2016-10-12 14:33:00

ቅዱስነታቸው "የፊት ማስዋቢያ በመጠቀም የሐይማኖትን ውጫዊ ገጽታን ብቻ ለማሳመር መሞከርን" መተው ይኖርብናል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በታላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 1/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕት ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት ኢየሱስ   የፊት ማስዋቢያ በመጠቀም የሐይማኖትን ውጫዊ ገጽታን ብቻ በማሳመር ያልሆኑትን ለመሆን መሞከርን ትተን መልካም ሥራዎችን በትዕትና እንድናከናውን አደራ ይለናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ከተነበበውና ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ገላቲያ ሰዎች በጻሐፈው (ገላ. 5.1-6) የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግና በእለቱ በተነበበው ወንጌል (ሉቃ. 11.37-41) ኢየሱስ ፈሪሳዊያንን ለውጫዊ ገጽታዎች ብቻ ሙሉ በሙሉ ትኩረትን በመስጠት እምነት የሚጠይቀውን ውስጣዊ ንጥረ ነገርን ችላ በማለት ውጫዊው ገጽታ ብቻ ማጽዳት ላይ ትኩረት በማድረጋቸው ምክንያት እንደ ገሰጻቸው በሚያወሳው ሐሳብ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበር ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተለ እንደ ገለጹት እነዚሁ ፈሪሳዊያን ኢየሱስ የእነርሱ ህግ አካል የሆነውን የመንጻት ሥነ-ሥርዐት ሳይፈጽም ማለትም እጁን ሳይታጠበ ምግብ መብላት በመጀመሩ እንደ ወቀሱትም ቅዱስነታቸው አስታውሰው ኢየሱስም “እናንተ ፈሪሳዊያን የብርጭቆውንና የሳሕኑን ውጭውን አጥራታችሁ ታጥባላችሁ፣ በውስጣችሁ ግን ቂምና ክፋት ሞልቱዋል” (ሉቃስ 11.39) ብሎ እንደ መለሰላቸው አውስተው ኢየሱስ በወንጌል ውስጥ የዚህን ዓይነት ምላሻ ደጋግሞ ለእነዚሁ ሰዎች መልሶ እንደ ነበረ አስታውሰው ውስጣችሁ   ነፃ ኣይደለም የተሞላውም በመልካም ነገር ሳይሆን በክፉ ነገር ነው ይላቸው እንደ ነበረና “ከእግዚኣብሔር የመጣውንና ኢየሱስ የሚሰጠንን ፍትህ  ባለመቀበላችሁ የተነሳ ባሪያዎች ናችሁ” ማለቱንም ገልጸዋል።

በሌላ የወንጌል ክፍል የተጻፈውንና ኢየሱስ ጸሎት በምያደርግበት ወቅት በስውር መሆን እንዳለበት፣ እንዲሁም ያለምንም አፍረትና በኩራት በሰዎች ዘንድ ተደናቂነትን ለማግኘት በማሰብ እነዚህን ተግባራት የሚፈጽሙ ሰዎችን መምሰል እንደ ሌለብን አሳስቦን እንደ ነበር ገልጸው በምትኩም አምላካችን በአጽኖት የሚያዘን የትህትናን መንገድ መከተል እንዳለብን መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንዳብራሩት ኢየሱስ እንዳለው ዋናው አስፈላጊው ነገር በመበዠታችን ያገኘነው ነጻነት መሆን እንዳለበት ካሉ ቡኋላ “ይህ ውስጣዊ ነጻነት መልካም ነገሮችን መፈጸም የሚገባን ለታይታ፣ ጥሩባ ወይም መለከትን እየነፋን ሳይሆን ነገር ግን ትክክለኛው የእምነት ጎዳና በምያስተምረን መልኩ በትዕትናና በውርደት መስመር” መፈጸም ይገባናል ብለዋል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ ኢየሱስ ራሱን እንዳዋረደና ባዶ እንዳደረገ ገልጾላቸው እንደ ነበረ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ራስ ወዳደንትን፣ ስስታምነትን፣ ትብዕትን፣ ኩራትንና ዓለማዊነትን ከውስጣችን ለማስወገድ ዓይነተኛ መንገድ ነው ብለዋል።

በተቃራኒዊው ኢየሱስ የወቀሳቸው እነዚህ ሰዎች “መዋቢያን” የተጠቀመ እምነት ተከታዮች መሆናቸውን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ውጫዊ ገጽታቸውን በመገንባት መልካም ሰው ይመስላሉ ውስጣቸው ግን ኢየሱስ ጠንከር ያለ ቃል ተጠቅሞ እንደ ገለጸው “በውስጣቸው በሞቱ ሰዎች አጥንትና በእርኩስ ነገር ሁሉ የተሞሉ በውጭ ግን በኖራ ተለስነው የሚያምሩ የመቃብር ግንቦችን ትመስላላችሁ፣ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ክፋት ሞልቶባችኋል” ብሎ የተናገረውን ሰዎች እንደ ሚመስሉም ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ኢየሱስ መልካም ተግባራትን በትህትና እንድንፈጽም ይጠይቀናል ካሉ ቡኋላ መልካም ተግባራትን ስንፈጽም በትህትና መሆን ይገባዋል የሚለውን የኢየሱስን ቃል አስታውሰው ነገር ግን መልካም ተግባራትን በትህትና የማንፈጽም ከሆነ እንደ መልካም ሥራ ሊቆጠርልን አይችልም ምክንያቱም ያለ ትህትና የተፈጸመ መልካም ሥራ የመነጨው ለእራሳችን በጎ በማሰብ እንጂ በኢየሱስ ስለተበዤን ባለመሆኑ ነው ብለዋል። ደኅንነትን ልንጎናጸፍ የምንችለው “የትህትናና የውርደትን መንገድ ስንከተል ብቻ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “ምክንያቱም ትህትና ያለውርደት በፍጹም ሊገኝ የማይችል ነገር በመሆኑ ነው፣ ይህንንም ውርደት እየሱስ በመስቀል ላይ አሳይቶናል” ብለዋል።

“ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “በእዚህ ዓይነት ጎዳና ላይ መራመድ እንዳይደክመን ይረዳን ዘንድና የታይታ፣ የውጫዊ ገጽታን ብቻ የሚያሳይና አስመሳይ የሆነ እምነትን ሳንሰለች ማስወገድ እንድንችል ኢየሱስ እንዲረዳን መጠየቅ ያስፈልጋል” ካሉ ቡኋላ “ መልካም ተግባራትን በጸጥታ በማከናወን መጉዋዝ እንድንችል ውስጣዊ ነጻነታችንን እንዲጠብቅልን ልንለምነው ያስፈልጋል፣ ለዚህም ፀጋውን ይሰጠን ዘንድ እንለምነው” ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.