2016-11-07 16:09:00

ቅዱስ የምሕረት ዓመት፥ የእስረኞች ኢዮቤልዩ ቀን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ የምሕረ ዓመት ውስጥ እ.ኤ.አ. ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. የእስረኞችና የግዞተኞች ኢዮቤልዩ ቀን ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተለያዩ ወህኒ ቤቶች የተወጣጡ አራት ሺሕ እስረኞችና የተበየባቸው የእስር ዓመታት አገባደው ነጻ የተለቀቁት እና ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸው እንዲሁም የወህኒ ቤቶች ቤተ ጸሎት ቆሞሶች በጠቅላላ ከ 12 አገሮች የተወጣጡ የተሳፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

ስለዚሁ የእስረኞች ኢዮቤልዩ ቀን ምክንያ በማድረግም የወህኒ ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች የጸሎት ቤት ቆሞሶች ጠቅላይ አስተዳዳሪ አባ ቪርጂሊዮ ባልዱኪ ከቫቲካን ረዲዮጋ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ለዚህ የእስረኞች ኢዮቤዩ ቀን ምክንያት በሁሉም ወህኒ ቤቶች በአስተንትኖ በቅዱስ መጽሓፍ ንባባት እንዲሁም በምስክርነትና በጸሎት የተሸኘ ሰፊና ጥልቅ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑ ገልጠው ከቅዱስ አባታችን የተሰፋ ቃል ለመታደል በቅቱል።

ጌታ የታሰሩትን የሚጎበኝ ብቻ ሳይሆን ወደ ቤቱም የሚጋብዝ ነው። ከእርሱ ጋር በማእድ ያስቀምጣቿል። ቤተ ክርስቲያንም እንደ መሥራቿ ይኸው በተለያየ ሁነት የሚገኙትን ልጆችዋን ትጎበኛለች። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እነዚህን ወንድሞቻችን በቤታቸው አስተናግደው መሪ ቃል ለግሷል።

የወንጌል ብሥራት ውጫዊ ተግባር ሳይሆን በእያንዳንዱ ሰው ልጅ ልብ ውስጥ ደስታ የመሻት በተስፋ መኖር የተስተካከለ ሕይወት መሻት በመኖሩ ይኽ ደግሞ በውስጣችን የብሥራተ ቃሉ ዘር እንዳለ ያረጋግጥልናል። ስለዚህ ወንጌልን ሥናበስር በሰው ልጅ ልብ ውስጥ በኑባሬ ያለውን የመልካም ነገር መሻትን ነው የምንቀሰቅሰው። ስቃይ ደስታ በሚፈራረቅበት ሕይወት በተለይ ደግሞ በወህኒ ቤት ያለው ዜጋ ዕለት በዕለት ከህሊናው ጋር የሚሟገት ወንድም ነው የምትሟገት እህንትም ነች። በወህኒ ቤት የሚገኙት ቆሞሶች እሰረኞን በመደገፍ እንደ ነፍስ አባትም በመሸኘት መንፍሳዊና ሰብአዊ ድጋፍ ያቀርባሉ፡ ጌታ ማንም የትም ይገኝ ልጆቹን ለብቻቸው ኣንደማይተዋቸው ቃሉን የሰጠ አምላክ ነው። ይኽ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በሮቿን በመክፈት በመቀበል ብቻ ሳይሆን በሮችዋን ከፍታ በመውጣት ወደ ተናቁት ወደ ተጠሙት ወደ ታሰሩት ወደ ታመሙት ሁሉ ደርሳ የጌታን ፍቅር በቃልና በሕይወት ታበስራለች።

ቤተሰብ ባለትዳርና ልጆች ያሉዋቸው እስረኞ ከልጆቻቸው ጋር ለመገናኘት እንዲችሉና በተለይ ደግሞ ወላጆቻቸው የታሰሩባቸው ልጆች የሚደርስባቸው ዘርፈ ብዙ ስቃይ፡ አልፎ አልፎ የእስረኛ የወንጀለኛ ልጅ እየተባሉ ሲገለጡና እነርሱም በሐፍረት ተገፍተው እንዲኖሩ የሚያስገድዳቸው ስነ አእምሮአዊና ማሕበራዊ ጫና ለከፋ ችግር እንዳይዳጋቸው ቤተ ክርስቲያን በወህኒ ቤቶች ቤተ ጸሎት ቆሞሶች አማካኝነት የተሟላ ድጋፍ ታቀርባለች። በወህኒ ቤት የሚገኙት እስረኛ ስደተኛው ደግሞ ያለበትን ዘርፈ ብዙ ችግር ተጋፍጦና አሸንፎ የእስራት ጊዜውን አጠናቆ እርምት ተጎናጽፎ እስኪወጣ ድረስም የተሟላ ድጋፍ ትሰጣለች። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ድጋፍ እስረኛው የእስራት ገደቡን አጠናቆ ነጻ ከወጣ በኋላ ከኅብረተሰብ በሰላም ተቀላቅሎ ለመኖር እንዲችል የሚያግዝ የእስራቱ ዘመን የለውጥ ዘመን የመታደስ ዘመን እንዲሆንለት በመምራት ጭምር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.