2016-10-28 15:37:00

በኤውሮጳ የምስራቅ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መልእክት


ወቅታዊው የስደተኞች ጸዓት ለኤውሮጳ ቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት ሳይሆን ማስተናገድ የሚለውን ወንጌላዊ ተግባር በተጨባጭ ለመኖር የሚያነቃቃት አዎንታዊ አጋጣሚ ሃሳብ የተሰመረበት መልእክት በፑርቱጋል ፋጢማ ከተማ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. የተካሄደው የመላ ኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሥር የሚታቀፈው በኤውሮጳ አግሮች የሚገኙት የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ዓውደ ጉባኤ የምክር ቤቱ የፍጻሜ ሰነድ ይፋ ማድረጉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ኅትመቱ አስነብቧል።

ከምስራቅ ሥርዓት ተከታይ አገሮች ተሰደው በምዕራብ አገሮች የሚኖሩት ካቶሊካውያን ምእመናን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ላይ እይታው በማኖር እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም. በፋጢማ የማርያም ግልጸ ዝክረ 100ኛው ዓመት ከወዲሁ ምክንያት በሊስቦና ፓትሪያርክ የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማኑኤል ክለመንት አዳሚነት በፋጢ የተካሄደው የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ባወጣው የጋራ መግለጫ በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች የሚገኙት የምስራቅ ሥርዓት ከሚከተሉት አገሮች ተሰደው በምዕራብ አገሮች መኖር የጀመሩት ምእመናን መንፈሳዊ እንክብካቤና እንዲሁም የምስራቅ ኤውሮጳ ክልል አገሮች ከአምባገነናዊ ሥርዓተ መንግሥታት ነጻ መውጣት ጋር ተያይዞ የክልሉ ዜጎች ወደ ተቀሩት ምዕራብ አገሮች መሰደድና እነዚህ ስደተኞችም ከምስራቅ ተከታይ ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ከመጡ 20 ዓመታት ያስቆጠሩ ወደ ሁለተኛው ትውልድ የተሸጋሩ ምንም’ኳ የላቲን ሥርዓት በሚከተሉ አቢያተ ክርስቲያን ዘንድ የሚታቀፉ ቢሆንም ቅሉ በሚኖሩባቸው የምዕራብ አገሮች በምሉ የምስራቅ ሥርዓት ሕገ ቀኖና ሥር መንፈሳዊ እንክብካቤ እንዲያገኙ ተደርጓል። እነዚህ በምዕራብ አገሮች የጸኑት የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ አቢያተ ክርስቲያን በተስተናገዱበት አገር በሚገኘው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሥር ጭምር በመታቀፍ ሙሉ ዜግነት አግኝተው ተጣማሪ የኅብረተሰቡ ክፍል ለመሆን መብቃታቸውንም ጠቁሞ በአሁኑ ወቅት ከምስራቅ ወደ የኤውሮጳ ክልል አገሮች የሚሰደዱት በተስተናገዱበት አገር ተዋህደት እንጂ ባስተናጋጅ ባህል ሥር ካለ መዋጥ የተስተናገዱበት አገር ባህል ጋር ትክክለኛው መተዋወቅ ፈጥረው ለመኖር እንዲችሉ የሚደግፍ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲቀርብላቸው አሳስቧል ያለው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ በማያያዝ ቀጣዩ በ2017 ዓ.ም. የሚያካሂደ ዓውደ ጉባኤ በሎንደን እንዲሆን ጉባኤ መስማማቱንም አክሎ ጋዚጣው ያመልካል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.