2016-10-14 14:37:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "ጌታን በሙልኋት ለመከተል እንቅፋት ከሚሆኑ መሰረታዊ ነግሮች አንዱ ግብዘነት ነው" አሉ።


ቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 4/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ጌታን በሙልኋት ለመከተል እንቅፋት የሚሆኑ መሰረታዊ ነግሮችና ወደ ግብዘነት የሚመሩንን ማታለልና ውሸትን በማሰውገድና በተለይም በዙ ነገሮችን እሰራለሁ እያልን ምንም ነገር በተግባር ሳንፈጽም እንድንኖር ከሚያደርገን ተለዋዋጭ የሆነ ባሕሪን የተላበሰ መፈሳዊነትን ማሰወገድ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በዛሬ ወንጌል (ሉቃስ 12.1-7) ኢየሱስ “ከአይሁዳዊያን እርሾ” ማለትም ከግብዝነት እንድንጠነቀቅ አዳራ ይለናል በማለት ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው “መልካም የሆነ እና መልካም ያልሆነ እርሾ መኖሩ ልብ ሊባል ይገባል” ብለው የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዲሰፋ የሚያደርግ እርሾ አለ በሌላም በኩል ደግሞ በውጫዊ ገጽታችን ብቻ የእግዚኣብሔር መንግሥት ተካፋዮች እንድንሆን የሚያደርገን እርሾ ደግሞ ሁለተኛው አይነት እርሾ ነው በማለት አብራርተዋል። 

እርሾ ሁልጊዜም ቢሆን መልካም ከሆነ ቀጣይነት በሆነ መልኩ አንድን ነገር እንድያድግ ያደርጋል፣ ጥሩ የሆነ ዳቦ ወይም እንጀራ ለማግኘት ያስችለናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአንጻሩም ግን መልካም ያልሆነ እርሾ አንድን ነገር አያሳድግም ካሉ ቡኋላ ይህንንም አባባላቸውን ለማጠናከር የልጅነት ትውስታቸውን እንደ ሚከተለው ገልጸዋል።

“ልጅ እያለሁ በዓል በሚከበርበት ወቅት አያታችን ብስኩት ትሰራልን ነበረ፣ ይህንንም ስታደርግ ሊጡ በጣም ስስ የምስላል። ከእዚያም በመጥበሻል ላይ በፈላ ዘይት ውስጥ ይህንን ስስ ሊጥ ስትጨምረው ቀስ በቀስ እየተነፋ እይተነፋ ይመጣል። ስንበላው ግን ውስጡ ባዶ ነው። አያታችንም በእኛ ቋንቋ የአንጋገር ዘይቤ ይህ ውሸታም ብስኩት ነው ምንም የሚረባ ነገር የለውም ውስጡም ባዶ ነው ትለን ነበር’ ካሉ ቡኋላ ኢየሱስም “ጥሩ ካልሆነ የፈሪሳዊያን እርሾ ተጠንቀቁ” ይል እንደነበረ አስታውሰው፣ ይህ ምን አይነት እርሾ ነው? ብለው ጣያቄን አንስተው መልሱም ቀላልና ቀላል ነው ግብዝነት ነው ካሉ ቡኋላ ከእዚህ የፈሪሳዊያን እርሾ ከሆነው ግብዝነት መጠንቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

ግብዝነት ማለት ጌታን በልባችን ስንሸነግለውና ነገር ግን ልባችን ከእርሱ ርቆ በሚገኝበት ወቅት የሚፈጠር ነገር ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ግብዝነት ውስጣዊ መከፋፈል ማለት ነው አንደኛው የሰውነት ክፍላችን አንድ ነገር ይላል ሌላኛው ደግሞ ሌላ ተግባር ይፈጽማል በአጠቃላይ ተለዋዋጭ የሆነ መንፈሳዊነትን ያመጣል በማለት ገልጸዋል።  ግብዝነት ተለዋዋጭ ባሕርዕ ያለውና አንድ አንዴም መልካም እና ትክክለኛ ይመስላል ነገር ግን በውስጡ ሾተል አለው አይደል? በማለት ጠይቀው እሲቲ ሂሮድስ እናስብ በታላቅ ጉጉት ነገር ግን ውስጥ ውስጡን በጣም ፈርቶ ስልነበር ሰባሰገሎችን ተቀበላቸው። እነርሱን በተቀበለበት ወቅት “ሄዳችሁ እዩ እና ተመልሳችሁ ኑ! የት እንዳለም ንገሩኝ እና እኔም ሄጄ እስግድለታለው! ነገር ግን ሊገለው ነበር የፈለገው። ግብዝነት ሁለት ገጽታዎች አሉት ተለዋዋጭ ባሕሪ አለው የምላችሁ ለእዚሁ ነው ብለዋል።

ኢየሱስ እነዚህን የሕግ አዋቂዎች በተመለከተ “እነዚህ የሚናገሩትን በትግባር አይፈጽሙም” ብሎዋቸው ነበር ይህም የግብዝነት ሌላኛው መገለጫ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የመኖር ህልውና መሆን የሚገባው ግን የሚናገሩትን በተግባር የሚያውሉ ሰዎች ናቸው እንጂ ነገሮችን በአፍ ብቻ ሊነገሩ ሳይሆን የሚገባ በተግባርም ሊመንዘሩ ይገባል ብለዋል። ግብዝነት ግን በአንጻሩ የሚያምነው በመናገር ብቻ እንጂ  በትግባር በሚፈጸም ነገር አይደለም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የግብዝነት ትልቁ ድክመት እራሱን መውቀስ አለመቻሉ ነው ብለው በራሴ ላይ ስህተት አለ ብሎ አይቀበልም ነገር ግን የሌሎችን ስህተት ለመቁጠር ግን ፈጣን ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸው በቀጠሉበት ወቅት እኛ እንድናድግ እያደረገን ያለው መልካሙ እርሾ ነው ወይስ መጥፎ እርሾ የሚልውን ለመለየት እርሳችንን መመርመር ይጠበቅብናል ብለው “በምን ዓይነት መንፈስ ነው ነገሮችን እያከናወንኩኝ የምገኘው? በምን አይነት መንፈስ ነው እየጸለይኩኝ የምገኘው? በምን አይነት መነፈስ ነው ሌሎች ሰዎችን የምቀርበው? ገንቢ በሆነ መንፈስ ነው? ወይም በአየር ላይ ተበትኖ እንደ ሚቀር አይነት ሐሳብ ነው? ብለው ጥያቀን በማንሳት ስብከታቸውን ቀጥለው ራሳችንን ማታለል የለብንም፣ ውሸትም መናገር አያስፈልግም ነገር ግን ሁልጊዜ ቢሆን እውነትን መናገር ያስፈልጋል ብለው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.