2016-10-21 16:16:00

ብፁዕ ካርዲናል ሙዩለር፥ በነዲክቶስና ፍራንቸስኮ፡ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት


የካቶሊክ  አንቀጸ እምነት ለሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ገርሃርድ ልድዊግ ሚዩለር በነዲክቶስ 16ኛና ፍራቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚል ርእስ ሥር ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተዛማጅ ባህል አምባገነናዊነት የሚል በስልጣናዊ ትምህርታቸው ላይ እንኳር ያደረጉት ሃሳብ እንዲሁም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የግዴለሽነት ማለትም የምን ገዶኝ ባህል በዓለማዊነት ትሥሥር ሂደት መስፋፋቱ የሚተነትነውን ስልጣናዊ ትምህርታቸው ማእከል በማድረግ የደረሱት መጽሐፍ፥ የእውነትና የሐሰት ድንበር የመልካምና የእኵይ ተግባር ጠረፎች በማግለል አደባልቆና አደናግሮ ተነባቢነቱንና ትንተናውን ለባለቤት ይተው የሚል ባህል የሚያስከትለው ጉዳት ቤተ ክርስቲያን በሁለቱ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት እርሱም በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥልጣናዊ ትምህርት ሥር በጥልቀት የተሰጠበት ተንታኝ ትምህርት የሚያትት አዲስ መጽሓፍ ለንባብ ማቅረባቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አሊና ቱፋኒ አያይዘው፥ ባህል መሳዩ ኢባህል ለይተው በማቅረብ ቤተ ክርስቲያን በሥልጣናዊ ትርምህቱ አማካኝነት አባላቶቿ ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያንን ውሉደ ክህነት በተያያዘ መልኩም ለምእመናን የምትሰጠው ሕንጸት በስፋት እንደተነተኑት አስታውቋል።

የብፁዕነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተክለ ሰብነትና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተክለ ሰብነት፡ ያላቸው ቲዮሎጊያዊ እሳቤና ብሎም በቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ዘንድ ኵላዊነት ተላብሶ እንዴት ባለ መልኩ ለመተግበር እንደሚቻል። ሁለቱም አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ያላቸው ቲዮሎጊያዊ አናስር ክሪስቶሎጊያ ነው። ሆኖም ይኸንን ክሪስቶሎጊያ ማእከል ያደረገው የሁለቱ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ቲዮሎግያ በቤተ ክርስቲያናዊ ሥልጣናዊ ትምህር ዘንድ አንድ ወጥ ቢሆንም አገላለጡና የእያናንዱ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ግላዊ ገጠመኝ ግምት በመስጠ በቀጣይነትና በእዳሴ በማካተት፥ ቀጣይነትና አዲስነቱን በጥልቀት የተነተኑበት መጽሓፍ መሆኑ ያብራሩት የቫቲካን ርዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አሊና ቱፋኒ አክለው፥ የዚህ የብፁዕ ካርዲናል ሙዩለር አዲስ መጽሐፍ የመቅድሙ ጽሑፍ ደራሲ ቸሳረ ካቫለሪ፥ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 17 ቀን 2015 ዓም. ከ10 ዓመት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ፍቱን ሥልጣን በሚል ርእስ ሥር የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየተ ብፁዕ ካርዲናል ሚዩለር የቅዱስ ጴጥሮስ ቀዳሚነት በበነዲክቶስ 16ኛ እርእስተ ሊቃነ ጵጵስና በሚል ርእስ ሥር ዙሪያ በተደረሰው አቢይ መድብለ መጽሓፍ በልዩ ተቆጣጣሪነት የመሩ መሆናቸው በማስታወስ ብፅዕነታቸው በዚህ መድብላዊ መጽሐፍ ዘንድ የመጽሐፉ ዋና ርእስ በማስደገፍ በመጽሐፉ የሚካተት ድርሰት ማቅረባቸውም ካቫለሪ አስታውሰው ብፅዕነታቸው በዚህ ባለንበት ዘመን ለቤተ ክርስቲያን ለውሉደ ክህነት ለገዳማውያን ለምእመናን ብቻ ሳይሆን ለወቅታዊ ኅብረተሰብ ተጋርጦዎችና የባህሎች ተግዳራት የሆኑትን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በእሷ ፊት የተደቀነ መሆኑ ካለ ምንም ጥርጥር ለይታ በማወቅና በመተንተን፥ ዓለማዊነት ለክርስትና እምነት ያለው ክብር ማለትም ልቅ ዓለማዊነት ማመንና አለ ማመን ያው ነው ከሚለው ዓለማዊነት ውጭ፡  የመንግሥት ኢሃይማኖታዊነት ርእየት የሚቀበል በክርስትና እምነት የሚገለጠው ኩላዊ እሴት የሚያበክር ዓይነት ዓለማዊነትና በአሁኑ ወቅት የር.ሊ.ጵጵስና ሚና፡ በናዝራዊ ኢየሱስ ላይ የተመሰረተች ቤተ ክርስቲያ አሃድነትና አንድያነት ፡ የቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያናዊነትና እንዲሁም የአቢያተ ክርስትያን መከፋፈል፡ በአሁኑ ወቅት አድነት ላይ በማተኮር በአቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚካሄደው የጋራው ውይይት፡ የሐዋርያነት ጥሪ፡ የቅድስና ጥሪ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በተሰኙትና ሌሎች አርስቶች ዙሪያ ሁለቱ በነዲክቶስና ፍራንቸስኮ ባላቸው መንፍሳዊ ውህበት አማካኝነት በማንበብና በማስተዋል ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ለምእመንናና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች የሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት በመጽሐፉ ዘንድ ተብራርቶ ይገኛል።

ወቅታዊው ሰው ላይ ያንዣበበው ቀውስ፡ ቅጥ የለሽ ርእሰ አምልኮነት ግጭት የመሳሰሉት ችግሮች ሁሉ በወንጌልና በቤተ ክርስቲያን ትውፊትና በቤተ ክርስቲያን አበው ትምህርት ዓይን ሥር በመመልከትና በመተንተን ለወቅታዊው ዓለም የመወጣጫ መንገድ በማሳየት የሚሰጡት ትምህርት በእውነቱ የሮማ ጳጳስ ለመላ ሰው ልጅ ለመደገፍና ወደ ቅን መንገድ ለመምራት ያለው ኵላዊ ጥሪው ምድራዊ አድማስ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አድማስ ሥር በማንበብ የሚሰጠው አገልግሎት የሚያትት መጽሐፍ መሆኑ እንዳሰመሩበትም ቱፋኒ ያስተላለፉት ዘገባ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.