2016-10-26 14:52:00

ቅዱስነታቸው የሕይወት ሁሉ ፈጣሪ፣ የሕልውናችን ምንጭ የሆነው እግዚኣብሔር የተልዕኮኋችን ዋና ዓላማ ሊሆን ይገባል አሉ።


በትላንትነው እለት ማለትም በጥቅምት 14/2009 ልማዳዊውን የመልዐከ እግዚኣብሔር ጸሎትን ለመከታተል በርካታ ምዕመናንና የሀገር ጎብኚዎች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙ ሲሆን በእለቱ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት አስተምህሮ እኛ ፍጡራን ነን ነገር ግን ለዘላለም ከእግዚኣብሔር ጋር እንድኖር የታጨን ነን ካሉ ቡኋላ የሕይወት ሁሉ ፈጣሪ፣ የሕልውናችን ምንጭ የእውነት እና የደስታ ምንጭ የሆነው እግዚኣብሔር የተልዕኮኋችን ዋና ዓላማ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ የተከበረው የዓለማቀፍ የተልዕኮ ቀንና አስመልክተው እና በእለቱ በተነበቡ ምንባባት ላይ ትኩረትን አድርገው ባስተላለፉት አስተምህሮ “ዛሬ ተልዕኮና የብርታት ጊዜ ነው፣ ራሳችንን መስዋዕት በማድረግ በወንጌል የሚገኘውን ደስታ ለማግኘትና ተልዕኮኋችን በራሱ የሚያስገኘውን ብርታት መልሰን ለመጎናጸፍ  ዳዴ እያልን እርምጃችንን የምናጠናክርበት ጊዜ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ብራታት ብቻውን ድል ልያጎናጽፈን አይችልም ብለዋል።

“ምንም እንኳን ብርታት ውጤታማ የመሆን ማረጋገጫ ባይሆንም ብርታት የሚጠይቅ ጊዜ ላይ እንገኛለን” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ብራታት ለመዋጋት እንጂ ለማሸንፍ አይጠቅምም፣ ወንጌልን ለማወጅ እንጂ ሰዎችን ለመለወጥ አይሠራም ብለዋል።

“ዛሬ ከእኛ የሚጠበቀው ነገር ምንም ዓይነት ክርክርና ኋይልን ሳንጠቀም በድፍረት በዓለም ውስጥ አማራጭ ይዘን መገኘትና ሊሆን ይገባል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ከእኛ የሚጠበቅብን ነገር ቢኖር የክርስቶስ ኋያልነትን፣ ልዩ መሆኑንና የሁሉም አዳኝ መሆኑን ሳንረሳ በብርታት ራሳችንን ለሁሉም ክፍት ማድረግ” የጠበቅብናል ብለዋል።

“ብራታት” አሉ ቅዱስነታቸው አስተምህሮኋችውን በቀጠሉበት ወቅት “ብራታት እብሪተኛ ሳንሆን በማያምን ሰው ፊት እንድንቆም ይረዳናል” ብለው “በዛሬው ጊዜ ከእኛ የሚጠበቅብን ልክ ዛሬ ከሉቃስ ወንጌል (18.9-14) ላይ የተጠቀሰውን የፈሪሳዊውና የትሑቱ ቀራጭ ሰው ምሳሌ ላይ እንደ ተጠቀሰው ትሑቱን ቀራጭ ሰው መምሰል ይጠበቅብናል” ካሉ ቡኋላ ይህ ትሑት የሆነ ግብር ሰብሳቢ ወይም ቀራጭ ሰው ቀና ብሎ ወደ ሰማይ ለማየት ሳይደፍር ጌታ ይቅርታ እንዲያደርግለት ይለምን ነበር ካሉ ቡኋል ይህም ምሳሌ የተጠናቀቀው ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፣ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁል ከፍ ይላል እንዳለው ራሳችንን ዝቅ በማድረግ ለተልዕክኋችን መዘጋጀት ይጠበቅብናል ብለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.