2016-11-09 13:36:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ስልጣንንና ባለ ጠግነትን የሚራቡ ሰዎች እግዚኣብሔርን በትክክል ለማምለክ ይቸገራሉ ማለታቸው ተገለጸ።


ክቡራን እና ኩቡራት አድማጮቻችን ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ለ349 ቀናት ያህል የቆየውን ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት እንደ ሚታወቀው ከኅዳር 29/2008 ዓ.ም ላይ የጀመረ ሲሆን ከ12 ቀናት ቡኋላም በኅዳር 11/2009 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት በመላው ዓለም በምትገኘው ያቅቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልዩ መንፈሳዊና አካለዊ የምሕረት ተግባራትን በመፈጸም እየተገባደደ ይገኛል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ በተደጋጋሚ እንደ ሚያሳስቡን በእነዚህ 347 ቀናት ውስጥ በቅዱስ በር ማለፍ እና ንስኋ መግባት አስፈላጊ መንፈሳዊ ተግባራት ቢሆኑም ነገር ግን ንስኋችን፣ መጸጸታችንን በሚገልጽ መልኩ መልካም ተግብራትን በመፈጸም መግለጽ እንደ ሚጋባ በተደጋጋሚ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን እነዚህን መንፈሳዊና አካላዊ የምሕረት ተግባራት ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ከተገባደደም ቡኋላ በመላው የካቶሊክ ምዕመናን ልብ ውስጥ እነዚ የምሕረት ተግባራት ታትመው ይቀሩ ዘንድና ቀጥይነት ባለው መልኩ እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ማከናወን የሚገባን መንፈሳዊ ግዴታዎቻችን እንደ ሆኑ ስያሳስቡን ቆየተዋል።

ስለዚህም በተቀሩት 12 ቀናት ውስጥ አካላዊና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት እነማን እንደ ሆኑ ማስታወስ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘታችን የመጀመሪያውን ክፍል ሁለቱን የመጀመሪያ አካለዊ የምሕረት ተግባራትን እነሆ ዛሬ እናቀብላችኋለን እንድትከታተሉን በትህትና እንጋብዛለን።

አካለዊ የምሕረት ተግባራት

አካላዊ የምሕረት ተግባራት መሰረታቸውን ያደረጉት በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፣31 ጀምሮ በጠጠቀሰው የኢየሱስ አስተምህሮ ላይ ሲሆን ይህም በዓለም መጨረሻ የሚሆነውን የፍርድ ሂደት የሚያመልክት እና “ኢየሱስ በመላእክቱ ታጅቦ በፍርድ ወንበር ልይ በመቀመጥ፣ እረኛው በጎችን ከፍዬሎች  እንደሚለይ እርሱም ሕዝቦችን ይለያል፣ በጎችሁን በቀኙ ፍዬሎቹህ ደግሞ በግራው ያቆማቸዋል” እንደ ሚለው በመጨረሻው ቀን በኢየሱስ ፊት በምንቆምበት ወቅት ለሚያቀርብልን ጥያቄዎች በድፍረት በቂ የሆነ ምላሽ መስጠት እንድንችል እና ከፍየሎቹ ተርታ ሳይሆን ገበጎቹ ጎራ መሰልፍ እድንችል የሚያግዙን ተግባራትን መፈጸም ይገባል። በዛሬው በትቅምት 29/2009 ዝግጅታችን ሁለቱን ቀዳሚ የምሕረት ተግባራትን እናቀርባለን እንድተከታተሉን እንጋብዛለን።

የተራበን ማብላት: አሁነ በምንገኚበት ዓለማችን በጣም ብዙ የሚባሉ ሰዎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። በተቃራኒውም የበለጸጉ በሚባሉ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የምግብ ብክነት የሚታይ ሲሆን በማነኛውም ረገድ ምግብን ማባከን ተገቢ አለመሆኑን በመረዳት በግባቡ እንድንጠቀም እና የተራቡ ወገኖቻችንን፣ ጎሬቤቶቻችንን፣ እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች በየመንገዱ ወይም ደግሞ የቤታችንን በር ለሚያንኳኩ ሰዎች አስፈላጊውን ምላሽ መስጠት መንፈሳዊነታችንን ያጠናክራል ከእግዚኣብሔር በረከትን ያስገኛል። የተራበን ማብለት በረከትን ያስገኛል። በሉቃስ ወንጌል 16.19-31  ላይ የተጠቀሰውን የሀብታሙን ሰውና የድኻውን የአልዓዛር ታሪክ ማንበብና ያነበብነውን በተግባር በሕይወታችን መፈጸም ይገባናል።

የተጠማን ማጠጣት: በተለያየ የዓለም ክፍል ውስጥ የሚገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መሰረታዊና ለሰው ልጆች ሕይወት አስፈላጊ ከሚባሉ ነገሮች በቀዳሚነት በሚጠቀሰው የንጹህ ውሃ እጥረት ይሰቃያሉ። በንጹሕ ውሃ እጥረት የሚሰቃዩ ለወንድም እና ለእህቶችን የተቻለንን ያህልል በማድረግ የክርስቲያናዊ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል። ይህንን የንጹህ ውሃ እጥረት ለተጠሙ ሰዎች ብቻ ውሃን በመስጠት የምንወጣው ተግባር ሊሆን ብቻ ሳይሆን የሚገባው ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል። ኢየሱስ በቃሉ “ እውነት እውነት እላችኋለሁ የኔ ደቀ መስሙር በመሆኑ ከነዚህ ታናናሶች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም” (የማቴዎስ ወንጌል 10.42)።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.