2016-10-13 16:23:00

ብፁዕ ካርዲናል ኮርት ኮኽ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በጆርጂያና በአዘርበጃ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉዞ ምዘና


 የክርስቲያኖች አሃድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 30 ቀን እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በጆርጂያና አዘርበጃን ስለ አካሄዱት 16ኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉዞ በማስመከት ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ከተሰየመው ከቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የሰጡት ምዘና እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ለንባብ በቅቷል።

ብፁዕነታቸው ሐዋርያዊው ጉዞ ዓቢይ ልባዊ መቀራረብና መተሳሰብ የተካነ መስተግዶ የጎላበት ነበር በማለት በተለይ ደግሞ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጸጋዊነታቸው ፓትሪያርክ ኢሊያ ዳግማዊ መካከል የተካሄደው ግኑኝነት ቅዱስ አባታችን ጆርጂያ እንደደረሱ ፓትሪያርኩ ወደ አየር ማረፊያ ድረስ በመሄድ ለቅዱስ አባታችን በተደረገው የእንኳን ደህና መጡ የአቀባበል ሥነ ስርዓት መሳተፍ በሁለቱ አበይት የሃይማኖት መሪዎች መካከል የተካሄደው ክሌአዊ ግኑኝነት ቅዱስ እባታችን ትብሊዚ የሚገኘው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የፓትሪያርክ ካቴድራል መጎብኘትና እንዲሁ ብዙ የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን ለቅዱስ አባታችን የሮማ ጳጳስ የሚል ያላቸውን መጠሪያ የማይቀበሉና የሮማ ጳጳስ ብለው እንደማይጠሩዋቸው የሚታወቅ ነው ሆኖም ኢሊያ ድግማዊ ቅዱስ አባታችንን የሮማ ጳጳስ ሲሉ ጠርቷቸዋል። ቅዱስ አባታችን በበኵላቸም ጸጋዊነታቸው ኢሊያ ዳግማዊን የእግዚአብሔር ሰው ሲሉ በአክብሮት ብቻ ሳይሆን ያንን በሁለቱ የሃይማኖ መሪዎች መካከል የነበርው መቀራረብና ጥልቅ ግኑኝነት ብጥልቀት ገልጠዋል።

እርግጥ ነው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ የጆርጂያ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ኢጲስ ቆጶሳት አልተሳተፉም ነገር ግን ይኸንን አለ መሳተፍ ብዙ ትኵረት የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም። አለ መሳተፉ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ጥልቅ ወዳጅነት የተካነው ግኑኝነት የሚሽር አይደለም። የጎደለውም ከማየት ይልቅ ያለውን ክብር ሰጥቶ ማየት ይበልጣል። ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በምታደርጋቸው ቲዮሎጊያዊ ውይይቶች አወዛጋቢ ቲዮሎጊያዊ ስነ ቤተ ክርስቲያናዊ ወዘተ ጥያቄዎችን ለመመለስ ትሞክራለች። የዚህ የውይይት ዘይቤ ሂደቱም በሥነ አኃዝ አነጋገር የጋራ አካፋይ በሆነው ላይ ረግጦ መቀራርብ የሚል ነው፡ ለምሳሌ መንፈሳዊ ጸሎት ፍቅር ወዳጅነት በማስከተል ባህላዊ ትውውቅ መከወን ያስፈልጋ። ይኽ ደግሞ ከእርስ በእርስ መቀራረብ የሚመጣው ትውውቅ የሚያሰማ ግኑኝነት ይሆናል። ሌላው በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ለአንድነት ታልሞ የሚደረገው ጉዞ በቲዮሎጊያዊ ሥነ እሳቤ ዙሪያ ብቻ የሚታጠር ሳይሆን ግብረአዊነትንም የሚመለከት ነው፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የጋራው ግኑኝነት በተግባራዊ ዘርፍ እንዲያተኵር ይሻሉ። በግብረ ሠናይ አገልግሎት ሰላም በማስፋፋት ለጋራ ጥቅም መሥራት የሚሉትን ተደራሽ ዓላማዎች የሚመለከት ይሆናል። በምዕራቡና በምስራቁ ዓለም በሚግኙት አቢያተ ክርስቲያን የተከሰተው ልዩነት በቲዮሎጊያዊና ጠመቃዊ ትምህርት ጥይቄ ክትልት ሳይሆን ለልዩነቱ ትልቁ ምክንያት ያለው ያስተሳሰብና የባህል መራራቅ ነው። ስለዚህ ያ ተራርቆ የነበረው ዓለም ዛሬ ዓለማችን በደረሰበት ስልጣኔ ምክንያት በቀላሉ ለመገናኘትና ለመቀራረብ የሚቻል በመሆኑ እነዚህ አቢያተ ክርስቲያን ሊቀራረቡና ባህላዊና እሳቤአዊ ትውውቅ ማረጋገጥ ይኖባቿል ማለት ነው፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጆርጂያ ተገኝተው ባስደመጡ ንግግር መከፋፍልን እንደ አንድ በሽታ ገልጠው፡ መከፋፈልና መለያየት የሕመም ስሜት በማለት ገጠዉታል፡ የዚህ ህመም ፍቱን መድሃኒትም በክርስቶስ ዘንድ ያለውን አሃድነት  ነው ሰለዚህ ልዩነቱ ይወገድ ዘንድ ክርስቶሳዊ አሃድነት ዳግም ማረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት የሚያስገነዝብ ንግግር ነው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ እ.ኤ.አ. ገና ባልተገባደደው 2016 ዓ.ም. ያካሄዱዋቸው ግኑኝነቶች ብሔራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ዑደቶች በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን በክርስቶስ ዘንድ ያለው አሃድነት ለመኖር የሚያነቃቃ ነው፡ ለዚህ ማረጋገጫ ይሆናል ብለው ብፁዕ ካርዲናል ኩኽ እ.ኤ.አ. የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በሃቫና ከመላ ሩሲያና ሞስኮ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት በለስቦ ደሴት ከቍስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊና በአቴንስ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ሃይሮንይሞስ ጋር በመሆን ያካሄዱት ጉብኝት ጠቅሰው በለስቦ የተካሄደው ጉብኝት ዓላማውም ለስደተኞችና ለተፈናቃዮች ቅርበት በማረጋገጥ ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ለሚጋለጡት ወንድሞቻችን ድጋፍና ትብብር በማቅረብ ሁሉም በጋራ ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የሚያጋልጠው ችግር መፍትሔ በማፈላለጉ ጉዳይ እንዲጠመዱ ጥሪ ለማስተላለፍ የሚል ነው፡ ስለዚህ ይኽ ግኑኝነት ደግሞ ግብረዊ ላይ የጸና ነው፡ የእኔ ተከታዮች መሆናችሁ ሌሎች እንዲያውቁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል የሚያስተገብርም ነው፡ ይኽ ደግሞ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ታልሞ በሚደረገው ውይይት በግብረ ሠናይ ዓላማ ላይ ማተኰር አለበት ከሚለው የፍቅር ሥራ የተንደረደረ መሆን አለበት የሚል ነው ብለዋል። አሃድነት ጉዞ ነው። የዚህ ጉዞው መሪም መንፈስ ቅዱስ ነው። በመንፈ ቅዱስ መርህነት ሥር አብሮ መጓዝ የአሃድነት ጎዳና ነው በማለት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጆርጂያና አዘርበጃን ሐዋርያዊ ጉዞ ምዘና እንዲህ ባለ መልኩ የሰጡት ቃለ መልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.