2016-10-28 12:48:00

ቅዱስነታቸው ገንዘብን እንደ አምላክ ለማምለክ’ በታወጀው ጦርነት ለሚሞቱት ንጹኋን ሰዎች እግዚኣብሔር ያነባል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፈራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 17/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በዛሬው አደጋ በበዛበት ዓለመችን ‘ገንዘብን እንደ አምላክ ለማምለክ’ በሚደረገው ጥረት በታወጀው ጦርነት ምክንይታት በሚሞቱት ብዙኋን ንጹኋን ዜጎች  እግዚኣብሔር ያነባል ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል በተወሰደው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ የተጠቀሰውን ኢየሱስ “ዝግ ስለሆነችው” ኢየሩሳሌም “አንቺ ነብያትን ትገያለሽ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም መልእክተኞች በድንጋይ ትወግሪያለሽ” ብሎ ለእየሩሳሌም ያለቀሰበት ምንባብ ላይ ተመስርተውና እየሱስ በተልዕኮው ወቅት ያለቀሰባቸው በርካታ ጊዜያት ላይ ጭብጡን ያደረገ ስብከት እንደ ነበረም ታውቁኋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር ለልጆቹ እንደ ምያነባ ኢየሱስም ልክ እንደ አባቱ ለእየሩሳሌም ከተማ የማንባት ዝንባሌ አሳይቶ እንደ ነበረ በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ለእዚህም ማሳያ የሚሆነው እና በወንጌል የተጠቀሰው “ደሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቹዋ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ስንት ጊዜ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ፈለግሁ እናንተ ግን እንቢ አላችሁ” ብሎ መናገሩን በዋቢነት ጠቅሰዋል።

“የሆነ ሰው እንዲህ ብሎ ነበር ‘ልጆቹ በፈጸሙት ተግባር ለማልቀስ እግዚኣብሔር ሰው መሆነ ፈለገ’። በአልዐዛር መቃብር ፊት ሆኖ ማንባቱ የጓደኝነት እምባ ነው። የህም የአባትነት እምባ ነው” ማለቱን በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተመሳስይ መልኩ የጠፋው ልጅ ምሳሌ ላይ እንደ ተመለከተው ልጁ አባቱ የውርሱን እኩሌታ እንዲሰጠው ጠይቆና ቤቱን ጥሎ በሄደበት ወቅት አባቱ ያሳየውን ባሕሪ በማስታወስ እንደ ገለጹት በወቅቱ የልጁ አባት “የደረሰብኝን ነገር ተመልከቱ! የፈጸመብኝን አጸያፊ ነገር ተመልከቱ! እረግመዋለሁኝ የሚሉትንና የመሳሰሉትን ነገሮች ለጎረቤቶቹ አለመናገሩን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው የጠፋው ልጅ አባት ይህንን አለማድረጉን እርግጠኛ ብሆንም ምን አልባት ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ብቻውን አልቅሶ ይሆናል የሚል ግምት ግን አለኝ ብለዋል።

“ለምን ይመስላቸኋል ይህንን ሁሉ የምነግራችሁ?” ብለው ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ምክንያቱም ቅዱስ ወንጌላችን ስለነዚህ ነገሮች ስለማያወራና የጠፋው ልጅ ወደ ቤቱ በሚመለስበት ወቅት ልጁን በሩቁ አባቱ እንደ ተመለከተው ብቻ ማውሳቱ የሚያሳየው ይህ አባት በእየጊዜው ከቤቱ እየወጣ ልጄ ይመጣ ይሆን በሚል ጉጉት መንገድ መንገዱን ይቃኝ እንደ ነበረ የሚያሳይ መሆኑን አስረድተው በእዚህ አይነት ሁኔታ የሚኖር አባት በለቅሶ ልጁ ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቅ አባት ነው ካሉ ቡኋላ በተመሳሳይ መልክም በእዚህ ዓይነት እምባ ነው አምላካችን በልጁ አማካይነት አዲስ ፍጡር ያደረገን ብለዋል።

“አሁን ባለንበት በአደጋዎች ጊዜያት፣ ገንዘብን እንደ እግዚኣብሔር አድርጎ ለማምለክ በማሰብ በታወጀ ጦርነት ብዙ ንጹሐን ሰዎች በእነዚህ ገንዘብን እንደ ጣኦት በሚያመልኩ ሰዎች በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በቦንብ እየተደበደቡ በሚሞቱበት ወቅት እግዚኣብሔር አሁንም በማንባት “እየሩሳሌም፣ እየሩሳሌም፣ ልጆቼ ምን እየሠራችሁ ነው? እንደ ሚል አስታውሰው የጦርነት ሰላብ ለሆኑ ምስኪን ሰዎች ደግሞና ለጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎችና የሰዎችን ሕይወት ለሚሸጡ ሁሉ ተመሳሳይ ጥሪን እግዚኣብሔር እንደ ሚያቀርብ ገልጸዋል።  ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ጠቀሱት እግዚኣብሔር አባታችን ለማንባት ፈልጎ ሰው መሆኑን እና እግዚኣብሔር አባት አሁን በእኛ ጊዜም ቢሆን ሰዎች እርሱ የሰጣቸውን የሰላም እና የፍቅር ስጦታን ባለመረዳታቸው ምክንያት እግዚኣብሔር ማንባቱን እንደ ሚቀጥል በመግለጽ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.