ እስከ ሆነም ድረስ ተስፋ ማድረግን ትዕግስትና ጽናት ድካምና ጥረትን ይወክላል። መግባባት ወጥረት አያስወግድም እንዳውም አልፎ አልፎን ለባሳ አለ መረዳዳት አደጋ ሊያጋልጥ ይችላል። በመሆኑም አኃድነት በዚያ ግብ በሆነው ገና ሩቅ የሚመስለው ለአንድነት በሚያደርገው ጥረት ብቻ ነው ከወዲሁ ሊስተናገድ የሚችለው። ገና ያልተደረሰ እርቁ ያለ ግብ ቢሆንም በዚህ ግብ ላይ አነጣጥሮ በሚደረገው ጉዞ ውጣ ውረዶች ቢኖሩም ሁለ መናው በዚህ ጉዞ ላይ ማኖር ደስተኛ ያደርጋል። ይኽ ጉዞ በደስታ መከወን አለበት። ሁሉም የጌታ ፍቅር ፈላጊ ነው። ኃጢአተኞች ከመሆናችን ካለን የጋራው ተመክሮ በተመሳሳይ መልኩ ኃጢአተኞች መሆናችን የዚያ በኢየሱስ ክርቶስ የሚገለጠው ወሰን አልቦ የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር ፍፈላጊዎች መሆናችን ካለን ተመክሮ በላይ የሚያስተባብረን ሌላ ምን ነገር ይኖረናልን? የተስተካከለ የፍቅር አኃድነት፥

በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና። እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው። እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል” (2ጴጥ. 2, 4-10)

ለዚህም ነው አኃድንት እየተጓዝክ የሚከወን መሆኑ የሚለውን ሃሳብ ደጋግሜ ለማስታወስ የምወደው። በአንድነት ስንጓዝ እንደ ወንድሞች ስንገናኝ በጋራ ስንጸልይ ወንጌልን ስናበስር የመጨረሻ የሚባሉትን በማገልገል ተግባር ስናብር ይኸው አኃድነትን ከወዲሁ የምንኖር መሆናችን ለማስታወስ ያክል ነው። አሁንም የሚከፋፍሉን እጽብ ድንቅ የቲዮሎጊያ የሥነ ቤተ ክርስቲያን ጥናቶችና ምርምሮች ዛሬ በዚህ ለቤተ ክርስቲያን በሚናገረው መንፈስ ቅዱስ የሚከወን በመሆኑ ውኅደቱ መቼና እንዴት መሆኑ ሳናስተውለው በምናደረገው ረዥሙ የጋራው ጉዞ ተኪዶ ወቅት ይወገዳሉ።

በሁለተኛ ደረጃም አኃድነት ተከታታይነት ያለው ሥርዓተ ጠበቅ አይደለም። የቲዮሎጊያ የሊጡርጊያ የመንፈሳዊነት ሕገ ቀኖናዊነት ያስከተሉ ልዩነቶች አሉ። እነዚህ ልዩነቶች በክርስትና ጉዞ በሐዋርያነት ጥበብና ንቃት የጸኑ በመሆናቸው ሃብት እንጂ ለቤተ ክርስቲያን አኃድነት ስጋት አይደለሙ። እነዚህን ዓይነት ልዩነቶች ማፈንና መጨቆን ያንን በተለያዩ ጸጋዎቹ ብዙኅነትን ያደለንና ለአማኙ ማኅበረሰብ በተለያዩ ስጦታዎቹ ሃብታም የሚያደርግና የሚንቀሳቀሰው መንፈስ ቅዱስ መቃወም ይሆናል።

ባለፉት የታሪክ ጉዞዎች የዚህ ዓይነቱ የሚያሰቃይ ተመክሮ አስቀምጦ ያለፈ ጉዞ ዛሬም በተለያየ ወቅት ይታያል። ሆኖም በመንፍስ ቅዱስ ለመመራት ስንፈቅድ ስጦታዎችና ብዙህነቶች ልዩነቶችና መለያዎች ወደ ግጭት የሚዳርጉ ምክንያቶች ሳይሆኑ ይቀራሉ። ምክንያቱም ብዙህነት በቤተ ክርስቲያናዊ ሱታፌ እንድንኖረው ስለ ሚያደርግ ነው። አኃድነትን አልሞ የሚደረገው ጥረት ቅንነት ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ርቱዕ የሆኑትን ብዙኅነቶች ማክበር ከዚያ እግዚአብሔር ከሚጠይቀን ግብረ አኃድነት ጋር ሊስማማ የማይችለው ወይንም ሊታረቅ የማይችሉ ልዩነቶች እንዲቀረፉ ያግዛል። ጽኑ የሚመስሉት ልዩነቶች ሰላላ እንዳያደርጉን መሰናክሎች ሁሉ ገና ከወዲሁ በጋራ ለመግጠም የሚዳርጉን መሆን ይገባቸዋል።

በመጨረሻም አኃድነት ስበት ወይም መዋጥ መጥጦ ማስቀረት ማለት አይደለም። የክርስቲያን አኃድነት ወደ ኋላ የሚሳብ አይደለም። ስለዚህ አያንዳንዱ ማኅበረ ክርስቲያን የገዛ እራሱ መለያ የእምነቱ ታሪክ መካድ አለበት የሚል ወይንም ሌላውን ሃይማኖቱን ለማስቀየር የሚደረግ ጉዞ ለክርስቲያን አኃድነት መርዝ የሆነው ተግባር እንደ ቅብሉ አድርጎ ማሳብ ማለት ሳይሆን የሚለያየውን ቀደሞ ከማየት ይልቅ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አበይት ጥንታውያን ቀደምት አኃዳውያን የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎችን የመሳሰሉት አንድ የሚያደርጉንን መሠረታውያን ነገሮች ያላቸው ሃብት ማስተዋል ያስፈልጋል።

በዚህ መንገድም እኛ ክርስቲያኖች በዚያ ብቸኛ በሆነው ጌታና መድኅን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የምናምን በጋራ ያንን አንድ የሚያደርገንን ቃለ እግዚአብሔር ለመታዘዝ የሚጣጣሩና የሚሹ እንደ ወንድማማቾች ለመተዋወቅ ነው። የአኃድነት ጥረት እውነተኛ የሚሆነው እይታው በገዛ እራሱ ላይና በገዛ እራሱ የመከራከሪያ ሃሳብና ስሌቶች ላይ እሳቤው የሚያኖር ሳይሆን ያንን ሊስተዋልና ሊደመጥ ለዓለም ሊመሰከር የሚሻው የእግዚኣብሔር ቃል እንዲስተዋል ሲያደርግ ብቻ ነው። ስለዚህ የተለያዩ ማሕበረ ክርስቲያን ሲወድሩና ሲበላለጡ ሳይሆን ሊተባበሩ የተጠሩ ናቸው። በቅርቡ (ዝክረ 500ኛው ዓመት የሉተራን ህዳሴ በዓል ምክንያት) በስዊድን ሉንድ ከተማ ያካሄድኩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያንን በ 1952 ዓ.ም. የሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት የሰነደው የተለያዩ ማኅብረ ክርስቲያን፥ “የጋራው ኑሮ ጥልቅና አቢይ ችግር ከሆነበት ጊዜ ውጭ ሁሉም ነገር በጋራ እንዲያደርጉ” በማለት የክርስቲያን አንድነት ያለውን ክብር እንዲስተዋል ማድረጉን በቅርብ ለመመልከት አስችሎኛል። ስለ የአንድነት ጉዞ የምታደርጉት ጥረት አመስግናለሁ ጸሎቴም አረጋግጥላችኋለሁ። እናንተም ስለ እኔ እንደምተጸልዩ አምነቱ አለኝ። ጌታ ይባርካችሁ ማርያም ታቅባችሁ በማለት የለገሱት ቃለ ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።  








All the contents on this site are copyrighted ©.