2016-10-11 13:10:00

ቅዱስነታቸው "ማሪያም እናታችን በእርግጥም በአብነት እንድንመለከተታት የተሰጠችን እናታችን ናት" ማለታቸው ተገለጸ።


በመስከረም 29/2009 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ ሲከበር የነበረውን የቅድስ ማሪያም ኢዩቤሊዩ በዓል ማብቅያን አስመልክቶ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው በእለቱ ባሰሙት ስብከታቸው ለምዕመናን እንደ ገለጹት “በአብነት ተሰታናለች፣ ማሪያም እናታችን በእርግጥም በአብነት እንድንመለከተታት የተሰጠችን እናት ናት” ካሉ ቡኋላ “ጌታ ላደርገልን ነገር ሁሉ ማመስገን ይገባል፣ ማመስገን በጣምም አስፈለጊ ነገር” መሆኑን አጥብቀው ገልጸዋል።

የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን ቅዱስነታቸው በመስከረም 29/2009 ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ ሲከበር የነበረውን  የእመቤታችንንን ቅድስት ድንግል ማሪያም የኢዩቤሊዩ በዓል እለት ያሰሙትን ስብከት እንደሚከተለው ተርጉመነዋል።

በዛሬ የሰንበት ቀን (ሉቃስ 17.11-19) የተነበበል የወንጌል ቃል እግዚኣብሔር ለሚሰጠን ስጦታዎች ሁሉ በመደነቅ እና በምስጋና እውቅናንን መስጠት እንደ ሚገባን ይጋብዘናል። ወደ ሞቱ እና ወደ ትንሳኤው የሚወስደውን መንገድ በመጓዝ ላይ ሳለ 10 ለምጻሞች መጥተው በሩቁ ቁመው እና ለመዳን ምክንያት የሆናቸውን መከራ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው “ኢየሱስ ሆይ! መምህር ሆይ! እባክህን ራራልን!” ይሉት ነበር። ታመው ስለነበረ የሚያድነቸውን ሰው በመፈለግ ላይ ነበሩ። ኢየሱስም አያቸውና በሕግ እንደ ተጻፈው ከሕመማቸው መዳናቸውን ማረጋገጫ ያገኙ ዘንድ “ሂዱ! ሰውነታችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው። ኢየሱስ ይህንን ያደረገው ያለ መክንያት አልነበረም፣ የእመነታቸውን ጥልቀት ለማወቅ ስለፈለገ ነው እንጂ። በእዚያን ጊዜ በእርግጥ 10 ለምጻሞች አልተፈወሱም ነበር። ፈውሱን የተገናጸፉት ኢየሱስ ያዘዛቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው በመሄድ ላይ በነበሩበት ወቅት ነበር። ከእዚያን ቡኋላ በደስታ እራሳቸውን ለካህናት ካሳዩ ቡኋላ መንገዳቸውን ቀጠሉ። ይህንን ታላቅ ስጦታ ሰው በሆነው በልጁ በኢየሱስ የሰጣቸውን እግዚኣብሔርን ዘንግተውም ነበር።

ከ10 ለምጻሞች አንዱ ብቻ ያውም ሳምራዊ ሰው፣ ምርጥ በተባሉ ሰዎች መኋል ይኖር የነበረ የሰው ሀገር ሰው፣ ያውም ከአህዛብ ወገን የሆነ! ይህ ሰው በእምነታቸው ከተፈወሱ ሰዎች ማኋል ባይሆንም ቅሉ፣ ነገር ግን ለተደርገለት ፈውስና ለተሰጠው ስጦታ ምስጋናንን ለማቅረብ ተመለሰ። ኢየሱስ ከተጣለበተት ያነሳውና ያዳነው በመሆኑ እውነተኛ ካህን መሆኑን እውቅናን ሰጥቶ ወደ እርሱ መንገድ ተመልሶ ከደቀመዛሙርቶቹ አንዱ ለመሆነ በቃ።

ምስጋናን ለማቅረብ መቻል፣ ጌታ ስላደረገልን ገር ሁሉ ማመስገን ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው! ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን ነገር “አመሰግናለሁ?” ለማለት እንችላለን ወይ? ምን ያህል ጊዜ ነው በቤተሰባችን፣ በማሕብረሰቡ እና በቤተ ክርስትያን ውስጥ “አመሰግናለሁ” ለማለት የበቃነው? ምን ያህል ጊዜ ነው ለረዱን ሰዎች፣ ለእኛ ቅርብ ለሆኑ ሰዎች፣ በሕይወት ጎዳን ከእኛ ጋር ለተጉዋዙ ሰዎች “አመሰግናለሁ!” ያልነው ምን ያህል ጊዜ ነው? ብዙን ጊዜ ነገሮችን በቸልተኛነት ነው የምንቀበላቸው። ይህንንም በእግዚኣብሔር ላይም እንፈጽማለን። ጌታን ቀርበን የምያስፈልገንን ነገር መጠየቅ ቀላል ነው፣ ነገር ግን ተመልሰን ምስጋናን ለእርሱ ማቅረብ. . . ይከብደናል. . .ኢየሱስም የዘጠኙን አመስጋኝ ያልነበሩትን ለምጻሞችን ሁኔታ በማጉላት “ከለምጽ የነጹት ሰዎች 10 አልነበሩምን? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ? እግዚኣብሔርን ለማመስገን ተመልሶ ከመጣው ከዚህ የባዕድ ሀገር ሰው በቀር ሌላ የለምን?”(ሉቃስ 17.17-18) ብሎ ነበር።

በዚህ ኢዩቤሊዩ በዓል አብነት ትሆነን ዘንድ ተሰታናለች፣ ማሪያም እናታችን በእርግጥም አብነታችን በመሆኑዋ እንድንመለከተታት የተሰጠችን ናት። የመልዐኩን መልዕክት ከሰማች ቡኋላ የምስጋና መዝሙር በመዘመር እና እግዚኣብሔርን በማመስገን ድምጿን ከፍ በማድረግ “ነብሴ ጌታን ታከብረዋለች. . .” አለች። ያለን ነገሩ ሁሉ የእግዚኣብሔር ስጦታ መሆኑን እውቅና በመስጠት “አመሰግንሀለውኝ” ማለት እድታለማምደን እመቤታችን ታግዘን ዘንድ ልንጠይቃት ያስፈልጋል። ከዚያን ቡኋላ ብቻ ነው ደስታችን ሙልኋት ሊያገኝ የሚችለው።

ለማመስገን ትሁት መሆን ያስፈልጋል። በመጀመሪያው ምንባብ የንጉሥ አራም የጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን ታሪክ ሰምተናል (2 መ.ነግሥት 5.14-17)። ከለምጹ እንዲፈወስ ከድኸው አገልጋይ እና እንደ ጠላት ይቆጥረው የነበረውን ነቢዩ ኤልሳዕ ያቀረበለትን ምክር በተስፋ ተቀበለ። ናማን በተጨማሪም ራሱን ዝቅ ለማድረግ ዝግጁ ነበረ። ነብዩ ኤሊያም የጠየቀው ከባድ የሚባል ነገር ሳይሆን በቀላል ቋንቋ በዮራዳኖስ ወንዝ እንዲታጠብ ብቻ ነበር የጠየቀው። ይህ ቀላል ጥያቄ ናማንን አወዛግቦት እና አናዶትም ነበረ። እንደነዚህ ዓይነት ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያስቀምጥ እግዚኣብሔር በእውነት እግዚኣብሔር ሊባል ይችላልን?” በማለት ወደ ቤቱ ተመልሶ ለመሄድ ፈልጎም ነበር። ነገር ግን በዮርዳንስ ወንዝ ለመታጠብ ተስማማ ከልመጹም ወዲያሁኑ ነጻ።

ከማንም በበለጠ ሁኔታ የማሪያም ልብ የእግዚኣብሔርን ስጦታ መቀበል የሚችል በጣም ትሁት የሆነ ልብ ነው።  እግዚኣብሔር ሰው መሆን ስለፈለገ በቤተ መንግሥት በስልጣን እና በሐብት በብዛት የምትኖረውንና ታላላቅ የሚባሉ ነገሮችን ማከናወን የምትችለውን ሴት ሳይሆን የመረጠው በናዝሬት የምትገኘውን አንድ ተራ ወጣት ሴትን መረጠ። የእግዚኣብሔርን ስጦታ ለመቀበል ወይም ደግሞ በቁሳዊ፣ በአዕምሮአዊ እና በእቅዳችን ተማምነን ራሳችንን በራሳችን ዘግተን መሆን አለመሆናችንን ራሳችንን እንጠይቅ።

ትርጉም በሚሰጥ መንገድ: ንዕማን እና ሳምራዊው ሰው  ሁለትም የባዕድ አገር ሰዎች ነበሩ። እኛ መልካም የሆኑ እሴቶቻችንን በምንዘነጋበት ወይም በአሽቀጥረን በምንጥለበት ወቅት መልሰን እንድንገናጸፋቸው የምያደርጉን የባዕድ ሀገር ሰዎች ወይም ደግሞ የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ ሰዎች መልሰን እንድንገነዘብ ያደርጉናል። በጎሬበታችን የሚኖሩ ሰዎች የባዕድ ሀገር ሰዎች በመሆናቸው የተነሳ እናገላቸዋለን ነገር ግን በጌታ መንገድ ላይ እንዴት መጓዝ እንዳለብን ልያስተምሩን ይችላሉ። የእግዚኣብሔር እናት ከእጮኛዋ ዮሴፍ ጋር በመሆን ከሀገር  ርቆ መኖር ምን ማለት እንደ ሆነ ያስተምሩናል። እርሷም እራሷ  ከቤተሰቦቿ እና ከጓደኞቿ ተለይታ በግብፅ በነበረችበት ወቅት የባዕድ ሀገር ሰው ሆና ኑራለች። ነገር ግን እምነቷ ችግሮቿን እንድትወጣ አስችልኋታል። ይህንን ቀላል የሆነ የእናታችንን ምሳሌ በመውሰድ ሁልጊዜም ወደ ኢየሱስ መመለስ እንድንችል እና በምሕረቱ የተነሳ ስለተቀበልናቸው ብዙ ስጦታዎች አመስጋኞች እንሆን ዘንድ እንድትረዳን አማላጅነቷን እንለምን። ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.