2016-10-28 15:31:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የጾታዊ ዓይነተኛው ልዩነት መሻር በጣም ግራ የሚያጋባ ተግባር ነው


በምሥጢረ ተክሊል ላይ ያለውን የእግዚአብሔር እቅድ ውበቱና በተለያየ ምክንያት ለተለያየ አደጋ በተጋለጡት ቤተ ሰብ ላይ ያለው የምሕረቱ ውበትና አዳዲስ የዕደ ጥበብ ግኝቶችና ግራ አጋቢው የጾታ ርእዮተ ዓለም የሚደቅነውን ተግዳሮት የተሰኙ ማእከል ያደረገ መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሥም የሚጠራው ጳጳሳዊ  የሥነ ምስጢረ ተክሊልና ሥነ ቤተሰብ ተቋም ማኅበረሰብ አባላት የተቋሙ የትምህርት መባቻ ምክንያት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንት አስታወቁ።

የአቢያተ ሰብእ ቀውስ፥ እኔነት በእኛነት ላይ ጫና ሲሆን

በአሁኑ ወቅት የጋብቻና የቤተሰብአዊ ተጋምዶነት ወይንም ትስስር በፈታኝ ወቅት ይገኛል። ለአቢይ ፈተና ተጋልጦ ይገኛል። ይኽ ደግሞ ርእሰ አምላኪነት ግለኝነት እኔነት ኃላፊነት የሚለውን ተግባር የሚያገል አዲሱ የነጻነት ትርጉም ለጋራ ጥቅም ግድ የማይሰጥ እንዳውም እግምት ውስጥ የማያስገባ ስለ ሌላው የማያስብ ግዴለሽነት የሚያስፋፋ ባህል፡ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የቤተሰብ መሆናዊ እቅድ የሚያጠቃ ቤተሰብ የሚለው ትርጉሙን የሚያዛባ በጫናነት እየቀረበ ያለው ርእዮተ ዓለምና የብዙ ቤተሰብ መጻኢ ለአደጋ የሚያጋልጥ እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ያለው ድኽነት ምክንይት ለከፋ አደጋ ተጋልጦ ይገኛል።

ወቅታዊው የእደ ጥበብ ምንጣቄ ክፍት አድርጎ የሚተዋቸው ጥያቄዎች ብዙውን ግዜ የሰብአዊ መብትና ክብር ሰብአዊ ሕይወት ጭምር ጋር የሚጋጭ ትግባሬው የእኔነት በእኛነት ላይ ተጽእኖ በማድረግ ማኅበራዊነትን የሚዘነጋ ባህል በጠቅላላ ያንን ዓለምንና ታሪክን በወንድና በሴት መካከል ለሚጸናው ቃል ኪዳን በኃላፊነት የሰጠው የእግዚአብሔር እቅድ የሚጻረር ነው።

አዲሱ የሥነ ጾታ ትምህርት ግራ የሚያጋባ ነው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ሥልጣናዊ ትምህርት አዲሱ ርእዮተ ዓለማዊ መሠረት ያደረገው የሥነ ጾታ ትምህርት በቀጥታ ሳይጠቅሱ ልዩነት የበላይነት ወይን የመቀሳፈት ምክንያት አድርጎ የማየቱ አዝማሚያው እያስከተለው ያለው ጾታዊ መደናግሮች በጥልቀት በማብራራት በወንድና በሴት መካከል ያለው የጋራው ሰብአዊ መብትና ክብር ተገቢውን እውቅና ቅነኛ አክብሮት መሰጠትን ያስከትላል። ስለዚህ አለዚህ መሆናዊ  ልዩነቶች ሰብአዊነትን በጥልቅና በተጨባጭ እንዴት አድርገን ነው የምንገነዘበው?

የጾታዊ ልዩነት ያለው ክብር በጥልቀት ዳግም የሚያረጋግጠው ወቅታዊው ባህል የሚስጠው አስተዋጽኦ መካድ አይቻልም ሆኖም ይኽ ወቅታዊው ባህል መሆናዊ ልዩነትን ለአደጋ የሚያጋልጥ አዝማሚያ ለይቶ ከመቅረፍ ይልቅ ልዩነቱን በሚሽረው ባህል እየተነካ መጥቷል። በወንድና በሴት መካከል ያለው ግኑኝነት መልካም ሲሆን ዓለማንችንና ታሪክም ጭምር መልካም ሂደት ይኖረዋል። ካልሆነ ግኑኝነት መልካም ሂደት ከሌለው ዓለማችን ለመኖር የማይቻልበት ታሪክም ቁሞ ቀር ያደርገዋል።

የምሥጢረ ተክሊልና ለቆሰለው ቤተሰብ ምህረት ያለው ውብት

ያ የክርስቲያን ቤተሰብ የውህበትና የውበት ተመክሮ ለጠለቀ አስተንፍሶ ምክንያት ሊሆነን ይገባል። በተመሳሳይ መልኩም በሰዎች መካከል የተሰናከለው ለተለያየ አደጋ የተጋለጠው በቋፍ ላይ ያለው ቤተሰብ ሊታዘንለትና የችግሩ ተካፋይ በመሆን ሊታሰብለት ይገባል። ስለዚህ ለቆሰለው ቤተሰብ ማሰብ ያንን እግዚአብሔር ከመላ ሰው ዘር ጋር በወንድና በሴት መካከል ያጸናው አዶ ወይንም ትእምርት የሆነው በቤተሰብ ላይ ያለው መለኮታዊ እቅድ የሚያመላክተው  ቃል ኪዳን ከመደገፍና ከማነቃቃት ሳንቦዝን የሚከወን መሆን አለበት፡ በእርግጥ አንዳንዴ ስለ ቃል ኪዳን ወይንም ስለ ምስጢረ ተክሊል ጋብቻ በተመለከተ የምናቀርበው ቲዮሎጊያዊ ትንተናና አመክንዮ ረቂቅና ኢግብራዊ መሰል ከተጨባጭ የቤተሰብ ኑሮና ተጨባጭ ሁነት ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝንት የሌለው ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ የዚህ አይነት ቅጥ የለሽ እውነታውን ትቶ በሃሳብ ብቻ ፈትኖ ማየት በተለይ ደግሞ በጸጋው ላይ እማኔ ማኖርን በይቆይልኝ እንዲታይ በማድረጋችን ምክንያት  ምስጢረ ተክሊል ተፈላጊነቱንና ማራኪነቱን ተዳክሙል (የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ድኅረ ሲኖዶስ, 36 ተመልከት)።

የቤተ ክርስቲያን ቅርበት

ቤተሰብ ርእስ ዙሪይ ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ሁለቱ ሲኖዶሶች ያንን ለመላ ሰው ልጅ የእግዚአብሔር ፍቅር መንገድ የሚሆነው የሰብአዊ የፍቅር ምሥጢር ቤተ ክርስቲያን በጥልቅት ልታስተውለውና ልትንከባከበው እንደሚገባት ያላትን ሐዋርያዊ ኃላፊነት በአጽንኦት የተስተዋለበት ነበር። ስለዚህ የወቅቱ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልው መርሐ ግብር የብዙዎች ከዚያ የክርስትና ቃል ኪዳናዊና ቤተሰብ ትርጉም ከሆነው ክርስትያናዊ እውነት መራቅ በስፋት የሚስከለው ችግር ላይ ብቻ ያነጣጠረ መሆን የለበትም። ስለዚህ ለራቀውና ክዚህ ክርስቲያናዊ እውነት እርቆ ለሄደው የቤተ ክርስቲያን ቅርበት የሚያረጋግጥ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ  ማረጋገጡ ወሳኝ ነው፡ ቅርበት ለአዲስ ሙሽሮች። ምክንያቱም በደስታና በሚያጋጥማቸው ችግር ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲደግፋቸውና ዳግም ፍቅሩን ሕያው እንዲያደርጉ ካጋጠማቸው ሰብአዊ ቁስል እንዲፈወሱ ቅርብ በመሆን ያንን የእግዚአብሔር የፍቅርና የምህረት ትእምርት የሆነው ቤተ ክርስትያን ከልክጆችዋ ጋር ያላት የማይሻረው ተጋምዶ የምትመሰክር መሆን አለባት እንዳሉ ቸንቶፋንቲ አስታውቋል።

ቲዮሎጊያና ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በአንድ ላይ የሚጣመሩ መሆን አለባቸውም

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን በለገሱት ምዕዳን ማጠቃለያ ቲዮሎጊያና ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በጣምራነት የሚሄዱ መሆናቸው በማስገንዘብ። እውነተኛ የቲዮሎጊያ ሊቃውንት የተዋጣለት የቲዮሎጊያ ሊቅ አንድ መልካም የቲዮሎጊያ ሊቅ እንደ መልካም እረኛ በሕዝቡ ፊት የሚንበረከክ በገዛ እራሱ የሚዘጋ ሳይሆን ወደ ጎዳና የሚወጣ ሕዝብን የሚፈልግ በጎዳና ወጥቶ የሰው ልጅ ቁስል የሚፈውስ መሆን አለበት። የቤተ ክርስቲያንን ጠመቅ ትምህርት ከወንጌላዊነትና ከቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ውጭ የማያደርግ ያንን የጌታ ግልጸት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚተረጉም እምነት የሚያስተልፈው የቤተ ክርስቲያን ባህል ሃብቱ የሚያደርግ በግብረ ኖልዎ የሚተረጉም መሆን አለበት እንዳሉ ቸንቶፍንቲ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.