2016-10-22 14:11:00

ካርዲናል ተርክሰን የፋይናንስ ሥርዓትና የዓለማቀፍ የኢኮኖሚ መዋቅር የሰው ልጆችን መብት ያከበረ መሆን እንደ ሚገባው አሳሰቡ።


በቅድስት መንበር የፍትህ እና የሰላም ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑ ካርዲናል ተርክሰን በጥቅምት 7/2009 ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ገለጹት የፋይናንስ ሥርዓት እና የዓለማቀፍ የኢኮኖሚ መዋቅር የሰው ልጆችን መብት ያከበረ መሆን እንደ ሚገባው አሳሰቡ። በሮም እየተካሄደ በነበረው ሦስተኛው የአውሮፓ የማይክሮ ፋይናንስ ምድረክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ካርዲናል ተርክሰን ያደረጉት ንግግር የጀመረው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አስተላልፈውት ከነበረው ምልዕክት በመጥቀስ “በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የአባካኚነት ባሕልና የስነ-ስብእ (antroplogical) ቀውስ የፈጠረውን  የእሴቶች ሁሉ ቆንጮ ባለ ጠግነት መሆኑን የሚገልጸውን አስተሳስብ የሚያወግዙ አወዲ መልዕክቶች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በተከታታይ አውጥተው እንደንበረ አስታውሰዋል።

ካርዲናል ተርክሰን በንግግራቸው ወቅት በማይክሮ ፋይናንስና በአነስተኛ ወለድ የሚሰጠው ብድር መልክም ኢኮኖሚያዊ ገጽታዎች እንደ ነበሩት እና ይህም ማህበራዊና ባሕላዊ ለውጦችን ማስገኘቱንም አወድሰዋል። ይህ የምክክር መድረክ የሕዝብ፣ የግልና አትራፊ ያልሆኑ ተቋማትን ለማቀራረብ ዓላማ ያለው መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ይህም ውይይቶች እንዲደረጉና በተለያየ አቅጣጫ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ልማትና የብድር ተቋማት ተደራሽነታቸውን በማጥናት ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦች የሚፈልቁበት መድረክ ነው።

ካርዲናል ተርክሰን በንግግራቸው እንደ ገለጹት ቅዱስነታቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነው በተመረጡበት ማግስት በጻፉት “ኢቫጄሊ ጋውዲዩም” በሚለው አወዕዲ መልዕክታቸው ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ አሁን ያለውን የኢኮኖሚ መዋቅር ብዙኋኑን በማግለል የተመሰረተ ማሆኑንና የአባካኝነት ባሕል የተጠናወተው ኢፍታዊ በሆነ መልኩ የተቀረጸ ነው ለዛም ነው ቅዱስነታቸው “ገዳይ የሆነ ኢኮኖሚ ስርዐት ነው” ያሉት በማለት ጨምረው ገልጸዋል።

ካርዲናል ተርክሰን በመቀጠልም “ላውዳቶ ሲ” የተሰኘውን አወዕዲ መልዕክት በመጥቀስ ንግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ቅዱስነታቸው “የድርጅቶችንና የግለሰቦችን ትርፍ ከፍ በማድረግ ብቻ ነው ችግሮች ለፈቱ የሚችሉት” የሚለውን ምህታታዊ የሆነውን የገበያ አስተሳሰብን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ይጠበቅብናል” ያሉትን በድጋሚ በማስታወስ ንግግራቸውን ቀጥለው ትርፍን በበለጠ ከፍ ማድረግ ይገባል የሚል አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች በአከባቢ ላይ እየደረሰ ያለውን ውድመት ያቆማሉ ብሎ ማሰብ እውነታ ይኖረዋል ወይ? ብለው ጥያቄን አንስተው ትርፍን ለማጋበስ ብቻ ተኩረት በተሰጠው ቦታ የተፈጥሮን የሂደት መዋቅርን፣ ነገሮች ወደ ተፈጥሮአዊ ባሕሪ የሚቀየሩበት ሂደትና የሚተካኩበት የተፈጥሮ ሁኔታን ያስባሉ ማለት ወይም ደግሞ በሰዎች ጣልቃ ገብነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳውን የስነ-ምዕዳር ስርዐት ረቂቅነትን የረዳሉ ማለት በጣም ያዳግታል ብለዋል።

ካርዲናል ተርክሰን ጨምረው እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ የሻርልማኝ ሽልማት አሸናፊ በሆኑበት ወቅት ከተናገሩ ቃል በመጥቀስ እንደ ገለጹት ቅዱስነታቸው “የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ተጠቅሚ ያደረገ ሳይሆን ማንኛውንም ተራ ሰው እና ማኅበረሰቡን በአጠቃላይ ተሳታፊ የሚያደርግ አዲስ፣ አሳታፊና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ መዋቅር በአስቸኳይ በማውጣት ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባዋል” ብለው እንደ ነበረ አውስተው ይህንንም መተግበር ማለት “ከሰዎች ይልቅ ለስሌት ማለትም ትርፍ ለማጋበስ ብቻ ትኩረት ከሚሰጠው የኢኮኖሚ ፍሰት ስርዐት ወደ ማህበረሰብ አቀፍ ስርዐት ለመጓዝ የሚደረግ ጥሪ ማለት ነው” ማለታቸውም ተገልጽኋል።

በአንድ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያወሱትን በመጥቀስ “በመንገድ ላይ የሚኖር አንድ ሽማግሌ ሰው በብርድ መሞቱን ከሚዘገብ ይልቅ የገበያ ምንዛሪ 2 ነጥብ ያህል ሲቀንስ የሚዘገበው ዜና በከፍተኛ ሁኔታ ሽፋን እንደ ሚሰጠው” መግለጻቸውን በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ካርዲናል ተርክሰን የዚህም ዋንኛው መንስሄ በአሁኑ ወቅት ዓለማችን እየተጋፈጠችሁ የምትገኘው የስነ-ሰብእ ቀውስ ድምር ውጤት መሆኑን ገልጸው በእዚህ አንጻር ስንመለከተው ከኢኮኖሚው ችግር በበለጠ ችግሩ ጥልቅ መሆኑን ገልጸው ይህም “የሰው ልጆች የሁሉም ነገር የበላይ ናቸው የሚለውን የሚክድ ቀውስ” መሆኑንም በጽኖት ገልጸው ገንዘብና ሐብት ልክ እንደ ጣኦት የሚመለኩበት ደረጃ ላይ ደርሰናል በማለት ጨምረው ገልጸኋል።  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህ በአሁኑ ጊዜ በስፋት እየታየ የሚገኘውን ፍታዊ ያልሆነ የኢኮኖሚ መዋቅር በመተቸት ብቻ አለማብቃታቸውን በመጥቀስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ካርዲናል ተርክሰን ቅዱስነታቸው ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ ይችላል ያሉትንም የመፍትሄ ሐሳቦችንም በዝርዝር አስቀምጠው እንደ ነበር አውስተው ይህም እያንዳንዱ የሰው ልጆችን መብት ባስከበረና ለስነ-ምዕዳን እንክብካቤን በማድረግ እንዲከናወን ለሁሉም እድል የፈጠረ መዋቅር እነደ ሆነ ጨምረው ገልጸኋል።

“ለሰው ልጆች የሥራ እድልን በመፍጠርና ስልጠናዎችን በመስጠት የማብቃት እርምጃዎች ላይ በማተኮር ማህበራዊ ኢኮኖሚን መገንባት” አስፈላጊ መሆኑን የጠቀሱት ካርዲናል ተርክሰን በእዚህም ረገድ ቅዱስነታቸው “ለሙስና የተጋለጠውንና ትርፍን ማጋበስ ላይ ትኩረት ያደረገውን የኢኮኖሚ ፍሰት ወደ ማሕበራዊ የኢኮኖም ፍሰት መሻጋገር የመሬት ተጠቃሚነትንና በሥራ በተፈጠረ እድል መኖሪያዎችን የመገንባት መብትን ያረጋግጣል” ቅዱስነታቸው ብለው እንደ ነበረ ካርዲናል ተርክሰን አስታውሰዋል።

ካርዲናል ተርክሰን በንግግራቸው ወቅት አጉለተው እንደ ገለጹት አዲስ የኢኮኖሚ መዋቅር ያስፈለገበትንም ምክንያት በመዘዘር ንግግራቸውን የቀጠሉት ካርዲናል ተርክሰን ይህም አዲሱ ማኅበራዊ የግብይት ስርዐት ሥራ አጥነትን የሚቀርፍ፣ እየጨመረ የመጣውን ኢፍታዊነትንና በስነ-ምዕዳር ላይ እየደረሰ ያለውን ውድመት የምያስወግድ፣ በተጨማሪም የሰው ልጆች ሁሉ መሠረታዊና ሊጣሱ የማይችሉ መብቶችን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ካርዲናል ተርክሰን “መዋቅሮችን በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃት ኢፍታዊነትን እንዲስፋፋ እያደርጉ የሚገኙት የገበያ መርና ትርፍን ለማጋበስ ብቻ ታቅዶ የሚከናወን የኢኮኖሚ ስርዐት ተወግዶ  የድሆች ችግር ሙሉ ለሙሉ እስካልተወገደ ድርስ ለዓለም ችግሮች መፍትሄን ማምጣት አይቻልም” የሚለውን ኢቫጄሊ ጋውዲዩም ከተሰኘው አወዲዕ መልዕክት በመጥቀስ ነግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.