2016-10-26 15:09:00

ቅዱስነታቸው ጦርነትን፣ ርሃብንና ድኽነትን ሸሽተው ለሚሰደዱ ሰዎች አቀባበል ይደርገላቸው ዘንድ ጥሪ አቀረቡ።


ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 16/2009 በቅዱስ ጴትሮስ አደባባ የጠቅላላ አስተምህሮን ለመከታተል ለመጡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኚዎች እንደ ገለጹት ጦርነትን፣ ርሃብንና ድኽነትን ሸሽተው በመፍለስ ላይ የሚገኙ ስደተኞች አቀባበል ይደርገላቸው ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ታወቀ።

የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴትሮ አደባባይ በዛሬ እለት ማለትም በጥቅም 16/2009 ያስተላለፉትን ጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! በእዚህ በያዝነው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት አካላዊ የምሕረት መገለጫ የሆኑትን ተግባራት ማለትም የባዕድ ሀገር ሰውን መቀበልና የታረዘን ማልበ የሚሉትን ጭብጦች በዛሬ እለት እንመልከታለን።

ኢየሱስ እነዚህን ሁለቱን አበይት አካለዊ የምሕረት ተግባራትን ከመጨረሻው የፍርድ ቀን ጋር አገናኝቶ ነበር። በአሁን ወቅት “የባዕድ ሀገር ሰው” በመካከላችን ያለውን ስደተኛ ሰው ነው። በሁለም ደርጃ ይህ በመታየት ላይ የሚገኘው የስደተኞች ክስተት ግልጽነት እና የአንድነት ምላሽ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት ጦርነትን፣ ርሃብንና የከፋ ድኽነትን ሸሽተው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥራቸ እየበዛ ስለሚገኝ ለእነዚህ ወንድሞች እና እህቶች እንክብካቤን ማድርገ ያስፈልጋል። ከእኛ በፊት ያለፉ ጠንካራ ክርስቲያን ወንድማቻችን እና እህቶቻችን እንዳደረጉት መልካምነት ለምሳሌም ቅዱስ ፍራንቸስክ ዛቪየር ካብሪን እንዳደርገው እኛም ይህንን ችግር በፍጥነት ለመፍታት ለጋስ መሆን እና የተለያዩ የፈጠራ መንገዶችን መፈለግ ይኖርብናል። ስለዚህም “የታረዘን ማልበስ” የሚለው በይበልጥ የሚያመለክተው ሰባዊ ማብታቸው ለተገፈፈባቸው ሰዎች ከእዚህ መካራቸው ወጥተው በመልካም ሆኔታ ላይ መሆናቸውን ማረጋጋአጥ ማለት ነው። የክርስቶስ ተከታዮች እንደ መሆናችን መጠን ልባችንን ለተቸገሩ ሰዎች መዝጋት አይጠበቅብንም። ራሳችንን ለሌሎች ክፍት በማድረጋችን ሕይወታችንን እናበለጽጋለን፣ በሕበረተሰባችን ሰላም ይሆናል በእዚህም ረገድ ሁሉም ሰዎች እግዚኣብሔር የሰጣቸውን መብት ያስከብራሉ ማለት ነው ካሉ ቡኋላ አስተምህሮዋቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.