2016-11-09 15:59:00

ቅዱስ የምሕረት ዓመት፥ የድኾችና የተናቁት ኢዮበልዩ ቀን


እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቀው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በዚህ ወደ መጠናቀቁ እያዘገመ ባለው ባወጁት የምኅረት ዓመት ውስጥ የድኾች የተናቁትና የተገፉት ኢዮበልዮ ቀን እንዲኖር የጠሩ ሲሆን ይኽ ለሦስት ቀናት የሚካሂደው የድኾች ኢዮቤልዩ ቀን በድኽነት የተጐሳቆሉት የተናቁት የተገፉት ማሕበራዊ መገለል አጋጥሞአቸው የሚሰቃዩትን የኅበረተሰብ አባላት እ.ኤ.አ. ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር በመገናኘት መሪ ቃል እንደሚቀበሉና እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚያሳርጉት ምስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚጠናቀቅ ስለዚሁ መርሃ ግብር በተመለከተ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማሳወቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ አስታወቁ፡

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ማግስት የዚህ ተጠቅሞ መጣል የሚለው በተለያየ ምክንያት ማሕበራዊ ኤኮኖሚያዊ እኩልነትን በማዛባት የዓለም ሃብትና እድሎችን ሁሉ በማግበስበስ ድኽነት የሚያስፋፋው ድኻውን እንደ ውዳቂ የሚያይ የሚያገል የሰው ልጅ ጥልቁና መሆናዊ መብቱን የሚተላለፍ ባህል በመቃወም ድኾች ለምንኖርበት ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ዘይቤ ብቻ ሳይሆን አማኞች ነን ለምንለው አቢይ ጥያቄ ናቸው። ስለዚህ ድኻውን ኅብረተሰ የማያማክል ኅብረተሰብ ስልጡን ሊባል እንደማይችል በመደጋገም የሚስጡት ትምህርት የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት የሚያመለክተው መሆኑ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር ያስደመጡት የካቶሊካዊው ቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር አባል ካርሎ ሳንቶሮ ማሳወቃቸው ሳባቲነሊ ገለጡ።

የምንኖበት ወቅታዊው ዓለም ድኻውን እያየኸው እንዳላየኸው ወይንም ድኻው ሊታይበት ወደ ማይቻልበት ክልል ባማጋዝ ድኻው ካካባቢና ወትሮው ከምንንቀሳቀስበት ክልል እንዲርቅ ማድረግ ይቻል ይሆናል ሆኖም ከሕሊናችን ሊንፍቃቸው ፈጽሞ የሚቻለን እንደማይሆን የተረጋገጠ ነው። በዚህ የምሕረት ዓመት በድኾች አማካኝነት ለጌታ በቃልና በሕይወት ምሕረትን እንጠይቅ ዘንድ ቅዱስ አባታችን እያሳሰቡንና አብነቱንም እየሰጡን ነው። ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ቅዱስ በሮች ናቸው።

ድኻውን የኅብረተሰብ ክፍል እንዳይታይ ራቅ ወዳለው ክልል በማጋዝ ተከሎ እንዲኖር የማድረጉ ባህል እውነተኛው ድኽነት እርሱ ነው። ስለዚህ የከፋው ድኽነትና ባዶነትም ድኻውን ለማግለል መሞከርና ድኻውን ችላ የሚል ባህል ነው፡ ተካፍሎ መኖር ወደ ተናቁትን ወደ ተጠሙትና ወደ ተራቡት ማቅናት የስሜት ጉዳይ አይደለ ሰብኣዊነታችን ምሉእ የሚያደርገው ተግባር ነው፡ የሃብት መመዘኛው ገንዘብ የሚያደርግ ባህል በጉኡዛዊ ነገር ከፍ ሊያደርግ ይችል ይሆናል። ሁሉ ያለው ሁሉ የሆነ የሌለው ለመሆን አደጋ ያጋልጣል፡ የወደቀውን ማንሳት ጎንበስ ብሎ መደገፍ ምሉእ ያደርጋል። ምክንያቱም በተናቁት በተረሱት ዘንድ ጌታ ማደሪያውን አድርጓል የጌታ ትስብእት እውነተኛ ድኽነት ነው፡ ድኻው ወንጌል በሕይወቱ ይሰብክልናል ለዚህ ወንጌል በሕይወቱ ለሚሰብክልን ሰው ጀርባ ሰጥቶ መኖር ወንጌልን ኣለ መቀበል ይሆናል ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ዕለት በዕለት በቃና በሕይወት የሚያቀርቡልን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚናገረው ቃል መሰረት ያድረገ ሥልጣናዊ ትምህርት ነው እንዳሉ ሳባቲነሊ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.