2016-10-07 11:23:00

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በዚህ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየታዩ የሚገኙ የሰላም መታጣት ያሳስባታል፡፡


 

የሐዘን መግለጫ

 

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በዚህ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየታዩ የሚገኙ የሰላም መታጣት ያሳስባታል፡፡

 

ማንኛውም ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሁልጊዜ ጸሎቷና ምኞቷ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በተላለፈው መመሪያ መሠረትም በመላው ሃገሪቱ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የመስከረም ወርን በጸሎት እያሳለፈች ትገኛለች፡፡ ምዕመናንም በዚህ ጥሪ መሠረት ተግተው ስለ ሰላም እየጸለዩ ይገኛሉ፡፡

 

መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ. ም. በቢሾፍቱ በተከበረው በኤሬቻ በዓል ላይ በተፈጠረው ሁኔታ በጠፋው የሰው ሕይወት እጅግ ማዘኗን ትገልጻለች፡፡ ለሞቱት ሰዎች እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው እንጸልያለን ለቤተሰቦቻቸውና ለወላጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡

 

በሃገራችን እየታየ ያለውን አለመረጋጋት መሠረታዊ ችግሮችን መንግሥትና ሕዝብ ተነጋጋሮ ወደ መፍትሄው እንዲመጣ ትሻለች፡፡ በዚህም መሠረት ሃገራችን በሰላምና በአንድነት ጉዞዋን እንድትቀጥል ሁላችንም ተባብረን እንድንጸልይ ቤተክርስቲያናችን ትማጸናለች፡፡

 

እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝቦቿን ይባርክ፡፡

 

 

አባ ሐጎስ ሐይሽ

ጠቅላይ ጸሐፊ

 








All the contents on this site are copyrighted ©.