2016-11-03 13:20:00

ቅዱስነታቸው "ሙታንን በምናስብበት ወቅት የሚሰማን የሐዘን ስሜት ቢሆንም ለእኛ ክርስቲያኖች ግን የተስፋ ምልክት ነው" አሉ።


በአውሮፓዊያን የሥርዐተ-ሉትርጊያ አቆጣጠር መሠረት በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 23/2009 ተዘከሮ የዋለውን “የሁሉም ከእዚህ ዓለም ያለፉ ክርስቲያኖች መታሰቢያ ቀን” ለማሰብ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ ትልቁ ወደ ሆነውና በፊላሚኒዮ ፕሪማ ፖርታ ወደ ሚገነው የቀብር ሥፍራ በማምራት ምዕመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው ታወቀ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በታደሙበት በዚሁ ስነ-ስርዐት ላይ ቅዱስነታቸው ክርስቲያን ለነበሩ አሁን ግን በሕይወት ለሌሉ ሰዎች ነብስ ጸሎት ያደረጉ ሲሆን ከጸሎታቸው በመቀጠል በቀብር ስፍራው እየተዘዋወሩ በዝምታ ጸሎት በማድረግ በአብዛኛዎቹ የመቃብር ሐውልት ላይ የአበባ ጉን ጉን አኑረዋል።

በመቀጠልም ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን በኢዮብ ታሪክ ላይ አድርጎ የነበረና ኢዮብ “አዳኜ በሕይወት እንዳለ አውቃለሁ” ባለው ቃል ላይ ተመስርተው እንደ ገለጹት ሙታንን በምናስታውስበት ወቅት የሚሰማን እንደ ሐዘን፣ ትካዜና ተስፋ ያሉ የተደበላለቁ ስሜቶች ናቸው የሚሰሙን ካሉ ቡኋላ “የቀብር ሥፍራ የሐዘን ቦታ ነው ምክንያቱም በሞት የተነጠቅናቸው ወዳጆቻችንን የሚያሳስበን ቦታ በመሆኑና እንዲሁም የመጭውን ጊዜያችንን ማለትም ሞትን የምያስታውሰን ቦታ በመሆኑም ጭምር የተደበላለቀ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ቦታ እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸኋል። ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው በእዚህ የሐዘን ስሜት ብንሆንም እንኳን የተስፋ ምልክት የሆነውን አበባ ይዘን መምጣታችንም ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚያደርገን ተስፋን የምጭርብን ምልክት ነው ብለዋል።

ይህን የተስፋ ቃል እኛንም ይረዳናል ምክንያቱ እኛ ራሳችንም ብንሆን በተመሳሳይ መንገድ ከእዚህ ሕይወት ወደ ከሞት ቡኋላ ወዳለው ሕይወት መጓዛችን አይቀሬ በመሆኑ ነው ያሉት ቅዱስንታቸው ከሞት ቡኋላ ያለው ትንሳኤ ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል ብለዋል።

   

 








All the contents on this site are copyrighted ©.