2016-11-08 12:50:00

የቅድስት መንበር የሕትመት ቢሮ በቅርቡ በቻይና ያለ ቅድስት መንበር ፈቃድ የተሰጠውን የጵጵስና ማዕረግን ተቃወመች።


በቅድስት መንበር የሕትመት ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑ አቶ ግሬግ ቡሬክ ያለ ቅድስት መንበር ፈቃድ በቻይና በቅርብ ጊዜ የተሰጠውን የጵጵስና ማዕረግን በመቃወም የሰጡት መግለጫ።

“ባሳለፍነው ጥቂት ሳምንታት በቻይና አህጉር ያለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፈቃድና በኦፊሴላዊ መንግድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ከሆኑት ሰዎች ውጪ ማዕረገ ጵጵስና እየተሰጠ ይገኛል። የቅድስት መንበር ለዚህ ተግባር ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ፍቃድ አልሰጠችም ይፋዊ በሆነ መንገድ ስለ ጉዳዩም በምንም ዓይነት መንገድ እንድታውቅም አልተደረገም። እደነዚህ ዓይነቶቹ የጵጵስና ማዕረግ አሰጣጥ ሂደቶች በከፍተኛ ሁኔታ ህገ ቀኖናን የሚቃረኑ ናቸው። የቅድስት መንበር እነዚህ ተግባራት መሠረት የለሽ እንደ ሆኑ ተስፋ ያደርጋል። ይህን ለማድረግ በመጀመሪያ በበቂ ሁኔታ ጉዳዮቹን መገምገምና አስተማማኝ መረጃ መጠባበቅ ይኖርብናል። ይሁን እንጂ በድጋሚ ማሳወቅ የምንፈልገው ያለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፈቃድ ከግል እምነት በመነሳሳት  ማንኛውንም ዓይነት የጵጵስና ሹመት መስጠት የተከለከል መሆኑን እናሳውቃለን።

                                            








All the contents on this site are copyrighted ©.