2016-10-21 16:04:00

የቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምዕዳን ለአጎስጢኖሳውያን ጠቅላይ ጉባኤ ተሳታፍያን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን በሚገኘው በቀለመንጦስ የጉባኤ አድራሽ በአጎስጢኖሳውያን ገዳም በሚያካሂደው የማኅበሩ ጠቅላይ ጉባኤ ለመሳተፍ ሮማ የገቡትን ገዳማውያንን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቲ አስታወቁ።

በተካሄደው ግኑኝነት ቅዱስነታቸው ያንን የሱታፌ ፈጣሪያን መሆን የሚለው በቅዱስ አጎስጢኖስ የተመለከተውን መንፈሳዊነት ማእከል በማድረግ ይኽም አንድ ልብና አንድ መንፈስ ሆኖ እንደ ወንድማማቾች መኖር የሚል ጥሪ መሆኑ አሳስበው፡ እግዚአብሔር ዋስትናችንና ደስታችን ነው። መላ ተስፋችን ባንተ ታላቅ ምህረት ላይ ነው። የምታዘውን ንገር የምትሻውን ሁሉ ጠይቅ” የሚለውን የቅዱስ አጎስጢኖስ ቃል ዋቢ በማድረግ እማኔአቸውን ሁሉ በጌታ ምኅረት ላይ የሚያኖሩ የተስፋ ሰዎች ሁኑ፡ ጌታ አያደናግርም አያታልልም ምሕረቱንና መሐሪነቱን በሚያስቀድም አባታዊፍ ፍቅሩ የሚመራ አባት ነው።

በዚህ በምታካሂዱት ጠቅላይ ጉባኤ ሁሌ ተአዝዞ በማስቀደም ኅዳሴ ለመሻትና ማኅበሩን ለማስመንጠቅ በምታደርጉት ውይይት የማኅበሩ ተስፋና ተግዳሮች ሁሉ ለጌታ አወክፉ። እግዚአብሔር የሚሰጠው ፍቅርና በሁሉ ሕይወት ህልወቱ የሚያረጋግጥበት ሃሳብ ያለፈው ታሪክ ብራት ከመሆኑም ባሻገር ወደ እውነተኛው የማኅበሩ መንፈሳዊ መርሆ ለመመለስ በማጣጣም በሙላት በመኖር ያለፉት ተግዳሮች እንዴት ለመቀረፍ መበቃቱ በማጤን ወቅታዊው ተግዳሮት ለመግጠም የሚደገፍና ይኽ ጉዞ በዚህ ከኢየሱስ ጋር በሚደረገው ጉዞ ጸሎት ይሆንና ውስጣዊ መንጻትንና ህዳሴን ያሰጣል። ህልው ጊዜ በተጋጋለ ስሜት በነጻነት መንፈስ ተመርቶ በመኖር የእግዚአብሔር ፍቅር በሕይወታችን የሚሸኝ መሆኑ ታምኖ የዚህ ፍቅር ተዘክሮ አላፊ ቢሆንም ለየት የሚያደርገው ህልውና ቀጣይ መሆኑ በመታመን ይከንን ቀጣይነት በማስተናገድ ለህዳሴ ዝግጅዎች መሆን ያስፈልጋል።

እግዚአብሔር የሕይወታችን ማእከል እንዲሆንና እርሱ እንዲመራ መፍቀድ በክፋት መንፈስ ላለ መገዛት ብርታት ይሆነናል። ስለዚህ የሱታፌ ፈጣሪያን የእግዚአብሔር ፍቅር መስካሪያን ሁኑ። ተልእኮአችሁ ይላሉ ለአጎስጢኖሳውያን ጠቅላይ ጉባኤ ተሳታፊያን ፍቅርና የፍቅር ነው፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ ያለው ሰብአዊ ክቡር ለይቶ የሚያውቅ ኅብረተሰብ እንዲገነባ የተላካችሁ ናችሁ። እያንዳንዱ ለእያናንዱ ጸጋ ነው። ይኸንን ሁሉ ታምኖ ለመኖር በሕይወት ከጌታ ጋር መገናኘት ወሳኝ ነው።

ኃይላችን የጌታ መሐሪው ፍቅር እንጂ ያሉን ሃሳቦችና እቅዶቻችን አይደሉም ይኽ መሐሪ ፍቅር ነው የሚለውጠን ሕይወትንም የሚሰጠን ብለው ወንድማማችነት የሚኖር ተጨባጭ ተመክሮ እንዲሆን ማርያም ታማልድልን ብለው የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ መኒከቲ ገልጧል።








All the contents on this site are copyrighted ©.